ፈልግ

2023.09.15 Palazzo del Governatorato

ቫቲካን “በስነ-ምዕዳር ለውጥ 2023” የተሰኘ ቀጣይነት ያለው ተንቀሳቃሽ ፕሮግራም ጀመረች!

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ ላውዳቶ ሲ (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) እና ላውዳቴ ዴውም (እግዚአብሔርን አወድሱት) በተሰኙት ሁለት ጳጳሳዊ መልእክት ማዕቀፍ ውስጥ ስነ-ምዕዳርን እና ለአከባቢያችን ጥበቃ ማድረግን በተመለከተ ለአከባቢ ብክለት ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ አስተዋጾ እያበረከተ የሚገኘውን የካርቦንዳውክሳይድ ልቀትን ለመቀነስ ተከታታይ ኃይል ቆጣቢ ውጥኖች እና ስልቶች መጀመሩን የቫቲካን ከተማ ጠቅላይ ግዛት ያሳወቀ ሲሆን ይህም ውጥን የሚከናወነው የቮልስዋገን ቡድን ከተሰኘው ተቋም ጋር እንደ ሆነም የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቫቲካን ከተማ አስተዳደር አካባቢን ለመጠበቅ እና ኃይል ቆጣቢ ስልቶችን ለማቅረብ በሥነ-ምህዳር ፖሊሲዎች ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት ለብዙ ዓመታት ያስቆጠረ ሥራ ስታከናውን ቆይታለች።

በላቲን ቋንቋ ‘ላውዳቶ ሲ' (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) እና አሁንም በላቲን ቋንቋ ‘ላውዳቴ ዴም’ (እግዚአብሔርን አወድሱት) የተሰኙ ሁለት ጳጳሳዊ መልእክቶች መርሆችን በመተግበር፣ በዓለማችን ላይ ዘላቂነት ያለው ፕሮጄክቶችን ለመከታተል ከመጀመሪያዎቹ ግዛቶች መካከል ቫቲካን አንዷ ስትሆን ይህም አዳዲስ መፍትሄዎችን በመፈለግ ለሥራው ጥበቃ በሚያደርጉበት ጊዜ የሥራውን መንገድ ለመለወጥ የሚረዳ አስተማማኝ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሰው ልጅ እንቅስቃሴ በአካባቢው ላይ የሚያደርሰውን ተፅእኖ በተጨባጭ የሚቀንሱ ፕሮጀክቶችን በመተግበር 'የጋራ ቤታችን' የሆነችውን ምድራችንን ለመከባበክብ ያለመ ፕሮጄክት ነው።

የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት እና የፓሪሱ ስምምነቶች የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲዎች እና የቅዱስ አባታችን ምልክቶች እና ምክሮች መካከል ድልድይ ናቸው ።

ቫቲካን የተፈጥሮ ሀብትን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ በመጠቀም፣ የኃይል ቆጣቢ ፕሮጀክቶችን በመተግበር፣የቴክኖሎጂ ሁኔታዎችን በማሻሻል፣ ዘላቂ ተንቀሳቃሽነት፣ የማጓጓዣ፣ ቆሻሻ አወጋገድ እና ልማትን የሚያመርቱ ንፁህ ወይም አማራጭ የኃይል ምርቶችን በማምረት የአየር ንብረት ለውጥ ለመግታት እና ይህንንም ግብ ለማሳካት ቁርጠኛ እንደ ሆናችን የተገለጸ ሲሆን ተጨባጭ የወደፊት የደን መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በተከታታይ ገቢራዊ እንደሚሆኑም ተገልጿል።

በቫቲካን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች

በቴክኖሎጂ ተቋማት ታዳሽ ሃይሎችን በመጠቀም መዋለ ነዋይ ፈሰስ ማድረግን፣ በአንድ አካባቢ የሚመረተውን ልቀትን ማካካስ እና በሌላ ላይ መቀነስ እና ከሁሉም በላይ የኤሌክትሪክ እና የድብልቅ ቴክኖሎጂዎችን እንቅስቃሴ ማስፋፋት ይጠይቃል። በዚ ምክንያት ቫቲካን 'Ecological Conversion 2030' የተባለ ቀጣይነት ያለው የእንቅስቃሴ ልማት ፕሮግራም ጀምራለች።

ይህንን ዓላማ ለማሳካት በቫቲካን ሥር የሚተዳደሩ መኪኖች ቀስ በቀስ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መተካት፤ እ.አ.አ በ 2030 በቫቲካን ሥር የሚተዳደሩ መኪኖች ሁሉ ከካርበን ልቀት ነፃ የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ብቻ እንደሚኖሯት ተገልጿል።  

ዘላቂ እና ስልታዊ የታጋሽ ኃይል አጠቃቀም

እ.ኤ.አ. በ 2050 ከካርቦን-ገለልተኛ ኩባንያ ለመሆን እና የተሽከርካሪዎቹን የካርበን አሻራ በ 30% በ 2030 ለመቀነስ ዓላማ ያለው የቮልስዋገን ግሩፕ የቫቲካን መኪኖችን ከቮልስዋገን እና ከስኮዳ ዓርማ ተሽከርካሪዎች ጋር ለማደስ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ስትራቴጂያዊ አጋር ነው ። የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የኪራይ ቀመር እንደ ተዘጋጀም ተገልጿል።

በዛሬው እለት ማለትም በኅዳር 06/2016 ዓ.ም ከቮልስዋገን ግሩፕ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል ይህም የዘላቂው እንቅስቃሴ ልማት መርሃ ግብር አካል ሲሆን ይህም የሰው ልጅ እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተፅእኖ በተጨባጭ ለመቀነስ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ነው።

17 November 2023, 16:06