ፈልግ

የሮም ከተማ ገጽታ የሮም ከተማ ገጽታ 

የአዲሶቹ ሰማዕታት የምርምር ምክር ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሥራውን ጀመረ

በቅድስት መንበር የቅድስና ጉዳዮች ጥናት ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2025 ዓ. ም. የሚከበረውን የኢዮቤልዩ ዓመት ከግምት ውስጥ በማስገባት፥ የሞታቸውን እና የአገልግሎት ሁኔታቸውን ቤተ ክርስቲያን የወቃቸው ከ550 የሚበልጡ ሰማዕታትን ለመዘርዘር ስብሰባ ማድረጉ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአዲሶቹ ሰማዕታት የእምነት ምስክሮች ምክር ቤት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2025 ዓ. ም. የሚከበረውን የኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ፥ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ተልዕኮውን ተግባራዊ ለማድረግ ሐሙስ ጥቅምት 29/2016 ዓ. ም. በጳጳሳዊ ምክር ቤቱ ስብሰባ ማካሄዱ ታውቋል።

የቅድስት መንበር መግለጫ ጽ/ቤት እንዳመለከተው፥ ጉዳት በደረሰባቸው ክርስቲያኖች ላይ የተደረገው ጥናት እና የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ምእመናን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የገዳማውያን እና ገዳማውያት ጉዳይ፥ “ፊደስ” በተሰኘ የቤተ ክርስቲያን የዜና ወኪል እና በሌሎች ኤጀንሲዎች የቀረቡ መረጃዎች ከመታየታቸው በተጨማሪ፥ አዲሱ ጥናት በብጹዓን ጳጳሳት፣ በገዳማት እና የእነዚህን ክርስቲያኖች የመታሰቢያ ታሪክ ጠብቀው ባቆዩ ሰዎች በመታገዝ ምርምር እንደሚደረግባቸው ታውቋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ሊካሄድ የታቀደው የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓቱ፥ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2000 ዓ. ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ ባለው ጊዜ ውስጥ በወንጌል ምስክርነት ወቅት ሕይወታቸውን ያጡ ወይም በተለያዩ መንገዶች የተሰው ክርስቲያኖችን እንደሚመለከት ታውቋል።

እስካሁን ድረስ ከ550 በላይ የወንጌል መስካሪዎች ቤተ ክርስቲያንን እና የእግዚአብሔርን ሕዝቦች በማገልገል ላይ እንዳሉ የተገደሉ መሆናቸው ሲታወቅ፥ የጳጳሳዊ ምክር ቤቱን ሥራ የሚያግዙ አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎች የሚቀርብበት ድረ-ገጽ መዘጋጀቱም ታውቋል።

ቁርጠኝነት እና የሥራ ዘዴ

ምርምሮችን ለማካሄድ የተወሰዱ የቁርጠኝነት እና የአሰራር ዘዴዎች የተዘረዘሩ ሲሆን፥ በተለይ ደማቸው የፈሰሰባቸው እና የሕይወት መስዋዕትነት የተከፈለባቸው አህጉራዊ፣ ክልላዊ እና ብሔራዊ ሁኔታዎችን መልሶ ለመገንባት ከኮሚሽኑ አባላት ውጪ የሚደረጉ ግንኙነቶችም ታሳቢ ሆነዋል። በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በእስያ እና ብዙ በምሥራቅ ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ ምእመናን አስተዋጽዖ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ሰማዕትነት ያለው ጠቀሜታ ሰፋ ባለ መልኩ እና ሌሎች የእምነት ተቋማት የሚያቀርቡት ምሥክርነት ምን ያህል እንደሆነ ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑም ተስተውሏል።በቅድስት መንበር የቅድስና ጉዳዮች ጥናት ጳጳሳዊ ምክር ቤት፥ የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋቢዮ ፋቤኔ በተገኙበት፥ ለምክር ቤቱ ባሳየው አስፈላጊ መንገዶች ማለትም የሰው ሃይል እና የቴክኒክ እገዛን በማቅረብ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።

የተስፋ ብርሃን

የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝደንት ከሆኑት ፕሮፌሰር አንድሪያ ሪካርዲ ጋር በመሆን ለወደፊት ምርምሮች ሃሳቦችን በማቅረብ የቀድሞ ምርምሮችን በድጋሚ ተመልክቶ ማሻሻያዎች መደረጋቸው ታውቋል። “በመረዳዳት መንፈስ፥ ሕይወታቸውን እና ሞታቸውን ለአቅመ ደካሞች ፍቅር ሲሉ፣ ሰላምን በመፈለግ እና በሕመም መካከል ወንጌል ከተመሰከረባቸው በጎ ነገሮች ጋር እምነትን በማዛመድ በርካታ ክፉ ንድፎች ውስጥ በመግባት ምስክርነቶችን ለማየት ዝግጅት ተደርጓል” ሲል መግለጫው አስታውቋል።     “ምስክርነቶቹ የተስፋ ብርሃን ያለባቸው ትሑት እና ለሕይወት መልካም ነገርን፣ ለሰው ልጅ ቤተሰብዓዊ አንድነት እና መሣሪያን ያልታጠቀ የክርስቲያኖች ጥንካሬ የሚጠሩ ናቸው" ሲል መግለጫው አክሏል።

 

14 November 2023, 16:32