ፈልግ

16ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ 16ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ  

የረቡዕ የሲኖዶስ ጋዜጣዊ መግለጫ ማጠቃለያ

ካርዲናል ሮበርት ፕሬቮስት እና ካርዲናል ዲዩዶኔ ንዛፓላይንጋ፣ ሊቀ ጳጳስ ጢሞቴዎስ ብሮሊዮ እና ዶክተር ኖራ ኮፎኖቴራ ኖንተራህ በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት እሮብ ጥቅምት 14/2016 በተደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የጠቅላላ ጉባኤውን ልምድ አካፍለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቫቲካን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዋና ዳይሬክተር እና የመረጃ ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ / ር ፓኦሎ ሩፊኒ  እና የኮሚሽኑ ፀሐፊ የሆኑት ሺላ ፒሬስ የጠቅላላ ጉባኤውን ሥራ በየዕለቱ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ገልጸዋል።

ለእግዚአብሔር ሕዝብ የተላከው መልእክት ረቡዕ ጥቅምት 14/2016 ጠዋት በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ለተሳታፊዎች መከፋፈሉን አስታውቀዋል። መልእክቱ ረቡዕ ከሰአት በኋላ ጸድቋል፣ የቅንጅት ሰነዱ ቅዳሜ ጠዋት ጮክ ተደርጎ መድምጽ ይነበባል እና ከሰአት በኋላ ድምጽ ይሰጣል።

የኮሚሽኑ ፀሐፊ የሆኑት ሺላ ፒሬስ... “ደብዳቤ ለእግዚአብሔር ሕዝብ” የተላከ ነው

ረቂቁ በጉባዔው ሲነበብ ከሰኞ ጀምሮ የቀረበው “በጉባዔው ሐሳቦች ላይ ተመርኩዞ በቃል ጣልቃ ገብነትና በጽሑፍ አስተያየቶች የተሻሻለው የእግዚአብሔር ሕዝብ መልእክት ዛሬ ለአባላት ተላልፏል፣ በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሟል ሲሉ ወይዘሮ ፒሬስ አብራርተዋል።

"በዛሬው ክፍለ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ብፁዕ ካርዲናል ግሬች እንደተናገሩት፣ በእነዚህ ቀናት የምንኖረውን አዎንታዊ ተሞክሮ ለመድገም ያለመ 'ቀላል ጽሑፍ' ነው" ሲሉ ንግግራቸውን የቀጠሉት ፒሬስ መጀመሪያ ላይ እርሳቸው መልእክቱ በአድናቆት ሊጸድቅ ይችላል የሚል ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል፣ ይህ እቅድ የተጣለበት ስለ ውህደት ሰነድ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት ነው ሲሉ አክለው ገለጸዋል።

የኮሚሽኑ ፀሐፊ የሆኑት ሺላ ፒሬስ “በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለውጦች በተጠየቁበት ወቅት፣ የሲኖዶሱ ሴክሬታሪያት ሰኞ ጥቅምት 12/2016 በመልእክቱ ላይ ዛሬ ድምጽ እንደሚሰጥበት አስታውቋል፣ እናም ቀደም ሲል ከቀረቡት ሃሳቦች በተጨማሪ የውህደት ሀሳቦችን ማቅረብ እንደሚቻል አስታውቋል ሲሉ አስታውሰዋል።  

በማጠቃለያው የኮሚሽኑ ፀሐፊ የሆኑት ሺላ ፒሬስ በመልእክቱ  ላይ ድምጽ መስጠት የሚችሉት የሲኖዶስ አባላት ብቻ እንደሆኑ እና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ኤሌክትሮኒክ እና ሚስጥራዊ እንደሚሆን ገልፀው ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የእያንዳንዱን የግል ነፃነት ለማረጋገጥ ነው ሲሉ ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።

