ፈልግ

አብረን መመላለስ እና መንፈስ ቅዱስን ማዳመጥ

የሲኖዶስ ጉባኤውን በሲኖዶስ ላይ በማስተዋወቅ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና ዋና አስተዳዳሪ የሲኖዶሱን ሂደት መንፈስ በማጉላት ምእመናን መንፈስ ቅዱስን እንዲያዳምጡ በሦስተኛው ሺህ ዓመት ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ፈቃድ እንዲረዱ ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 16ኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደርጉትን የመክፈቻ ንግግር ተከትሎ በመቀጠል የሲኖዶሱ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ንግግር አድርገዋል። በጳጳሱ በ2021 የተጀመረውን የሶስት ዓመት ሲኖዶስ ሂደት ግቦችን፣ መንፈስ እና ዘዴን በድጋሚ የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆሌሪች ነበሩ።

ሲኖዶሳዊ ቤተክርስቲያን የምታዳምጥ ቤተክርስቲያን ናት

የመሰናዶ ደረጃዎችን በመገምገም የሀገረ ስብከቱን፣ የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች - የምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶስ እና የአህጉራዊ ደረጃዎችን ጨምሮ - ብፁዕ ካርዲናል ግሬች ጠቁመው፣ ምንም እንኳን የመነሻ ጥርጣሬዎች እና አንዳንድ ችግሮች እና አለመግባባቶች ቢኖሩም ይህን ጉዞ ቤተክርስቲያን “በብርታት እንድታድግ” ረድቷል፣ “በአንድነት መመላለስ” በሲኖዶሳዊ ልምድ” ማስተማር ይገባል ብሏል።

"ቤተክርስትያን እራሷ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች እና ለአስቸኳይ ተግዳሮት በጥብቅ መናገር የስነ-መለኮት ወይም የቤተክርስቲያን ተፈጥሮ አይደለም፣ ነገር ግን በዚህ በታሪክ ውስጥ ቤተክርስቲያን እንዴት ለእያንዳንዱ ወንድ እና ሴት የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት እና መሳሪያ ትሆናለች" የሚለው ዋና ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብሏል።

“ዛሬ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጳጳሳት ሲኖዶስ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር “የሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ሰሚ ቤተክርስቲያን ናት” ብለው ያቀረቡት የቤተክርስቲያን ራዕይ ምን ያህል እውነት መሆኑን እንመሰክራለን ብሏል።

ጉባኤው ለቤተክርስቲያን ጠንካራ የሲኖዶስ ምልክት መሆን አለበት።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በእግዚአብሔር ሕዝብ እና በመጋቢዎቻቸው የኖሩት የሲኖዶሳዊ ልምድ፣ ጉባኤው “የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት በትውፊት ብርሃን ለቤተክርስቲያን ጠንካራ ምልክት እንዲሆን ጥሪውን ያቀርባል። የእግዚአብሔርን የዛሬውን ፈቃድ ለመረዳት፣ እና “ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድ እና አንድ ብቻ ለማሳየት ጠንክረን መሥራት ይኖርብናል ብሏል።

“ከየትኛውም ቦታ ይልቅ እዚህ ላይ ዮሐንስ ክሪሶስተም የሚናገረው ግልጽ መሆን አለበት፡- ‘ቤተ ክርስቲያን እና ሲኖዶስ አንድ ናቸው’” ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ግሬች፣ የጳጳሳት ሲኖዶስ በሮም ኤጲስ ቆጶስ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ዙሪያ የኤጲስ ቆጶስነት አንድነት መግለጹን አስታውሰዋል።

የሚታይ የኅብረት ምልክት

የሲኖዶሱ ዋና ጸሃፊ በመቀጠል ጉባኤው "የሚታይ ምልክት" የህብረት ምልክት እንዲሆን እና ለቤተክርስቲያን እና ለአለም አገልግሎት መሳሪያ እንዲሆን መጠራቱን አጽንኦት ሰጥተው ገልጿል።

ብፁዕ ካርዲናል ግሬች እ.አ.አ. በጥቅምት 17 ቀን 2015 በሲኖዶስ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተናገሩትን ቃል በመጥቀስ "በዓለም አቀፍ ደረጃ - በቤተክርስቲያን 'አብረው ስለመሄድ' እራሷን ለመጠየቅ" ጊዜ ያገኘችበት ወቅት ነው ብሏል። እርግጠኛነት 'የሲኖዶሳዊነት መንገድ እግዚአብሔር ከሦስተኛው ሺህ ዓመት ቤተ ክርስቲያን የሚጠብቀው መንገድ ነው'' ሲሉ አክለው ተናግሯል።

ለመንፈስ ቅዱስ መመሪያ ክፍት መሆን

ብፁዕ ካርዲናል ሆለሪች በጉባኤው ላይ ስላለው የሲኖዶስ ሂደትና መንፈስ የበለጠ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሲኖዶሱ ዋና ተዋናይ “ክርስቶስን በመካከላችን እንዲገኝ የሚያደርግ” መንፈስ ቅዱስ እንደሆነና “ለተቀበልነው ጥሪ ምላሽ የምንሰጥበት ሙሉ በሙሉ ለመንፈስ መመሪያ ክፍት በሆነ ልብ ብቻ እንደሆነ ለሲኖዶሱ አባላት አስታውሰዋል።

