ፈልግ

የስምንተኛው ቀን የሲኖዶስ ውሎ መግለጫ የተሰጠበትን ወቅት የሚያሳይ ምስል የስምንተኛው ቀን የሲኖዶስ ውሎ መግለጫ የተሰጠበትን ወቅት የሚያሳይ ምስል  (Vatican Media)

የሲኖዶስ አጭር መግለጫ፡- የወንድማማችነት ጥያቄ እንጂ ጦርነት ሳይሆን ለግጭቶች መፍትሄ መፈለግ ነው!

በሐሙሱ ጥቅምት 01/2016 ዓ.ም የሲኖዶስ መግለጫ ላይ በርካታ ተሳታፊዎች በጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ እየተወያዩ ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ያካፍላሉ፤ እነዚህም በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው አሳሳቢ ሁኔታ ጸሎትን ያካትታል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

መካከለኛው ምስራቅ፣ ዩክሬን፣ ኢራቅ፣ አፍሪካ፡ ለሰላም የሚደርገው ጸሎት በመላው አለም የምትገኝ ቤተክርስቲያንን አንድ ያደርጋል።

በቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት አማካይነት በቀረበው ወቅታዊ መግለጫ መሠረት ሲኖዶሱ ስለ ሲኖዶስ ያስተላለፈው መልእክት ይህ ነው። ሐሙስ ከሰአት በኋላ የተናገሩት በሃይማኖቶች እና በባህላዊ ውይይቶች ውስጥ አብሮ ለመራመድ አጣዳፊ መሆኑን ተናግረዋል ።

ለሰላም የጸሎት ኃይል

ምስክርነታቸውን ለጋዜጠኞች ከሰጡት መካከል እስራኤላዊ እና ፍልስጤማዊት የአረብ ካቶሊካዊት የፎኮላር ንቅናቄ ፕሬዝዳንት ማርጋሬት ካርራም ይገኙበታል።

ሐሙስ ጠዋት በሲኖዶስ የተደረገው የልመና ጸሎት “በጣም ጠንካራ ወቅት ነው” ሲሉ ለጋዜጠኞች የተናገሩ ሲሆን ምክንያቱም “ጦርነቱ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ ልቤ ተሰብሮ ነበር እናም እዚህ በሲኖዶስ ውስጥ ምን እያደረግሁ እንደሆነ እያሰብኩ ነው። ከሁሉም ጋር ለመጸለይ የምያስችል በጣም ጥልቅ ጊዜ ነበር” ብሏል።

እንደ ማርጋሬት ካርራም ለሰላም ብዙ ጥረቶች ያስፈልጋሉ፣ ነገር ግን "የጸሎት ኃይል ወሳኝ ነው" ያሉ ሲሆን

“ይህ ተሞክሮ አብሮ መመላለስ፣ መነጋገር፣ ራስን በሌሎች መፈተን ምን ማለት እንደሆነ እያስተማረኝ ነው፣ እና ሲኖዶሳዊነት ዘዴ ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያን የአኗኗር ዘይቤ መሆን አለበት፡ ሌላውን በአክብሮት ማዳመጥ፣ ከተለያዩ አስተያየቶች ባሻገር " በማለት ተናግሯል።

ከመላው ዓለም ጋር በጸሎት

የፎኮላር ንቅናቄ ፕሬዝደንት በመቀጠል በአለም ዙሪያ ያሉ ታማኝ የሆኑ ብዙ ሰዎችን ለማሳተፍ በዲጂታል መድረኮች ላይ ጨምሮ በቅርብ ቀናት ውስጥ የተተገበሩትን የሃይማኖት ተቋማት ያደረጉትን ጸሎት ብዙ ተነሳሽነት ጠቅሰዋል።

"ትናንት ከዩክሬን ጋር ግንኙነትም ነበር። በሕያው ሰላም ተነሳሽነት ለመጸለይ በተመሳሳይ ጊዜ ለመገናኘት ተስማምተናል፣ እና ለዓለም መሪዎች የሚቀርበውን የሰላም ጥሪ ለመፈረም ቃል በመግባት ለሌሎች ሃይማኖቶች ወንድሞች ተጨባጭ የአብሮነት መግለጫዎችን ጠየቅን ስሉ ጨምረው ገልጿል።

ጩኸት የማይሰማ መልካምነት

መልካም ስራዎች ድምጽ አያሰሙም፣ ሰዎች ስለ ጥላቻ ብቻ ይናገራሉ፣ ነገር ግን ማርጋሬት ካርራም በእስራኤል ውስጥ ብዙዎች በጋዛ ውስጥ ከሚኖሩት ጋር የሰላም ድልድይ ስለመገንባት እንደሚያሳስቧቸው ለመጠቆም ይፈልጋሉ።

