ፈልግ

የሲኖዶሱ አጭር መግለጫ በስደተኞች እና በጥገኝነት ጠያቂዎች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነበር። የሲኖዶሱ አጭር መግለጫ በስደተኞች እና በጥገኝነት ጠያቂዎች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነበር።  

የሲኖዶሱ አጭር መግለጫ በስደተኞች እና በጥገኝነት ጠያቂዎች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነበር።

የሲኖዶስ ተሳታፊዎች በምሽት የጸሎት ጊዜ ለስደተኞች እና ጥገኘት ጠያቂዎች ለመታደም በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት፣ ቤታቸውን ጥለው ለተሰደዱ ሰዎች ሁኔታ ቤተክርስቲያኗ የሰጠችው ምላሽ ሐሙስ ጥቅምት 8/2016 በሲኖዶሱ ላይ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ግንባር ቀደም አርዕስት ነበር።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሁሉም የሲኖዶሱ ተሳታፊዎች ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ ጋር ትላንታን ጥቅምት 8/2016 ማምሻውን - በአስራ ሦስተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ - በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ፣ “ድንገተኛ መላዕክት” ሐውልት አጠገብ በመሰባሰብ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ጸሎት አድርሰዋል። የተለያዩ የስደተኛ መንገዶች፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለተረፉት፣ እና አሁንም በመንገድ ላይ ላሉ ስደተኞች እና ጥገኘት ጠያቂዎች ጸሎት አድርገዋል።

እናም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ ዛሬ ከጋዜጠኞች ጋር በተደረገው አጭር መግለጫ ማዕከል ነበር።

የእግዚአብሔር ቃል ማበብ፣ በዝምታ ማሰላሰል፣ ምልጃ እና የጌታ ጸሎት የሐሙስ ምሽት የጸሎት ጊዜ የሚከበርበት ሲሆን ይህም የሲኖዶስ ማህበረሰብ ከጉባኤው መጀመሪያ ጀምሮ የውይይት እና የጭንቀት ማዕከል የሆኑትን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ጭብጥ የያዘ የጸሎት ጊዜ ነው።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወደሚገኘው ምሳሌያዊ ሃውልት ከጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ “በአንድነት” በሚደረገው የሲኖዶስ ዘይቤ “ያልታወቁ” ጦርነቶችን ጨምሮ በተለያዩ ጦርነቶች የተከሰቱትን አሳዛኝ ክስተቶች ለማጉላት ዝግጅቱ “ሁለንተናዊ ባህሪ” ይኖረዋል።

ሐሙስ ዕለት በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት የቫቲካን የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ፕሬዚደንት እና የመረጃ ኮሚሽን ዋና ፕሬዝዳንት ዶ / ር ፓውሎ ሩፊኒ በመሰብሰቢያ አዳሽ ውስጥ የተከናወነውን የእለቱን ጉባሄ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። እሮብ ከሰአት በኋላ እና ሐሙስ ጥዋት፣ በ35 አነስተኛ ጠረጴዛዎች ዙሪያ ጉባሄ ያደርጉት   አሥረኛው እና አሥራ አንደኛው ክፍለ ጊዜ የተካሄደው “በመንፈስ ውስጥ ለመነጋገር” ከተወሰነ ጊዜ ጋር ነው። ውይይቶቹ በአሁኑ ጊዜ በሥራ መርዓ ግብር  ክፍል B3 ላይ ያተኮሩ ናቸው፡ 35ቱ ትንንሽ ቡድኖች ስለ አጠቃላይ ጭብጥ የተለያዩ ገጽታዎች እየተወያዩ ነው፡ “ተሳትፎ፣ ኃላፊነት እና ስልጣን። በሚስዮናውያን ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ሂደቶች፣ አወቃቀሮች እና ተቋማት ምንድን ናቸው?”

