ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ጳውሎስ 6ኛ እና የክርስቲያኖችን አንድነት የሚያራምዱ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቴናጎራስ ር. ሊ. ጳ ጳውሎስ 6ኛ እና የክርስቲያኖችን አንድነት የሚያራምዱ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቴናጎራስ  

ካርዲናል ኩርት፥ የወንድማማችነት ምልክት ቁርጠኝነት ያለበት የአንድነት መንገድ እንደሆነ አስገነዘቡ

ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፥ የክርስቲያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት እያከበረች በምትገኝበት በዚህ ወቅት፥ በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ኅብረት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ፥ በወንድማማችነት መቀራረብ ለአንድነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚገልጽ ነው” በማለት አስረድተዋል። በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ከ60 ዓመታት በላይ የዘለቀውን ግንኙነት በማስታወስ፥ ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ በቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ እና በኤኩመኒካል ፓትርያርክ አቴናጎራስ መካከል በተደረገው ታሪካዊ ግንኙነት ላይ በማስተንተን አስተያየታቸውን አክፍለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ እና የክርስቲያኖች አንድነት ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ አቴናጎራስ በኢየሩሳሌም የተገናኙበት 60ኛ ዓመት ባለፈው ጥር 5 እና 6 ተከብሮ ውሏል። ይህ ግንኝነት በቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዩጄንዮስ አራተኛ እና በብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዮሴፍ ዳግማዊ መካከል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ1438 እስከ 1439 ዓ. ም. በፌራራ በተካሄደው ጉባኤ ወቅት ካደረጉት ግንኝነት በኋላ ለመጀመሪያው ጊዜ የተደረገ እንደ ሆነ ታውቋል። 

ይህ የሚታወስበት ጠቃሚ በዓል በመጀመሪያ ደረጃ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የነበረውን ግንኙነት ለማየት የሚያስችል ፍሬያማ ዕድል እና ያለፈውን ጊዜ በተግባር ለመግለጽ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ የሚያሳምም ታሪካዊ ትውስታን ማጽዳት የሚቻለው በይቅርታ መሆኑን አውቆ፥ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ1964 ዓ. ም. ጀምሮ ለተገኙት መልካም ውጤቶች ምስጋናን በማቅረብ እና እውቅናን በመስጠት ለሚቀጥሉ አዳዲስ እርምጃዎች ፈቃደኛ መሆን ነው።

በሕጋዊነ ወደ በጎ አድራጎት መንገድ መመለስ

በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም የተደረገው ጉባኤ በተለይ ሁለቱ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በወንድማማችነት መንፈስ መተቃቀፋቸው አብያተ ክርስቲያናቱ ማለትም የካቶሊክ እና ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እርስ በእርስ በመዋደድ ወደ በጎነት መንገድ ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት ያረጋገጡበት በመሆኑ በታሪክ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። ይህም ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ለእርቅ ያላቸውን ፈቃደኝነት በዓይኖቻችን የተመለከትንበት መልካም ምልክት ነው።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2023 ዓ. ም. ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ዓመታዊውን የቅዱስ እንድርያስ በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ወደ ዕርቅ የሚደረገው ጉዞ የጀመረው ሁለቱ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለአብያተ ክርስቲያናቱ ወንድማማችነት ያላቸውን የጋራ እውቅናን በሚገልጽ መንገድ በመተቃቀፍ የጀመሩት በዚህ ምክንያት ነው” በማለት ተናግረዋል።

ወንድማማችነትን የሚገልጽ ይህ መሳሳም ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው ነው። አጋፔ እና ወንድማማችነት የአምልኮ ሥርዓትን እና የቅዱስ ቁርባን አንድነትን የሚወክል በመሆኑ በኢየሩሳሌም የተጀመረው የአንድነት ጉዞ ግብ እና የቅዱስ ቁርባንን ኅብረትን እንደገና የሚመሠርት ነው። በእርግጥም አጋፔ እንደ ቤተ ክርስቲያን አካሄድ በእውነት ሲለማመዱት የቅዱስ ቁርባን አጋፔ መሆን አለበት። በኢየሩሳሌም የተገናኙት የሁለቱ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዓላማ ይህ ነበር። በዚህ አጋጣሚ መጪው ትውልድ አንድ ጌታን በኅብረት የሚያወድሱበት፣ በቅዱስ ቁርባን ሥጋውን እና ደሙን ተካፍለው የሚያመሰግኑበትን አዲስ ቀን መባቻን አይተዋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በታኅሣሥ 7 ቀን 1965 ዓ. ም. በኢየሩሳሌም የተካሄደው የማይዘነጋ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ግንኙነት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1054 ዓ. ም የተፈጠረውን ልዩነት ለማስተካከል መንገድ የጠረገ ነበር። በፋናር በሚገኘው በቁስጥንጥንያው ፓትርያርካዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እና በሮማ በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ባለው የፍቅር መቀራረብ ላይ እንቅፋት እንዳያጋጥም የሚል የጋራ ፈቃደኝነት አረጋግጠዋል። በዚህ ውድ እና ሕጋዊ አስገዳጅነት የ 1054 ዓ. ም. ክስተቶች እና ውጤቶቹ ለታሪካዊ ይቅርታነት የዋሉ እና በተመሳሳይ መንገድም ልዩነቱ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ዝርዝር ጉዳይ እንዳልሆነ ይፋ ተደርጓል።