“አንድ አይሁዳዊ ጓደኛ አለኝ” በማለት የተናገሩ ሲሆን “ከሙስሊሞች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ከነሱ ጋር በጸሎት አንድ እንዲሆኑ ለመጸለይ ወሰነ” ስሉ ተናግሯል።

ከጋዜጠኞች በተነሱት ጥያቄዎች የፎኮላር ንቅናቄ ፕሬዝደንት ድርድር እንዲቀጥል እና ይህን ግጭት የመፍታት አጣዳፊነት እንዲሰማ የአለም ማህበረሰብ የተቀናጀ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

“አሁንም በጣም ብዙ ዝምታ አለ። ድምፄ ብቻውን ፍሬ አያፈራም፣ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ እና በህዝቦች መካከል እርቅ እንዲፈጠር የሁሉም ሰው ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።

አፍሪካ እና ሲኖዶሳዊነት

"ሲኖዶሳዊነት የአፍሪካ ባህል አካል ነው፥ ምክንያቱም እኛ ሁልጊዜ ነገሮችን በቤተሰብ ደረጃ አንድ ላይ እናደርጋለን" በማለት የባሜንዳ ካሜሩን ሊቀ ጳጳስ አንድሪው ንኪያ ፉአንያ የአገሪቱ የጳጳሳት ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት ተናግሯል።

“ይህ ሲኖዶስ ለአፍሪካ ትልቅ መጽናኛ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ምክንያቱም በአፍሪካ ውስጥ ባሉብን ችግሮች አንዳንድ ጊዜ የተገለልን እና የተተወን ስሜት ይሰማናል። ወደ ሲኖዶስ ስንመጣ ግን ከዓለም አቀፉ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን በአፍሪካ እየተከሰቱ ያሉትን ችግሮች እና በተለይም በጦርነት ለተጎዱ አገሮች በጋራ ተቀምጠን እንጸልያለን” ስሉ የተናገሩ ስሆን እናም “ይህ ለአፍሪካ በሲኖዶስ ውስጥ የራሷን አሻራ ለማሳረፍ በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው ብዬ አስባለሁ” ሲሉም አክለዋል። ጦርነትን በተመለከተ ሊቀ ጳጳሱ በቅንነት “ጦርነት ፈጽሞ መፍትሔ ሊሆን አይችልም” ብለዋል።

የተለያዩ ቋንቋዎችን አንድ የሚያደርግ ወንጌል

በባግዳድ ጤና ጣቢያ ዶክተር እና የቅዱስ ልብ የኢየሱስ ገዳማዊያት ማሕበር አባል የሆኑት ሲስተር ካሮላይን ጃርጂስ ሲኖዶስ እንደ አንድ ቤተሰብ ሆኖ እንደ ተሰማቸው ገልጿል።

ዛሬ ጠዋት ከሌሎች የጉባኤው ተሳታፊዎች ጋር በመሆን በራሳቸው ቋንቋ በአረብኛ ወንጌልን አንብበው ንግግራቸውን ሁሉም ሰው እንዴት እንደተረዳው እንዳስገረማቸው ገልጿል።

“በሲኖዶስ በምንሠራው ሥራ እግዚአብሔር አለ። ወደ ሮም ከመምጣታችን በፊት መረጠንና አዘጋጀን ሲሉ ተናግረዋል፣ “በአንድ ላይ ሆነን ሁሉንም ነገር የተካፈሉ የመጀመሪያዎቹን ክርስቲያኖች ተሞክሮ እያገኘን ነው በማለትም አክለው ገልጿል።

የኢራቅ ሰማዕታት ምስክርነት

የእህት ካሮላይን እይታ በአገራቸው የሃያ አመታት የስቃይ ምልክቶችን ባይደብቁም አሁን ያለው ሁኔታ ተስፋን ያሳያል ያሉ ሲሆን “እኔ የመጣሁት በጦርነት ውስጥ ካለ፣ ክርስቲያኖች ጥቂቶች ከሆኑበት አገር ነው፣ ነገር ግን የቤተክርስቲያናችን ብልጽግና የሚሰጠው በሰማዕታት መገኘት ነው። ደማቸው “ለመቀጠል መነሳሳትን ይሰጠናል፣ እናም ከአለም አቀፋዊው ቤተክርስትያን ጋር ካለው ግንኙነት ልምድ በማግኝት በከፍተኛ ጥንካሬ ወደ ቤት እመለሳለሁ” ሲሉ ለጋዘጤኞች ተናግረዋል።

ለጋዜጠኞች ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢራቃዊው መነኩሲት ብፁዕ ካርዲናል ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ ከባግዳድ ፓትርያርክ ዋና መሥሪያ ቤት ለመልቀቅ መወሰናቸውን ፕሬዚደንት ራሺድ ለከለዳውያን ቤተ ክርስቲያን ካርዲናልን የክርስቲያን መሪ አድርገው እንደ ማይቆጥሩ በመግለጽ ያወጡትን ድንጋጌ በመሻር ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጻለች። ለቤተ ክርስቲያን ንብረት ኃላፊነት ያለው ማህበረሰብ መፍጠር የገባል ብለዋል።