በተጨማሪም የኮሙንኬሽን ዳይረክተሩ አክለው እንደ ገለጹት በትላንትናው እለት የጉባሄው ዋና ኃላፊ በሆኑት  ካርዲናል ዣን ክላውድ ሆሌሪች የተነገረውን እውነታ አስታውሰው፣ “ከጠቅላላ ጉባኤዎች ጋር የሚካፈሉ የነገረ መለኮት፣ የሐይማኖት እና የሕገ ቀኖና ሊቃውንት ሦስት የሥራ ቡድኖች ተቋቁመው በሦስት ሪፖርቶች የእነርሱን አስተያየት አስታውሰዋል። በሥራ መርዓ ግብር  B3/3 ነጥቦች ላይ ("የሚስዮናውያን ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያንን ለማጠናከር ምን ዓይነት መዋቅሮች ሊዘጋጁ ይችላሉ?")፣ B3/4 ("የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መቧደንን የሚያካትት የሲኖዶሳዊነት እና የሕብረት ሁኔታዎች እንዴት ሊዋቀሩ ይችላሉ?")፣ እና B3/5 (“የሲኖዶሱ ተቋም በሁሉም ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሕብረት እንዲሆን እንዴት ሊጠናከር ይችላል?”)።

ካርዲናል ቼርኒ በምድር ላይ ካሉ በጣም ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር አብሮ መጓዝ

ብፁዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ፣ በቅድስት መነበር የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማትን ለማስፋፋት የሚሰራው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተዳዳሪ፣ ለስደተኞች እና ለጥገኘት ተያቂዎች በትደርገው ጸሎት ላይ ተገኝተዋል። ‘ድንገተኛ መላእክት’ በተሰኘው ሐውልት ፊት፣ የሲኖዶስ ጉባኤው “እንደ ቤተ ክርስቲያን እንዴት በአንድነት መሄድ እንዳለብን እየተማረ ያለው በፕላኔታችን ላይ ካሉት በጣም ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ማለትም ከሚሸሹት፣ ከእነዚያም ጋር አብሮ መሄድን ያሳያል። በጉዞ ላይ እንዲሆኑ የተገደዱ፣ እኛ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከምንላቸው ጋር እንዴት አብረን ለመጓዝ እንችላለን” ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

ስለዚህም “ይህንን ቀን በምናሳልፍበት ወቅት መንፈሳዊ እና እንዲያውም ውበት ያለው የባህል ስምምነት አለ” ሲሉ በሲኖዶስ ጉባኤ ላይ በመጠኑም ቢሆን ረቂቅ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በመርከቡ የተወከለውን የስደት ክስተት “በመጓዝ ወይም በመያዝ” በነሐስ የተቀረጸው በጢሞቴዎስ ሽማልዝ በተሰራው ሐውልት ዙሪያ ተስብስበው ለስደተኞች ጸሎት እንደ ሚደረግ ገልጸው “ይህም በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን እና በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ሰዎችን ሁሉ ይወክላል” ሲሉ ተናግረዋል።

ካርዲና ቼርኒ ግን “በመስማማት እና በጎ ፈቃድ እና በሲኖዶስ አዳራሽ ውስጥ በምናገኘው ጥልቅ ልውውጥ” እና በስደተኞች እና በጥገኝት ተያቂዎች “ጭንቀት፣ ስጋት፣ ተጋላጭነት፣ መገለል” መካከል ያለውን “አስደናቂ ልዩነት” ገልጸው እናም “አስፈሪው ጸጥታ…የእኛ ማህበረሰቦች፣ እምቢተኛ ማህበረሰቦቻችን” እንደ ሆነ ያሳያል ብሏል።

አቡነ ዳኒኤል ኤርነስት፡- ከድንበር ሀገረ ስብከት

የጉባኤው ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የመሰናዶ ኮሚሽን አባል አቡነ ዳንኤል ኧርነስት ፍሎሬስ አሜሪካ ከሜክሲኮ ጋር የምትወሰንበት የቴክሳስ የብራውንስቪል ጳጳስ ናቸው። እርሳቸው መግለጫቸውን የጀመሩት “በዓለም ላይ ያለው እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የራሱን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ስጦታና ልምድ ይዞ ወደ ሲኖዶስ ይመጣል” በማለት አስታውሷል።

