ፈልግ

ከባርቶሎ ዲ ፍሬዲ ሥራዎች ውስጥ እ.አ.አ በ1385 የተሠራው 'የእረኞች ልደት እና አምልኮ' የሚባለው ሥራው - በቫቲካን ሙዚየም ከባርቶሎ ዲ ፍሬዲ ሥራዎች ውስጥ እ.አ.አ በ1385 የተሠራው 'የእረኞች ልደት እና አምልኮ' የሚባለው ሥራው - በቫቲካን ሙዚየም 

መላዕክቱ ስለ ሠላም ይዘምራሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እንዳሉት “የመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የውልደት ቀን ማክበር የእግዚአብሔርን ልጅ ሥጋ ለብሶ የመገለጥ ምስጢር በትህትና እና በደስታ ከማሳወቅ ጋር እኩል ነው” ብለዋል። ብጹእነታቸው እንዳስታውሱት፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ለብዙ መቶ ዘመናት ውበትን በመግለፅ ሲሰብኩ የነበሩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን አነሳስቷል። የገናን ሰሞን በድምቀት ለማክበር የቫቲካን ሙዚየሞች እና የቫቲካን ዜናዎች ከተለያዩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቃላቶች ጋር የታጀቡ የጳጳሳዊ ስብስቦች ውስጥ እጅግ ውብ የሆኑ ድንቅ የፈጠራ ስራዎችን ያቀርባሉ።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ከጥንት ጀምሮ የክርስቶስ ልደት ትዕይንቶች በመኖሪያ ቤቶች እና በሌሎች ቦታዎች እየተዘጋጁ ይቀርቡ ነበር። ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በ1223 የአሲሲው ቅዱስ ፍራንቺስኮ በጣሊያኗ ግሪቺዮ መንደር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ቀን የጌታን የመገለጥ ምስጢር ወክሎ ለመቅረብ ፍላጎት እንዳለው ገልፆ ነበር፥ በዚህም ጊዜ አዲስ እንደ ተወለደ ሕፃን በግርግም ውስጥ በመቀመጥ እና በበሬ እና በአህያ መካከል ባለው ገለባ ላይ በመተኛት ያጋጠመውን መከራ በራሱ ሥጋ አይን ተመልክቷል” (የፍራንቺስካዊያን ምንጮች 30, 468)

እንዲሁም በሚቀጥሉት መቶ ዘመናት በማይታመን ሙልአት እና ጨዋነት ውስጥ ሆነው መፍትሄ በመፈለግ የገናን ክብረ በዓል ወይም ትዕይንት ወክለው ለማሳየት የጣሩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተፅዕኖ ከፍተኛ ነበር። በ1385 አካባቢ የባርቶሎ ዲ ፍሬዲ (እ.አ.አ. 1352 – 1410 ሲዬና ከተማ ውስጥ የኖረ ታላቅ ከያኒ ነበር) ወርክሾፕ ውስጥ የተሰራው ሥራም በተደጋጋሚም ባይሆን የእረኞችን የምስራች ብስራት ትዕይንት ወይም የእረኞችን አምልኮ ክፍል የሚያካትተውን ሥራውን አሳይቷል።

“ሰውን የፈጠረው የእግዚአብሔር ልጅ፣ የጨቅላ ህፃኑ አልጋ አጠገብ፥ ወደዚህ ሥፍራ የሚመጣ ሰው ሁሉ ከፍ ባለ እና በቅን ኅሊና እንደሚያንጸባርቅ እና በገናናው መግቢያ በር በኩል ስለ ሕይወት ስጦታ ጥብቅ መለያ እንደሚጠየቅ ነው። በመጨረሻም የማይሻር ምህረት ወይም ቅጣት ይኖረዋል። ስለዚህም ከዚህ ተጠያቂነት ግንዛቤ ለማግኘት፥ የክርስቲያኖች እና የሁሉም ሰዎች ተሳትፎ የሚለካው በዚህች ሌሊት በምንዘክረው ታላቁ ምሥጢር ነው። ከዚህ ሥፍራ ተስፋ ይኖረናል፣ ከእግዚአብሔር ቃል ብርሃን አለ፣ ለሕዝቦች ጥቅም የሚውሉ የሰው ልጅ ሥልጣኔዎች ወደ ብሩህ ብርሃን ሊያመጣቸው የሚችለውን ብልጭታ ሊቀበሉ ይችላሉ። በህፃኑ ኢየሱስ አልጋ ዙሪያ መላእክቱ ሰላምን ዘምረዋል። በሰማያዊው መልዕክት ያመኑና ያከበሩትም ክብርና ደስታን አግኝተዋል። ስለዚህ ትናንት ነበረ፥ ወደ ፊት በዘመናት ውስጥም ይሆናል። የኢየሱስ ታሪክ ዘላለማዊ ነው። እሱን የተረዳ እና ከሱም ውስጥ ጸጋን፣ ጥንካሬን እና በረከትን ፈልጎ የሚያገኝ እሱ የተባረከ ነው”
                                                                                                        (ዮሐንስ XXIIII - ታህሳስ 24 ቀን 1962)
 

27 December 2023, 14:16