በሲኖዶሳዊ አስተምህሮ ውስጥ ተልእኮ ቁልፍ ሚና እንዳለው ያስታወሱት ዋና አስተዳዳሪ፥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልእኮ እውን ለማድረግ የሲኖዶሱ አባላት ከጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳርሽ ባሻገር  "ራዕያቸውን ለማስፋት" ጥሪ ቀርቦላቸዋል። በብዙ ክፉ ነገሮች የተጠቃ፡ ከአየር ንብረት ለውጥ እስከ ፍልሰት፣ ጦርነቶች፣ ከፍተኛ ዋልታ ረገጥነት እና ከፍተኛ የሆነ የፍጆታ አኗኗር ዘይቤን የመሳሰሉ ድርጊቶች በአሁን ዓለማችን ውስጥ እየተሰተዋሉ መሆናቸውን ገልጿል።

“የሲኖዶሳዊ ሰዋሰው” እና ማስተዋልን መማር

በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲኖዶሳዊ እንድትሆን እና “የሲኖዶሳዊውን ሰዋሰው” እንድትማር እየተጠራች ነው። "ልክ የቋንቋዎቻችን ሰዋሰው ሲያድጉ እንደሚለዋወጡ ሁሉ የሲኖዶሳዊ ሰዋሰውም እንዲሁ ነው" ብለዋል ካርዲናል ሆለሪች። "ስለዚህ የዘመናችን ምልክቶችን ማንበብ ለዘመናችን የሲኖዶሳዊ ትምህርት ሰዋሰው እንድናውቅ ሊረዳን ይገባል" "የካቶሊክ መሠረታዊ ደንቦችን" ሳንቀይር በማለት ተናግሯል።

ብፁዕ ካርዲናል ሆለሪች በድጋሚ የሲኖዶሱን አባላት በማሳሰብ ሥራቸው በአብላጫ መርህ የሚመራ የፓርላማ ክርክር ሳይሆን “የጋራ የማስተዋል ሥራ ነው” በማለት አብረው ሳይጸልዩ ሊሠሩ አይችሉም ብሏል።

“በእውነተኛ ማስተዋል፣ መንፈስ ቅዱስ ሀ እና ለ በመተው አእምሯችንን እና ልባችንን ወደ አዲስ ቦታ ይከፍታል!” ብሏል።

የንግግር ዘዴ በመንፈስ ቅዱስ

ከሥራው አደረጃጀት ጋር በተያያዘ - እንደ ልማዱ የጠቅላላ ጉባኤዎች እና አነስተኛ የሥራ ቡድኖች በትናንሽ የጥረቤዛ ዙሪያ የተሰበሰቡ ተሳታፊዎች ሲኖዶሳዊነት፣ ሕብረት፣ ተልዕኮ እና ተሳትፎን ከማዘጋጀት በፊት በአራቱም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ። የተከናወነው ሥራ ውህደት – ካርዲናል ሆሌሪች ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲኖዶሳዊ ጉዞ ቀጣይነት ባለው መልኩ በትናንሽ የጥረቤዛ ዙሪያ የተሰበሰቡ ተሳታፊዎች ውይይቶች “በመንፈስ መነጋገር” የሚለውን ዘዴ እንደሚከተሉ አስታውሰዋል።

የዚህ ዘዴ አንዱ ጠንካራ ጎን “የሁሉም ሰው አመለካከት እንዲገለጽ የሚፈቅድ፣ ልዩነቶችን ችላ ሳይል ተነባቢነትን የሚያጎለብት ነገር ግን ከሁሉም በላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ውዥንብርና ጭቅጭቅ” እና “በቡድን ሳይከፋፈሉ ወይም ሳይከፋፈሉ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ እንደሆነ አብራርተዋል። “በዚህ መንገድ፣” ካርዲናል ሆለሪች፣ “እርስ በርስ ከመደማመጥ ወደ መንፈስን ከመስማት ምናብን ያሳድጋል” ብለዋል።

ለቀጣዩ የሲኖዶስ ጉባኤ ፍኖተ ካርታ

ዋና አስተዳዳሪው ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ የሲኖዶስ ሥራ በሚቀጥለው ዓመት በጥቅምት ወር ለሚካሄደው ሁለተኛው የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ "የፍኖተ ካርታ" ለማዘጋጀት እንደሚፈቅድ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። “በሐሳብ ደረጃ፣ ይህ ፍኖተ ካርታ በመካከላችን እና ከሁሉም በላይ በእግዚአብሔር ሕዝብ ውስጥ መግባባት እንደተደረሰ የሚሰማንን የሚጠቁም መሆን አለበት፣ ይህም ለመንፈስ ድምፅ ምላሽ ለመስጠት የሚቻለውን እርምጃዎችን አስቀምጧል። ነገር ግን ጠለቅ ያለ ማሰላሰል የት እንደሚያስፈልግ እና ያንን የማሰላሰል ሂደት ምን ሊረዳ እንደሚችል መግለጽ አለበት ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

05 October 2023, 11:33