አቡነ ዳኒኤል ፍሎሬስ የራሳቸውን የድንበር ሀገረ ስብከት ልምድ ሲናገሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከላቲን አሜሪካ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ብራውንስቪል የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። ነገር ግን የምእመናንን ምላሽ አጥቶ አያውቅም፡- “በሀገረ ስብከቴ ውስጥ ከሰዎች፣ ከሬስቶራንት ባለቤቶች፣ ከሐኪሞች፣ ከነርሶች፣ እናቶችንና ሕጻናትን ለመንከባከብ ጊዜያቸውን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚሰጡ ታላቅ፣ ታላቅ የኃይል ፍሰት አለ” ሲሉ የሌሎች ማኅበረሰቦች አባላት፣ ሌሎች የክርስቲያን ቤተ እምነቶች፣ ሙስሊሞችና አይሁዶችም ጠቃሚ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አቡነ ዳኔል ፍሎሬስ እንዳስረዱት፣ ሀገረ ስብከታቸው ብዙ ቁሳዊ ሀብት እንደሌለው፣ ነገር ግን የሕዝቡ ልብ በጣም ለጋስ ነው፣ እናም ድህነት ምን እንደሆነ የሚያውቅ አንድ ነገር ስለሚያውቅ ለጋስ ምላሽ ይሰጣሉ ብለዋል።

አክለውም “መርሀችን የሚመጣውን ቤተሰቦች ሰብአዊ ክብር ለማክበር እና ለማስተናገድ በሚሞክር መንገድ መላመድ ነው። እያንዳንዳቸው ታሪክ አላቸው" ብለዋል።

ማሮናይት አልዋን፡ የሊባኖስ የሶሪያ ስደተኞች ድራማ

የሊባኖስ ማሮናዊ ሚስዮናውያን የቀድሞ ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩት አባ ካሊል አልዋን የምስራቃውያን የካቶሊክ ፓትርያርኮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ እና በቤይሩት በሚገኘው የሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ናቸው። የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት የሲኖዶስ ምስክር እና የመካከለኛው ምስራቅ ዋና አስተባባሪ በመሆን በጠቅላላ ጉባኤው እየተሳተፉ ነው።

ከአህጉር አቀፍ ጉባኤዎች የመጡት ከኤጲስ ቆጶሳት ውጪ ካሉት ተሳታፊዎች መካከል አንዱ የሆኑት አባ አልዋን በአራት ሲኖዶስ የተሳተፉ ሲሆን አሁን ያለውን በአሰራርና በይዘቱ የተለየ አድርገው ይመለከቱታል፡- “ከጌታ ጋር፣ ከቤተክርስቲያን ጋር እውነተኛ ጉዞ ነው። ሁሉም እውነታዎች እዚህ ይወከላሉ። በዚህ ውስጥ መሳተፍ ለቤተክርስቲያኗ አስደሳች የወደፊት ተስፋ ምክንያቶችን የሚሰጥ ታላቅ ጸጋ ነው” ብለዋል።

በመቀጠልም የማሮናዊው ቄስ በሊባኖስ ስላሉት የሶሪያ ስደተኞች ሁኔታ ሲናገሩ ወደ ዋናው የንግግራቸው ጭብጥ ሲሄዱ፡- እ.አ.አ “ከ2011 ጀምሮ እዚህ ሲደርሱ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ እየኖሩ ነው፣ በስደተኞች ካምፖች ውስጥ በብዛት ተጨናንቀው ይገኛሉ። ይህም ከእነርሱ አቅም በላይ ነው፣ ምክንያቱም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊባኖስን በግዛቷ ላይ ስደተኞችን እንድታቆይ ስለሚያስገድዳቸው ወደ አውሮፓ እንዳይሄዱ ይከላከላል” ብለዋል ።

አባ አልዋን እንዲህ ባሉ አካባቢዎች “ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይኖራሉ” ሲሉ ገልፀው “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብዙ ልደቶች ተመዝግበዋል” ሲሉ አክለውም “አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ሊባኖስ በዓለም ላይ ከፍተኛውን የስደተኞች ቁጥር የያዘች ሀገር ነች” በማለት ተናግሯል። አስጊ ሁኔታውን ለመቅረፍ አንዳንድ ሰብዓዊ እርዳታዎች መደረጉን አምነው፣ ስደተኞች ሰብዓዊ ክብራቸውን ወደጠበቀ ቦታ እንዲሄዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።

