ፈልግ

የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ  

የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አጠቃላይ እይታ

በአሁኑ ጊዜ 184 ግዛቶች ከቅድስት መንበር ጋር ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ከነዚህም 89 የልዐኡካናቸው ቡድን ኤባሲዎች በሮም ከተማ ውስጥ ይገኛል። እ.አ.አ በ2023 ከኦማን፣ ካዛኪስታን እና ቬትናም ጋር አዲስ ግንኙነት ተፈጠረ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅድስት መንበር ዕውቅና ለተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ ቡድን አባላት ዓመታዊ “የዓለም ሁኔታ” ንግግራቸውን አቅርበዋል።

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በሚመለከት የተለያዩ መረጃዎችን የያዘ መግለጫ ሰኞ ይፋ አድርጓል።

በአጠቃላይ 184 ግዛቶች ከቅድስት መንበር ጋር ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው። ከእነዚህ ውስጥ 89 በሮም ተልእኮ አላቸው።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት እና የማልታ ሉዓላዊ ወታደራዊ ሥረዓት ከቅድስት መንበር ጋር ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው፣ እንዲሁም በሮም ውስጥ ተልእኮዎች አሏቸው።

የዓረብ ሊግ አገሮች፣ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር መቀመጫቸውን ሮም ያደረገ የቅድስት መንበር ጽ/ቤቶች አሏቸው።

እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም የታዩ እድገቶች

እ.ኤ.አ. የካቲት 23 ቀን 2023 ቅድስት መንበር ከኦማን ሱልጣኔት ጋር ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሰረተች።

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 19/2023 ቅድስት መንበር እና ካዛኪስታን፣ እ.አ.አ በመስከረም 24/2023 በቅድስት መንበር እና በካዛኪስታን ሪፐብሊክ መካከል የተደረሰው የጋራ ግንኙነት ስምምነት ፣ ለቤተክርስቲያን እና ለሚሲዮናዊያን ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ መስጠትን የሚመለከት ስምምነትን አፅድቀዋል ።

እ.አ.አ በሐምሌ 27/2023 ቅድስት መንበር እና ቬትናም የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ይህም መልካም እምርታ ያስገኘ እና በአገሪቱ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሚስዮናዊያን ጥበቃ እና ከለላ ማድረግን ያካተተ እንዲሁም እውቅናን የሚሰጥ ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል።  

11 January 2024, 14:29