ፈልግ

የሲኖዶስ ጉባኤ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት አደረገ!

የሲኖዶሱ ጠቅላላ ጉባኤ የሀሙስ ማለዳ ዝግጅቱን በጸሎት በጀመረበት ወቅት በተለይም በቅድስት ሀገር የከለዳውያን ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ፓትርያርክ በመሪነት በተካሄደው ጸሎት በሁከትና በፍርሀት ለሚኖሩ ሁሉ መጸለያቸው ተገልጿል።  

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የሲኖዶሱ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሀሙስ ማለዳ ጥቅምት 1/2016 በተደርገው ጸሎት ለዓለማችን ሰላም እግዚአብሔርን ለመለመን ወስኗል።

የእለቱ የመክፈቻ ጸሎት በኢራቅ ብፁዕ ካርዲናል ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ የከለዳውያን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በዓለማችን በጦርነት ለሚሰቃዩ እና በፍርሃት ለሚኖሩ ሁሉ በመጸለይ የተጀመረ ሲሆን ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ እንዳሉት "ዛሬ ጠዋት ለዓለም ሰላም በተለይም ለቅድስት ሀገር በተጨማሪም በዩክሬን በኢራቅ፣ በኢራን እና በሊባኖስ ስላለው ሁከት እንድትፀልዩ እጋብዛችኋለሁ ማለታቸው ተገልጿል።

"ህዝቡ በብዙ ተስፋ እየጠበቀ ነው" ሲሉ የተናገሩት ካርዲናል ሳኮ በመቀጠልም "በክብር እና በወንድማማችነት ለመኖር እንጂ ሁልጊዜ በፍርሃት እና ለመጨነቅ አይደለም የተፈጠርነው" ብሏል።

ብፁዕ ካርዲናል ጸሎታቸው ወንድማማችነትን እና በመከራ ውስጥ ካሉት ሁሉ ጋር እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

"የሰው ልጅ ያለ ግፍ አንድ ቤተሰብ ይመሥርት" ሲሉ የገለጹ ሲሆን ጉባኤው መዝሙር 129ን ጨምሮ "ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ አቤቱ ቃሌን ስማ" የሚለውን ጨምሮ ብዙ ጸሎቶችን አድርገዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ በማለዳው ጸሎት ላይም እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፡- “ለሁሉም የምትጨነቅ አምላክ ሆይ ከአንተ አንድ መነሻ ያለው፣ አንድ ቤተሰብ ያለው፣ ያለ ግፍ፣ ያለምክንያት ጦርነት፣ በወንድማማችነት መንፈስ የሰው ዘር በሙሉ በአንድነት በሰላም ይኑር። አምላክ ለሆነው ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልጅህ ከአንተ ጋር በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚነግሥ ነው” ሲል ጸለዩ።

“‘ስለ ሁሉም የምታስብ አምላክ ሆይ፣ ከአንተ አንድ መነሻ ያለው፣ አንድ ቤተሰብ፣ ያለ ግፍ፣ ያለምክንያት ጦርነት፣ በወንድማማችነት መንፈስ፣ በአንድነት የሚኖር የሰው ዘር በሙሉ በሰላም ይኑር...”

የጳጳሱን የማያቋርጥ ጸሎቶችን መቀላቀል

 

እንዲሁም በሲኖዶሱ የጠዋት ፀሎት ወቅት የፎኮላር ንቅናቄ ፕሬዝዳንት የፍልስጤም ካቶሊካዊት መሪ ማርጋሬት ካርራም ለሰላም ፀሎት እንዲደረግ ጋብዘው ነበር።

“ጌታ ሆይ፣ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁከትና ብጥብጥ ሥር ላሉ የእስራኤልና የፍልስጥኤም ሕዝብ፣ ለተጎጂዎች፣ በተለይም ለሕጻናት፣ ለቆሰሉት፣ ለታጋቾች፣ ለጠፉት እና ለሟቾቹ ስለ ቅድስት አገር እንጸልያለን ብሏል።

"በእነዚህ የጭንቀት እና የእገታ ሰአታት ውስጥ ድምጻችንን ወደ ጳጳሱ እና በአለም ዙሪያ ሰላም ለሚለምኑ ሰዎች የመዝሙር ጸሎት እናቀርባለን" ብሏል።

ወይዘሮ ካራም ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን እና በጦርነት ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም ሀገራት በሽብር እና በጥፋት ውስጥ እንዳሉ አስታውሰዋል።

"እነዚህ ህዝቦች እና በተመሳሳይ የእርስ በርስ ግጭት እና ብጥብጥ ሁኔታ ውስጥ ያሉት ፍትህ፣ ውይይት እና እርቅ የማይታለፉ የሰብአዊ መብቶች መከበር መንገድ እንዲያገኙ የወንድማማችነትን ዓለም ለመገንባት እራሳችንን እንድንሰጥ እርዳን። ሰላምን መገንባት አንድንችል እርዳን” ሲሉ ጸልየዋል።  

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይግባኝ

በእነዚህ ቀናት እና ቀደም ባሉት ጊዜያት ቅዱስ አባታችን በጦርነት ለሚሰቃዩት ሀገራት ሰላም እንዲሰፍን በረቡዕ እለት አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ ለቅድስት ሀገር እና በመካከለኛው ምስራቅ በሁከት ለተጎዱ ሀገራት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፀሎቶችን አድርገዋል።

ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የሩስያ ወረራ ከጀመረ ወዲህ በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ጥሪዎችን አቅርቧል።

12 October 2023, 15:20