ሊባኖሳውያን “ለሰብአዊነታቸው” እየተቀጡ ነው ሲሉ አባ አልዋን አረጋግጠዋል። እነዚህ ሁሉ ስደተኞች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ያሳድራሉ፤ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ድርጅቶች ሊቋቋሙት የማይችሉት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን በውጤቱም “የሊባኖስ ዜጎች እየደኸዩ እና እየደኸዩ ነው። ይህ በእነሱ ውስጥ ትልቅ ቁጣን ያስከትላል፡ የሰብአዊ ጉዳይን የፖለቲካ ጥገኝነት አገር እንድትሆን በተገደደችው ሊባኖስ ውስጥ ስደተኞችን ለማቆየት እንደ ምክንያት አድርገው ይመለከቱታል ብለዋል።

“ብዙ ድምፅ ተሰምቷል” ሲል ቄሱ ሲያጠቃልሉ፣ “ሶሪያውያን ወደ አውሮፓ እንዲሄዱ ጥሪ አቅርበዋል። የሰው ልጅ አሳዛኝ ክስተት እየገጠመን ነው እና የአለም ኃያላን ጉዳዩን በአጽኖት ለመፍታት እንዲሰሩ እና ሶርያውያን አንድ ቀን ወደ ሀገራቸው እና ወደ ባህላቸው እንዲመለሱ ዛሬ ምሽት እንጸልያለን ካሉ በኋላ ንግግራቸውን እጠናቀዋል።

አቡነ ምፓኮ፡ መቀበል፣ ማዳመጥ፣ መከባበር

የፕሪቶሪያ ሊቀ ጳጳስ እና የደቡብ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባኤ ምክትል ፕሬዚዳንት ሊቀ ጳጳስ ዳቡላ አንቶኒ ምፓኮ፣ በአገራቸው ያሉ ስደተኞችንና ጥገኘት ጠያቂዎችን ሁኔታ ዘርዝረዋል።

“በመንፈስ ቅዱስ የሚደረግ ውይይት” ላይ የመሳተፍ እድል እንደ ሲኖዶስ ሂደት ዘዴ በመሆኑ አድናቆታቸውን በመግለጽ የጀመሩት ሊቀ ጳጳሱ በመደማመጥ፣ በመከባበር እና በመቀበል ሰዎች በእውነት መደጋገፍ እንደ ሚችሉ ተናግረዋል። "በተመሳሳይ ጊዜ፣ ከየት እንደመጣሁ መለስ ብዬ ሳስበው በብዙ የአፍሪካ አገሮች ለዚህ ሲኖዶሳዊ ሂደት ምቹ ሁኔታ እንዳለን ተረድቻለሁ" ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ምፓኮ እንዳሉት አገራቸው "ለስደት እና ለስደተኞች ሐዋርያዊ እንክብካቤን ለመስጠት ተግዳሮት እየተጋፈጠች ነው" ሲሉ ሀገሪቱ ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እያስተናገደች ሲሆን ይህም በአፍሪካ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚመጡት አብዛኞቹ ስደተኞች “የኢኮኖሚ ስደተኞች” መሆናቸውን በማብራራት “የዚህ የስደት ዋነኛ መንስኤ ድህነት ነው” ብሏል።

እራሳቸው ሊቀ ጳጳሱ በሚኖሩበት ከተማ ፕሪቶሪያ - ለስደተኞች በጣም ታዋቂ ከሆኑ መዳረሻዎች አንዷ እንደ ሆነች ጠቅሰው - ሊቀ ጳጳስ ምፓኮ ቤተክርስቲያን "ለስደተኞች እና ለጥገኝነት ጠያቂዎች የሐዋርያዊ እንክብካቤ አገልግሎት በጥሩ ሁኔታ የተመሰረተ አገልግሎት" እንዳላት ገልጸዋል ይህም የምግብ አቅርቦትን ጨምሮ ተግባራዊ ፍላጎቶችን ለመርዳት የሚሞክር ነው። ልብስ፣ ጤና አጠባበቅ እና አስፈላጊ በሆኑ ሰነዶች እገዛ በማድረግ።

