ፈልግ

ISRAEL-PALESTINIAN-CONFLICT-BORDER

ቅድስት መንበር፡- በጋዛ ‘እየተፈጸም ያለው ዘግናኝ ጥቃት’ ማብቃት አለበት ማለቷ ተገለጸ።

የቅድስት መንበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር “መላው ህዝብ አስከፊ የሽብር ድርጊት የሚያስከትለውን መዘዝ እንዳይከፍል ማድረግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጋዛ ስላለው ጦርነት “ጥልቅ ስጋት” ተሰምቷቸዋል፣ እና የተኩስ አቁም ጥሪያቸውን በተደጋጋሚ እያቀረቡ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ገብርኤሌ ካቺያ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ረቡዕ ጥር 15/2016 ዓ.ም  ባስተላለፉት መልእክት ገልጸዋል።

በጋዛ ውስጥ "ሊታሰብ ከሚችለው በላይ ያለው" ችግር

ሊቀ ጳጳሱ "በጋዛ ያለው ሰብአዊ ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ ነው" እና "ከምንገምተው በላይ ስቃይ" እንደሚያስከትል አስምሮበታል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእስራኤል እ.አ.አ በጥቅምት 7/2023 ዓ.ም የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በተደጋጋሚ ያወገዙ ስሆን “መላው ሕዝብ የሽብርተኝነት ድርጊት የሚያስከትለውን መዘዝ እንዳይከፍል በጣም መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

“ራስን ለመከላከል የሚወሰደው ማንኛውም እርምጃ በልዩነት እና በተመጣጣኝነት መርሆዎች መመራት እና የአለም አቀፍ የሰብአዊ ህጎችን ማክበር አለበት” ብለዋል ።

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ አክለውም “ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የአምልኮ ቦታዎች፣ በጋዛ ያለውን ሁከት ለሸሹት የመጨረሻ አማራጭ ቦታዎች የሆኑት እነዚህ ሁሉ ለወታደራዊ ኢላማዎች ጥቅም ላይ መዋልና በዚህም ምክንያት ጥቃት እየደረሰባቸው መሆናቸው በጣም አሳዛኝ ነገር ነው” ብለዋል።

"እንዲህ ያለው የሁሉም ወገኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማቆም አለበት እና እነዚህ ጣቢያዎች በአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ መሰረት ለእነሱ የሚሰጠውን ጥበቃ ማረጋገጥ አለባቸው" ያሉት የቅድስት መንበር ተወካይ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊቀ ጳጳስ ካቺያ እንዳሉት “በጋዛ የሚገኙ ታጋቾችን ለማስፈታት እና በጣም አስፈላጊ የሆነውን የሰብአዊ ርዳታ ስርጭት ለማመቻቸት አስቸጋሪ ቢሆንም ለውይይት ቦታ ይፈቅዳል” ብለዋል።

የሁለት-ግዛት መፍትሄን በተመለከተ የታደሰ ቁርጠኝነት

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ንግግራቸውን ያጠናቅቁበት “እያንዳንዱ ሰው ክርስቲያን፣ አይሁዳዊ፣ ሙስሊም፣ የትኛውም ሕዝብ ወይም ሃይማኖት ቢሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ፣ ክቡር እና በሰላም የመኖር መብት ያለው ነው ” ያሉ ስሆን ለእንዲህ ዓይነቱ ሰላም እጅግ በጣም አዋጭ የሆነው መንገድ የሁለት መንግሥታት መፍትሔ ሆኖ እንደሚቀጥል የቅድስት መንበር አቋም ደግመዋል፣ “ለኢየሩሳሌም ከተማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጠ ልዩ ቦታ” አለው፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ከፍልስጥኤም መንግስት እና ከእስራኤል መንግስት መሪዎች ጋር” ይህንን መፍትሄ “በአዲስ ቁርጠኝነት” መከተል አስፈላጊ ነው ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

26 January 2024, 13:40