ፈልግ

የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት  (@VaticanMedia)

የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ ተካፋዮች የሁለተኛ ቀን ሱባኤያቸውን በመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ጀምረዋል

16ኛውን የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤን የሚካፈሉት ብጹዓን ጳጳሳት፣ ካኅናት፣ ገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የአብያተ ክርስቲያናት ልዩ ተወካዮች እና ምዕመናን የሁለተኛ ቀን ሱባኤያቸውን በሮም ባቀረቡት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ጀምረዋል። በመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ላይ የቀረበውን አስተንትኖ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፥

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በየዕለቱ በሚቀርብ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ የሚነበበው ቅዱስ ወንጌል የቤተ ክርስቲያንን ቀናት እና ሲኖዶስንም ያድሳል፣ ያጅባል። ከሉቃ. 9፡51-56 ተወስዶ የተነበበው የወንጌል ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ የተልዕኮውን የመጀመሪያ ምዕራፍ በማጠናቀቅ ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደውን መንገድ መጀመሩን የሚገልጽ ነበር።

ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ለአገልግሎት ለማዘጋጀት ያደረገው ጥረት አድካሚ እና ወሳኝ የለውጥ ሂደት የታየበት ነበር። ዛሬ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት የምትጓዘው የኅብረት ጉዞ ወሳኝ እና ብርሃን የፈነጠቀበት የለውጥ ምዕራፍ ነው። የደቀ መዛሙርት መንፈሳዊ ዕይታ ሁል ጊዜ አዝጋሚ ቢሆንም ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በትዕግስት ወደፊት ይጓዛል።

ወንጌላዊው ሉቃስ የኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮ የመጀመሪያውን ክፍል ሲጽፍ፥ በገሊላ ስላለው መንግሥት በመናገር ያበቃል። (4.14-9.50) ኢየሱስ በናዝሬት በምኩራብ ውስጥ የጀመረውን ስብከት እና በዚያም ተከታዮቹ አለመቀበላቸውን ይናገራል። (ሉቃስ 4፡14-30) ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ለመውጣት የወሰደው ቆራጥ ውሳኔ ለደቀ መዝሙርነት እና ለሲኖዶሳዊነት ዘይቤ ብስለት የሚያገለግል ነው። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ መሪዎች ተፅዕኖ ከፈጠሩበት እና ከደቀ መዛሙርቱ አዝጋሚ ሂደት በኋላ ያሳየው አዲስ መነሳሳት ነው።

“የሰው ልጅ ለሞት አልፎ ሊሰጥ ይገባዋል” (ሉቃስ 9:44) ነገር ግን እነዚያ ጆሮዎች ይህን ምስጢር ከመስማት ይልቅ ተዘግተው መቆየትን መርጠዋል። ግልጽ ያልሆነላቸውን ለመጠየቅ ፈሩ። (9.45) ስለዚህ በልባቸው ይዘው እርስ በርስ ይወያዩበት ነበር። ልክ እንደ ኤማሁስ ደቀ መዛሙርት ጠንካራ የእርስ በርስ ንግግር እና የሃሳብ ትኩረትን የሚከፋፍል እንጂ የትም የሚያደርስ እንደሆነ በደንብ ይታወቃል።

ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምክንያት ወደ ኋላ አላፈገፈገም። የተለያዩ ሥልጣኖች ባለቤት ሆኖ ሁሉን ታጋሽ መለኮታዊ ትምህርት በእርሱ ተገለጠ። በሚያስደንቅ እና ቀላል በሆኑ ምሳሌያዊ ንግግሮቹ ሃሳቡን ይገልጽ ነበር። መንግሥቱን፣ አምላክነቱን እና ምሥጢርን ማወቅ እንዲችሉ አንድ ሕፃን ወስዶ፥ “እውነተኛ ሥርዓት ከዚህ የተለየ ነው፤ እኔን መከተል ሌላ ነው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎትም እንደዚህ ነው” በማለት ገለጸሁ። ቦንሆፌር የተባለ ጸሐፊ፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሕፃናትን ይገልጻል” በማለት ጽፏል። በሕጻን ውስጥ የእግዚአብሔርን ብርሃን ይታያል። እግዚአብሔር ከሕጻናት ወገን መሆን ይመርጣል። ምክንያቱም የምሥራች ደስታ የተገለጸው በሕጻኑ ኢየሱስ በኩል ነው"

በክርስቲያን ማኅበረሰብ እና በድሆች፣ በሰዎች መካከል ወጥተው በማይታዩት እና በእግዚአብሔርን እቅድ መካከል ጥልቅ ግንኙነት አለ። ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያ እንድናስብ ይጋብዘናል። እንደ ደቀ መዛሙርቱ መልካም ሥራዎችን እንድንሠራ በማሰብ የሌሎችን መልካምነት በልቡ ይይዛል። ለእግዚአብሔር ነፃነት ሌላ ምርጫ እንዳለ እንድንረዳ ያግዘናል። በጸጋው ነፃነት የተነካ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ የቃሉ ዘር አለ።በቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ውስጥ ወንጌልን መስበክ፥ በሰው ልጆች መካከል ያለው ነፃነት የሲኖዶሱን ሂደት የሚያሳይ መሆን አለበት።

ስለዚህም ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ፊቱን ከማዞሩ በፊት በሚያስገርም ምልክት ሕፃናትንን ወደ እራሱ ጠርቶ መንገድ አድርጎ ገለጸ። ይህ የወንጌል መልዕክት ለሲኖዶስ ጉባኤ ኃይለኛ ምልክት ነው። የኢየሱስን ፈለግ በመከተል በወንጌል መንገድ ላይ የመራመድ ዘዴን፣ የማያቋርጥ መለወጥን፣ ያልተለመዱ ሲኖዶሳዊ ዘይቤን ማለትም ደቀ መዝሙርነትን ይናገራል። በዛሬው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዝቅተኛውን እና ድሃውን እንዴት መለየት እና መቀበል ይቻላል? እኛ ምዕመናን ችግር ውስጥ በሚገኝ የሰው ልጅ መካከል አዲስ እንድንሆን እና ትንቢትን ለይተን እንድንቀበል ተጠርተናል።

03 October 2023, 16:59