ሊቀ ጳጳስ ምፓኮ በተጨማሪም የካቶሊክ ስደተኞችን ፍላጎት በተመለከተ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር እንዲዋሃዱ ለመርዳት ጥረት እንደምታደርግ ገልጸው፣ እንዲሁም ሁኔታቸውን የሚያሟላ የሐዋርያዊ አገልግሎት በመስጠት፣ ለምሳሌ በቋንቋቸው ሥርዓተ አምልኮ በማዘጋጀት እና የሚስዮናውያን ካህናትን ለነሱ በመሾም እነሱን ለመርዳት የራሳቸው አገር ሰዎች እንዲረዷቸው ጉዳዮችን በማመቻቸውት ላይ እንደ ሆኑም ገልጿል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲኖዶሳዊነት እና ተዋረድ

ሲኖዶሳዊ ጉባኤን መሠረት አድርጎ የመዋቅር እድሳት መታደስ የሀገረ ስብከቱን ጳጳሳት ሥልጣንና ሥልጣናቸውን ሊያሳጣው ይችላል ወይ ለሚለው ጥያቄ አቡነ ፍሎሬስ ሲመልሱ፣ ይህ ጉዳይ አዲስ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። የቤተክርስቲያኗ የስልጣን ወይም የአገልግሎት አጠቃቀም በልብ መለወጥ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ምክንያቱም ይህ ለማንኛውም መዋቅር አዎንታዊ ግቦችን ለማሳካት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ይህ እድሳት እንዴት እንደሚካሄድ ብዙ አስተያየቶች እንዳሉ አምነዋል፣ ነገር ግን የበለጠ እንደሚያሳስበን ተናግሯል “እርስ በርስ በማገልገል ላይ ያተኮሩ የተጠመቁ እና የተሾሙ ሰዎች ለመሆን ጥልቅ ጥማትን እንዴት ከክርስቶስ ልብ ጋር ማጣጣም እንደምንችል "ለእኔ ይህ ሁሉም ነገር ነው" በማለት ተናግሯል።

ከእዚያም በመቀጠል ሊቀ ጳጳስ ምፓኮ ሲናገሩ ሁለቱ መዋቅሮች በአንድነት መኖር እንዳለባቸው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው አስታውሰዋል። “ይሁን እንጂ፣ እኛ ለማየት የምንፈልገው ምናልባት ሁለቱ እንዴት ሊሠሩ እንደሚችሉ፣ ሲኖዶሳዊው የቤተ ክርስቲያን ተዋረዳዊ መዋቅር በሚሠራበት መንገድ እንዲሠራ ማድረግ ነው” ብሏል።

በዚሁ ጊዜ “በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲኖዶሳዊው ልዩ ባህሪ አለው። በመሃል ላይ የጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ መንበር የሚገኝበት ሲኖዶስ ነው። በቀኑ መጨረሻ የሥልጣን ተዋረድ ከሲኖዶሳዊነት ጋር አብሮ ይሄዳል።

ብፁዕ ካርዲናል ክዘርኒ አክለውም፣ “የቤተክርስቲያኗ ተዋረድ አወቃቀሮች በማዳመጥ ከሚጀመረው ሂደት ምንም የሚያስፈራቸው ነገር የለም። ይህ የቤተክርስቲያኗን ተዋረድ ሊጎዳ አይችልም” ብሏል።

የኤልጂቢቲ ሰዎች በስደተኞች መካከል መኖራቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሊቀ ጳጳስ ምፓኮ ሲመልሱ፣ ቤተ ክርስቲያን እነሱን እንዴት መቅረብ እንዳለባት ያላት አቋም ግልጽ ነው፡- “በመጀመሪያ ርኅራኄን እና ተቀባይነትን ለማሳየት እንጂ አድልዎ ላለማድረግ፣ የውጭ ሰዎች እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ አይደለም። በቤተክርስቲያኗ ማህበረሰብ ውስጥ። ይህንንም ቅዱስ አባታችን በሚያስደንቅ እና በሚያምር መልኩ የገለጹት ይመስለኛል ብለዋል።

በመቀጠል “ነገር ግን፣ እኛ የምናስተናግደው ባህላዊ የክርስቲያን ስነ-ሰብዕ ነው፣ አሁንም ያ አንትሮፖሎጂ ከዚህ ጥያቄ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ለማየት እየሞከርን ነው። እናም እኔ የማስበው ይህ ነገር በቅርቡ አይፈታም ምክንያቱም እኛ ለረጅም ጊዜ የነበረን ወግ እያስተናገድን ነው ።

