ፈልግ

የጋራ ቤታችን እንክብካቤ፡ ዘላቂነትን እና ሰላምን የሚያበረታታ ኢኮኖሚ መገንባት በሚል አርዕስት በቫቲካን የተካሄደ ስብሰባን የምያሳይ ፎቶ የጋራ ቤታችን እንክብካቤ፡ ዘላቂነትን እና ሰላምን የሚያበረታታ ኢኮኖሚ መገንባት በሚል አርዕስት በቫቲካን የተካሄደ ስብሰባን የምያሳይ ፎቶ  

ቫቲካን የጋራ ቤታችንን እንከባከብ በሚል አርዕስት ላይ የተካሄደ ስብሰባ አስተናገደች!

ጳጳሳዊ የሳይንስ አካዳሚ በቫቲካን ዋና መሥሪያ ቤት ካሲና ፒዮ አራተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ማክሰኞ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም የቫቲካን የኮሙንኬሽን ጽሕፈት ቤት ባዘጋጀው እና የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጽሕፈት ቤት የገነዘብ ድጋፍ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

አካባቢን የምንከባከብ፣ ሰላምን የምያጠናክር እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚተጉ የእምነት፣ የንግድ፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የመንግሥት ተወካዮች አርባ የሚጠጉ መሪዎች “የጋራ ቤታችን ግንባታን እንከባከባለን እና ዘላቂነትን እና ሰላምን የሚያበረታታ ኢኮኖሚ መግባባት” በሚል መሪ ቃል በጥቅምት 27/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ማለዳ ዝግጅት በጳጳሳዊ የሳይንስ አካዳሚ የተስተናገደ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ክስተት የአየር ንብረት ቀውስን "ለውጦች" አሳይቷል፣ እሱም በዓለም ታዋቂ የሆኑ የፎቶግራፍ አንሺዎች ስራን ያካተተ ነበር፣ ከአዚዚው ቅዱስ ፍራንችስኮች ቃላት ጋር በሊያ እና ማሪያና ቤልትራሚ በተባሉ ሰዎች መሪነት ነበር የፎቶ ኤግዝቢሽን የተካሄደው። ወይዘሮ ሊያ ቤልትራሚ ለዝግጅቱ በቦታው ተገኝታለች፣ እናም ይህ ኤግዚቢሽን የተሻለ አለም ለመፍጠር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በተፈጠሩት ሰፊው “ለውጥ ለመፍጠር ስሜቶች” ከሌሎች መካከል እንዴት አንዱ እንደሆነ ገልጻለች።

ዶ / ር ፓኦሎ ሩፊኒ የቫቲካን የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ፕሬዝዳንት የመጀመሪያውን ንግግር አቅርበዋል። እርሳቸውም በሁለቱ ክብ ጠረጴዛ ዙሪያ የተካሄደው  የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽኑ “የድርጊት ጥሪ…ዘላቂ ልማትን በሚያበረታታ ኢኮኖሚ ውስጥ ለመሳተፍ የሚረዳ ነው” በማለት የሰውን ልጅ እና ፍጥረትን በማዕከላዊነት የሚጠብቅ ተግባር ነው ሲሉ ገልጿል። ዶ/ር ሩፊኒ በተጨማሪም “የጥሩ እና እውነተኛ የግንኙነት መረብ”፣ “የመጋራት ሥነ-ምህዳር… ሥነ-ምግባርን ወደፊት ለማስቀጠል መሥራት የእኛ ፋንታ ነው” ብለዋል፣ “መረጃው እንደ ትምህርት ያለውን ሐሳብ እንደገና ማግኘት ነው። የህዝብ ጥቅም ነውና የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን መከላከል እና መጠበቅ አለብን” ሲሉ የተናገሩት  ዶ/ር ሩፊኒ "የእኛ የዴሞክራሲ የወደፊት እጣ ፈንታ በእሱ ላይ የተመሰረተ ነው" በማለት ደምድመዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሰን የዝግጅቱ ተሳታፊዎችን በጳጳሳዊ የሳይንስ አካዳሚ ስም ተቀብለዋል። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ ካርዲናል እንዳብራሩት፣ ሳይንስ እና እምነት እርስ በእርሳቸው እንደማይጋጩ ቤተክርስቲያን ተገንዝባለች፣ እንድሁም ቤተክርስቲያን ከሳይንስ በንቃት የምትማርበት አካዳሚ መመስረቱን ጠቅሰዋል። ካርዲናል አክለውም አካዳሚው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀልበስ ንቁ ተሳትፎን ለማበረታታት በእነርሱ ማለትም በሳይንቲስቶች እንዲሁም ከንግድ መሪዎች ጋር ንቁ ውይይት እየተደረገ ነው ሲሉ ተናግሯል።

