ፈልግ

የቅድስት መንበር ፍርድ ቤት ችሎት የቅድስት መንበር ፍርድ ቤት ችሎት   ርዕሰ አንቀጽ

ቫቲካን ውስጥ የሁሉንም መብት በማረጋገጥ የተካሄደ የፍርድ ሂደት

የቅድስት መንበር የገንዘብ ኢንቨስትመንት፥ በሎንዶን ከተማ ከሚገኝ የሕንጻ ግዢ ጋር የቫቲካን ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ አስተያየቶች ቀርበዋል። በቫቲካን ሙዚዬም አዳራሽ ውስጥ ቅዳሜ ታኅሳስ 6/2016 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ የተጠናቀቀው የፍርድ ሂደቱ በቫቲካን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ትልቅ ትርጉም ያለው እና ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ፈተና ቢሆንም፥ “የክፍለ ዘመናችን የፍርድ ሂደት” ብሎ መጥራቱ ትክክል አይሆንም።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቫቲካን ከተማ አስተዳደር የላተራን ውል ስምምነትን መሠረት በማድረግ እንደ ጎሮጎሮሳውያኑ ከ1929 ዓ. ም. ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ይታወቃል። በቅድስት መንበር የፋይናንስ አስተዳደር በማስመልከት የተደረገው የፍርድ አስጠጣጥ ሂደት፥ በሁለቱንም መንገዶች ማለትም ወደ ሕዝብ ዘንድ የቀረበውን ረጅም እና ከባድ ፈተናን ገሃድ ለማድረግ የገንዘብ አስተዳደሮች እና አንዳንድ የውጭ ተዋናዮች ለቤተ ክርስቲያኗ ተገቢውን ግብዓት ለማግኘት የተሳተፉበት የፍርድ ሂደቶች ናቸው።

በተከሳሾቹ ላይ የቀረቡት ክሶች እና በምርመራው ወቅት የቀረቡት ጥያቄዎች ለመደበኛው የፍርድ ሂደት ግልፅ እና አስፈላጊ መንገድ ከፍተዋል። የቫቲካን የፋይናንስ አስተዳደር ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የምርመራ እና አንዳንድ ጊዜ የፍርድ ቤት ጋዜጠኝነት ላይ ትኩረት ሲሰጥ ቆይቷል። የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በቆራጥነት የጀመሩትን የግልጽነት መንገድ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማሻሻያዎችን አድርገውበት በጽናት ቀጥሏል።

በሌሎች አገራት ዳኞች በኩል ሳይሆን በቅድስት መንበር የውስጥ ጽሕፈት ቤቶች፥ ለፍትህ አካላት ሪፖርት በሚያደረጉባቸው ሕገወጥ ድርጊቶች ላይ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፍትሃዊ የሆነ ተቋማዊ አካሄድን እንዲከተል አድርገዋል። በአንዳንድ ሰዎች በኩል ከቀረቡት ገለጻዎች ባሻገር፣ በለንደን ስሎን ጎዳና የሚገኝ ሕንፃ ኢንቨስትመንት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተደረገው የፍርድ ሂደት ፍትሃዊ የነበረ ሲሆን፣ ይህ የፍርድ ሂደት ሙሉ በሙሉ የተከሳሾችን መብት በማክበር በችሎት የተካሄደ ነበር። ይህን ማስመስከር የሚቻለው በተሰሙት ችሎቶች፣ በሠነዶች እና በምስክሮች ብዛት ብቻ ሳይሆን በመጀመሪያ መሠረታዊ የሚመስሉ ምስክሮች በኋላ ላይ በፍርድ ቤቱ ክርክር እና የሠነድ ማስረጃዎች ምክንያት ፋይዳ የሌላቸው መሆናቸው ተመልክቷል።

የዚህ ችሎት ውጤት እንደሚነግረን፥ የችሎቱ ዳኞች በነጻነት ትክክለኛ በሆነ መንገድ በሠነድ ማስረጃ እና በምስክርነት ቃሎች እንጂ በቅድመ ፅንሰ-ሀሳቦች አይደለም። ለክርክሩም ሰፊ ቦታ ሰጥተዋል። ስለሆነም የፍርድ ሂደቱ የተከሳሾቹን መብቶች ሁሉ በማክበር የተከራካሪዎቻቸውን አቤቱታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ደንቦቹ ለዓቃቤ ሕጉ ምቹነት ያለውን በመገድ በማዘጋጀት ለብይን ደርሷል። ለምሳሌ ፍርድ ቤቱ በቫቲካን የክብር ዘብ በሆኑት በአቶ ጃንሉዊጂ ቶርዚ ባደረገው ምርመራ ወቅት የተሰጡት መግለጫዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው በመቁጠር የሰጠው ውሳኔ ይህን ያሳያል። መግለጫዎቹ በሌሎች ተከሳሾች ላይ የቀረቡትን ውንጀላዎች ያካተተ ቢሆንም፥ አቶ ጃንሉዊጂ በፍርድ ቤት ችሎት በአካል ቀርበው መድገም እና ማጣራት ባይችሉም ተቀባይነት የላቸውም ተብሎ አይታሰብም።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው የካቲት ወር በፍትህ ዘመን ምሥረታ በዓል ላይ እንደተናገሩት፥ አንድ ሰው ግልጽ መሆን እንዳለበት፥ የማይታመኑ ምክንያቶችን ከማቅረብ መራቅ እንዳለበት እና ችግሩ ክስ ማቅረብ ሳይሆን የመነሻ እውነታ እና ባህሪ መሆን እንደሚገባ ተናረዋል። ግልጽነትን በተመለከተ የውጭ ተቆጣጣሪዎች በገንዘብ አያያዝ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደረግጉ እና ክፍተቶች አለመኖራቸውን በመገንዘባቸው የቤተ ክርስቲያን ንብረቶችን ከማስተዳደር ጋር ተመሳሳይነት ያለውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።

የፍርድ ሂደቱ እንደሚያሳየው ቅድስት መንበር እና የቫቲካን ከተማ አስተዳደር በደሎችን ወይም የሥ-ነምግባር ጉድለቶችን ለመለየት አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰዳቸው እና የእያንዳንዱን ሰው መብት በማክበር እና ንፁህነቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የአሠራር ደንቦችን በመከተል ያለ አቋራጭ መንገድ ተካሂዷል።

18 December 2023, 15:55