የበጎነት ውይይት እርቅን በማምጣት አገልግሎት

እነዚህ የማይረሱ ክስተቶች የክርስቲያኖች የአንድነት ውይይት የሚጀምርበት የበጎነት መንገዶች ናቸው። “ቶሞስ አጋፒስ” በሚለው የጋራ ሠነድ ላይ እንደተጠቀሰው፥ በሚቀጥሉት ዓመታት ውስጥ ጥልቅ ጉብኝቶችን በመለዋወጥ እና በብዙኃን መገናኛዎች አማካይነት የሚደረግ የተጠናከረ የበጎነት ውይይቶች መነሻ ነበሩ። የበጎነት ውይይቱ በተለይ በቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስትያን እና በሮማ ቤተ ክርስትያን መካከል በጋራ በሚደረጉ በዓላት ወይም ሌሎች አስፈላጊ ክስተቶች ላይ በሚደረጉ የእርስ በእርስ ጉብኝቶች መልካም የጋራ ባሕል የሚታይበት አገላለጽ ተገኝቷል። አዲስ ለተመረጡት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ብዙም ሳይቆዩ በቁስጥንጥንያ ፋናር የሚገኙትን የክርስቲያኖች አንድነት አራማጅ ፓትርያርክ መጎብኘታቸው በትርጉም የተሞላ ልማድ ሆኗል። በሮም እና በቁስጥንጥንያ መካከል በተደረገው የማኅበረ ቅዱሳን ግንኙነት ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ነበር፥ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መሪ ሆነው የተመረጡበት በዓል ለማክበር ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ወደ ሮም መምጣታቸው ያደገ የወዳጅነት ምልክት ነበር።

በበጎነት የሚካሄድ የጋራ ውይይት ዛሬም ሆነ ወደ ፊት ሊቀጥሉ እና ሊጠናከር የሚገባ ምልክት ነው። ምክንያቱም በታሪክ ዘመናት ሁሉ በምስራቅ እና በምዕራቡ ዓለም ያሉ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዲቀራረቡ ትልቅ አስተዋፅዖ ስለሚያደርግ ነው። ብፁዕ ካርዲናል ዋልተር ካስፐር ይህንን ሂደት በአጭሩ እና በጥልቀት ሲገልጹ፡- “ክርስቲያኖች በዋነኛነት በክርክራቸው እና በተለያዩ አስተምህሮአቸው ምክንያት ራሳቸውን አላራቁም። የተራራቁት ይልቁንም በአኗኗራቸው ልዩነት የተነሳ እርስ በርሳቸው በመለያየታቸው ነው። ይህ እድገት ሊገለጽ የሚችለው ገና ከጅምሩ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ምዕራባዊ እና ምስራቁ ዓለም በተለያየ መንገድ ሲቀበል እና እንደ ተለያዩ ባህላዊ ወጎች እና ቅርፆች ይተላለፍ ስለ ነበር ነው። እነዚህ ልዩነቶች ቢኖሩም፥ በምስራቅና በምዕራቡ የመጀመሪያው ሺህ ዘመን የነበረው የክርስቲያን ዓለም እንደ አንድ ቤተ ክርስቲያን የኖረ ነበር። ነገር ግን ክርስቲያኖች ቀስ በቀስ እየተለያዩ ስለሄዱ፥ ያንን ለማስቀረት እርስ በርስ መረዳዳት ጀመሩ።

ከእነዚህ ታሪካዊ ዕድገቶች አንጻር፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ ምስራቅ እና ምዕራብ መከፋፈል በእውነት መነጋገር ይቻል እንደሆነ ራሳችንን መጠየቅ አለብን። “ክፍፍል” እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ 1054 ዓ. ም. ጋር የተያያዘ፥ ቁስጥንጥንያ እና ሮም መለያየታቸውን ሲናገሩ ነው። ሆኖም ይህ ከታሪካዊነት ይልቅ ተምሳሌታዊ ነው። በእርግጥም በእውነተኛው የቃሉ ትርጉም በምስራቅ እና በምዕራብ ቤተ ክርስቲያን መካከል መከፋፈል አልነበረም። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 1054 ዓ. ም. ሆነ በሌላ ጊዜ ምንም ዓይነት የጋራ ውግዘት አልነበረም። ካርዲናል ዎልተር ካስፐር ይህን ጠቃሚ እውነታን በማስመልከት ሲጽፉ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በምስራቅ እና በምዕራብ መካከል እያደገ ስላለው መከፋፈል እንጂ ስለ መከፋፈል መናገር የለብንም። በታሪክ ዘመናት በሙሉ አለመግባባቶችን እና ውዝግቦችን ያስከተለው ይህን መራራቅ በትዕግስት እና ከሁሉም በላይ በበጎነት መንገድ በመገናኘት በቅንነት ለማሸነፍ መሞከር ይቻላል።

 

 

 

23 January 2024, 16:38