ክፍት የሆነው ውይይት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻው ንግግር ያደረጉት ጄኒፈር ዮርዳኖስ-ሳይፊ (ዋና ሥራ አስፈፃሚ - ዘላቂ የገበያ ተነሳሽነት፣ በግርማዊ ንጉሡ ቻርልስ ሳልሳዊ የዌልስ ልዑል በነበሩበት ጊዜ የተጀመረው) የዛሬውን ዓለም አቀፍ ቀውሶች ለመጋፈጥ ስላለው የሞራል ድፍረት ተናግራለች።

ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄኔፈር በተባበሩት መንግስታት ዘላቂ ግቦች እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ ‘Laudato Si’ (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት ላይ በመመስረት ሁለቱም በ 2015 ይፋ የሆነውና  እምነትን መሰረት ያደረገው በግሉ ክፍል መሪዎች መካከል የውይይት መድረክ በሚሰጡበት የክብ ጠረጴዛውን አወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት ከተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል፡ ጥበብና ተግባቦት ግንዛቤን በማሳደግና በውጤታማ ለውጥ ላይ ያለው ሚና፣ ቋንቋን ከዋልታ ረገጥነት የመራቅ አስፈላጊነት፣ ተረት ተረት መልእክቶችን ለማስተላለፍ እንደ ሃይለኛ የጥበብ ዘዴ፣ ካለፉት የባህል ፈረቃዎች መማር እና የለውጡ አስፈላጊነት ይገኙበታል። ከላይ ወደታች ሳይሆን ከታች ወደ ላይ ይምጡ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

ሁለተኛው ውይይት በኢኮኖሚው እና በቢዝነስ ሴክተሩ መሪዎች ተመርቷል። እዚህ የተብራሩት ርዕሰ ጉዳዮች በአየር ንብረት ለውጥ ውጤቶች ምክንያት መንግስታት የሚደርሱትን የገንዘብ ኪሳራ ለማሳየት በመረጃ አስፈላጊነት ላይ ያተኮሩ ናቸው ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአየር ንብረት ለውጥን "የጋራ ቤታችንን" በመጠበቅ ላይ በማተኮር በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ዋልታ ረገጥ ያልሆኑ ቋንቋዎችን ሰጥተዋል፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ብዙ የሚያጡ የዓለማችን ኢንሹራንስ የሌላቸው የብዙዎቹ ህዝቦች ችግር፣ አንድ የፋይናንስ ተቋም ዝቅተኛ የካርቦን ሽግግር ኢንቨስት በማድረግ ዘላቂ ፋይናንስ ውስጥ እንዴት እንደሚሳተፍ እና የንግድ ደንበኞቹን ወደዚያ አቅጣጫ እንዲሄዱ የሚያበረታታ ተጨባጭ ምሳሌ፣ የታጋሽ ኃይል ሽግግር፣ ከተመሳሳይ አሃዛዊው በተለየ፣ ሁሉም ሰው - ግለሰቦች እና ድርጅቶች በየደረጃው - በአንድ አቅጣጫ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን እንድረዱ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ የተናገሩ ሲሆን በንግዱ ዓለም ውስጥ አዳዲስ የፅንሰ-ሀሳባዊ ሞዴሎች አስፈላጊነት ዘላቂነትን ለማግኘት ለሚያስፈልጉ ለውጦች አስተዋፅዖ ለማድረግ የምያስችሉ ግባቶችን ማዘጋጀት እንደ ሚገባ ጨምረው ገልጿል።

ዝግጅቱ የተጠናቀቀው በቅድስት መንበር የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲስተር አሌሳንድራ ስሜሪሊ ባደረጉት ንግግር ሲሆን እንደ ቫቲካን ያሉ ትንንሽ አካላት በ COP28 እና ሌሎች ጉዳዮችን በመተሳሰር፣ በጋራ በመስራት እና ጥረቶችን በመቀላቀል ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ አሳስበዋል። አክለውም “አንድ ነገር ካደረግን ፣ ምናልባት የሆነ ነገር ይለወጥ ይሆናል” ብለዋል ።

08 November 2023, 11:46