“በሰማዕትነት ምድር እንደ ክርስቲያን ተከባብረን መኖር ተገቢ ነው፤ ሁለተኛ ዜጋ አይደለንም” ሲሉ መነኩሲቷ ተናግረዋል።

ወደ ካታኮምብስ የሚደረገው ጉዞ

ሐሙስ ከቀትር በኋላ የሲኖዶስ ተሳታፊዎች የቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስን ንዋያተ ቅድሳትን በጊዜያዊነት በማኖር ወደ ሚታወቀው የቅዱስ ሰባስቲያን ካታኮምብ እንዲሁም የቅዱስ ካታኮምብ እና የቅዱስ ዶሚቲላ ካታኮምብ ለመጎብኘት መጋበዛቸውን ጠቁመዋል።

አርብ ጧት ብፁዕ ካርዲናል አምቦንጎ ቤሱንጉ በሚመሩበት መስዋተ ቅዳሴ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው መንበረ ታቦት ላይ የተካሄደው ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኋላ 8ኛው ቀን አጠቃላይ ጉባኤው ይከናወናል። ጉባኤው በሦስተኛው በላቲን ቋንቋ Instrumentum laboris ‘የሥራ እቅድ’ ሰነድ  ላይ “በተልእኮ ውስጥ የጋራ ኃላፊነት፡ በወንጌል አገልግሎት ውስጥ ስጦታዎችን እና ተግባሮችን እንዴት በተሻለ መንገድ ማካፈል እንችላለን?” በሚል መሪ ቃል ይነጋግራል።

ቀደም ሲል በሰባተኛው ጉባኤ ረቡዕ መስከረም 30/2016 ከሰአት በኋላ እና ሐሙስ ጥዋት በጥቃቅን ቡድኖች ስድስተኛ ጉባኤ እና ሪፖርቱን ለሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት በማቅረቡ በሁለተኛው የሥራ ሰነድ - "ሕበረት" ላይ የተካሄደው ሥራ ተጠናቋል።

የሰባተኛው ቀን ጠቅላላ ጉባኤ ርዕሰ ጉዳዮች

ረቡዕ እለት በአዳራሹ 343 አባላት ተገኝተው 36ቱ ንግግር አድርገዋል። ከተነሱት ጭብጦች መካከል በሃይማኖቶች መካከል እና በባህል መካከል የሚደረግ ውይይት፥ በቅኝ ግዛት ውስጥ በአገሬው ተወላጅ ማህበረሰቦች ላይ ያለው ተጽእኖ፥ የኃጢአት ይቅርታን ከጠየቅን ለመቀበል የሚያስችለንን የእርቅ ምስጢር የሆነውን የምስጢረ ንስሐ አስፈላጊነት፥ እና ወጣቶችን ማዳመጥ እና ኢየሱስን ለመገናኘት በሚጠሙበት ጊዜ ማሳተፍ ... እነዚህን የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተውበት ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዚህ ረገድ ሊቀ ጳጳስ ንኪያ ፉአንያ እንደ ገለጹት ከሆነ ይህ ዓመት ለቅዱስ ቁርባን በተሰጠበት ወቅት እያንዳንዱ ደብር ለዘላለማዊ ስግደት የጸሎት ቤት በማዘጋጀት ላይ ያለውን ልምድ አካፍሏል።

በተጨማሪም በሲኖዶሱ ሥራ መሃል የካልካታዋ እናት እማሆይ ቴሬዛ ምስል እና ለታመሙ ሰዎች እንክብካቤ ማድረጋቸውን፣ ሰላምን ለማስፋፋት የካቶሊክ መሪዎች ቁርጠኝነት አጣዳፊነት፣ በዳርቻው ውስጥ የተገለሉ ሴቶች ድራማ፣ እና በቤተክርስቲያኗ ህይወት ውስጥ የመደመር እና የማዳመጥ አስፈላጊነት በተመለከተ ንግግር አድርጓል።

ሲኖዶሱ እና ማርያም

በመጨረሻም የማስታወቂያ ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፓኦሎ ሩፊኒ የቫቲካን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ ሐሙስ የእመቤታችን የአፓሬሲዳ እና የፒላር እመቤት ቅድስት ድንግል ማርያም በዓል መሆኑን አስታውሰዋል።

“ዛሬ ጠዋት”፣ “የማሪያን መገለጫ የሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነት አጽንዖት ተሰጥቶበታል። ማርያም እናት ናት፣ ምእመን ናት፣ ትንቢት ናት፣ ውይይት ናት፣ ባሕሪ ናት፣ ቅድስ ናት፣ ቅዱስ ወንጌልን የኖረች እናት ናት” ካሉ በኋላ የእለቱ መግለጫ አብቅቷል።

13 October 2023, 13:42