ስለዚህ የደቡብ አፍሪካው ሊቀ ጳጳስ “ሁለት ነገሮችን እያደረግን ነው። ያንን የክርስቲያን አንትሮፖሎጂ በመያዝ፣ LGBTQ+ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ቤታቸው ሆኖ እንዲሰማቸው ለማድረግ መንገዶችን እንፈልጋለን።

አቡነ ፍሎሬስ በበኩላቸው፣ በሀገረ ስብከታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን መቀበል “የቤተ ክርስቲያን የበጎ አድራጎት ተልእኮ” እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል። ስለዚህ፣ ሁሉም ፈቃደኛ ሠራተኞች “የሚሰቃይ ሰው የክርስቶስን ፊት እንዲፈልጉ” ያበረታታቸዋል፣ አክሎም፣ “ካቶሊክ መሆናቸውን አንጠይቃቸውም፣ ክርስቲያን መሆናቸውን አንጠይቃቸውም። በፖለቲካዊ መንገድ እንዴት እንደሚያምኑ ታውቃላችሁ ብለን አንጠይቃቸውም፣ ስለ ጾታዊ ዝንባሌያቸው አንጠይቃቸውም፣ እኛ የምንፈልገው መከራ የሚቀበለውን ክርስቶስን ማገልገል ነው።

አቡነ ፍሎሬስ ስለ ሲኖዶሱ አመለካከት የላቲን አሜሪካን ባህሎች ፍላጎት በተመለከተም ተጠይቀዋል። አቡኑ ሲመልሱ ምንም እንኳን ቀላል ባይሆንም በተለይም በጥሩ ሁኔታ ከሰራህ የተለያዩ ባህሎችን አንድ ላይ ማሰባሰብ የሲኖዶሳዊነት መገለጫ ነው ሲሉ መለሱ። በተጨማሪም በላቲን አሜሪካ እና በአንግሎ-አሜሪካዊ ባህሎች መካከል ምንም መለያየት በሌለበት በሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ቤተሰብ ውስጥ ስላደጉበት የግል ልምዱ ተናግሯል። አንዱን ዓለም ወደ ሌላ ዓለም ለመተርጎም የመሞከር ጉዳይ ነው ሲል ገልጿል። ወጣቶች ይህንን እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ በተለይም እንደ እርሳቸው በድንበር አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ጠቃሚ ነው ብሏል። ሆኖም፣ አንድ ሰው በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ማቃለል እንደማይችል አስጠንቅቋል። በተቃራኒው፣ በተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ይበልጥ የተዋቀሩ ውይይቶችን ለማድረግ አንድ ሰው እድገት ለማድረግ መጣር አለበት።

"በሁለት አለም የኖሩት" ካርዲናል ቼርኒ ለእርሳቸውም ቢሆን "ህይወት ትርጉም ነው፣ እና 'ሲኖዶሳዊነት' ምናልባት በሁለቱም ባህሎች ወይም በሁለት ባህሎች ውስጥ ባትወለዱም እንኳ እንዴት መተርጎም መማር ሊሆን ይችላል።

በትናንሽ ቡድኖች ውስጥ ስለሚደረጉ ውይይቶች እና ስለ ውህደት ሰነዱ ላይ ድምጽ መስጠትን በተመለከተ አንዳንድ ዘዴያዊ ማብራሪያዎች ዶክተር ሩፊኒ ለሌላ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

አቡነ ፍሎሬስ እና ሊቀ ጳጳስ ምፓኮ ለተጨማሪ የመገናኛ ብዙኃን ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ የሲኖዶሱ ነጸብራቅ በውጫዊ ጫናዎች ወይም “ሴራዎች” ላይ ተጽዕኖ እንደሌለው ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል ፣ “ሴራ አይታየኝም” ብለዋል ። “በቅንነት፣ ታማኝነት፣ የበጎ አድራጎት ንግግሮችን ሰምቻለሁ፣ እንዲህ ልበል… ‘sub tutela Petri’፣ በጴጥሮስ እንክብካቤ። ይህ ለእምነት አስጊ አይደለም" ብለዋል።

 

20 October 2023, 14:27