ሩፊኒ፡- የ"ሰነዱን ጥንቅር" የማጽደቅ ሂደት

የቫቲካን ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር እና የመረጃ ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ / ር ፓውሎ ሩፊኒ  በበኩላቸው እንደ ተናገሩት ከሆነ “ዛሬ ጠዋት የዚህ የሲኖዶስ የመጀመሪያ ስብሰባ የመጨረሻ የውይይት ሰነድ ቀርቦ ተሰራጭቷል” ሲሉ ይገለጹ ሲሆን  ጽሑፉ 40 ገፆች ያሉት ሲሆን በጣሊያንኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ተሰራጭቷል፣ በሌሎች ቋንቋዎች የሚሰራባቸው ትርጉሞች በቅርቡ ይከናወናሉ ብሏል። በሰነዱ ላይ የሚደረገው ውይይት እና ድምጽ መስጠት እንዴት እንደሚካሄድም አብራርተዋል።

በተጨማሪም የቫቲካን ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር እና የመረጃ ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ / ር ፓውሎ ሩፊኒ   አክለው  “እንዲሁም የጉባኤውን ተፈጥሮ እና ስልጣን፣ ጳጳስ ያልሆኑ አባላት በተገኙበትም ቢሆን በድጋሚ ለማረጋገጥ የሚያስችል አጋጣሚ ነበር። ይህ የምክክር ጉባኤ መሆኑ አጽንኦት ተሰጥው ተናግረዋል። ኤጲስ ቆጶስ ያልሆኑት ተሳታፊዎች በሐዋርያዊ ሕገ ቀኖና በላቲን ቋንቋ “Episcopalis communio” (የኢጲስ ቆጶሳት ሕብረት) ውስጥ ተካቷል ብሏል። አሁን ያለንበት የማጠቃለያው ምዕራፍ አዲስ ጅምር ሳይሆን የኢጲስ ቆጶሳት ሕብረት የታሰበውን የሲኖዶስ ሂደት ውስጥ ሌላ እርምጃ ነው። የጉባዔው ኤጲስ ቆጶስነት ባህሪ ከኤጲስ ቆጶስ በላቲን ቋንቋ “munus” (ተግባር) ጋር መሳተፋቸው እና መኖራቸው አይጎዳም። መገኘታቸው የጉባኤውን ባህሪ እንደማይለውጥ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ዶክተር ሩፊኒ። “ኤጲስ ቆጶስ ያልሆኑ አባላት መገኘት በምስክርነታቸው ላይ የተመሰረተ ነው፡ ይህ ጉባኤ የተናጠል ክስተት ሳይሆን ዋና አካል እና አስፈላጊ የሆነ የሲኖዶስ ሂደት፣ በማስፋት እና በማጠናከር፣ በመላው ቤተክርስቲያን፣ እ.አ.አ በጥቅምት 10 ቀን 2021 በቅዱስ አባታችን የተጀመረው የመስማት እና የቤተክርስቲያን ማስተዋል” ሂደት ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ዶክተር ሩፊኒ “የሲኖዶሱ ሂደት በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ይቀጥላል እና በሚቀጥለው ዓመት ይጠናቀቃል” ሲሉ አረጋግጠዋል። ረቡዕ ጥቅምት 14/2016 ከሰአት በኋላ በጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ የጽሁፉ ውይይት የሚጀምረው በመልእክቱ ላይ ድምጽ ከተሰጠ በኋላ በጉባኤው ውስጥ ጣልቃ በመግባት እና በትንሽ ቡድኖች ውስጥ በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ነው፣ ድምጽ ለመስጠት ብቁ የሆኑ አባላት ብቻ ናቸው ጣልቃ መግባት የሚችሉት ሲሉ ተናግረዋል።

 

“ውይይቱ ነገ ጥዋት በትናንሽ ቡድኖች የሚቀጥል ሲሆን ነገ ከሰአት በኋላ በአጠቃላይ ጉባኤው ውስጥ የሚቀጥል ሲሆን ይህም በመጀመሪያ ለቀጣዩ የሲኖዶሳዊ ሂደት ዘዴዎች እና ደረጃዎች ላይ ሃሳቦችን ለማሰባሰብ ታስቦ ነበር” የተከናወነው ሲሉ ዶክተር ሩፊን ገልጸዋል።

ሆኖም “ለውይይት ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል አርብ ጠዋት የሚካሄደው ተጨማሪ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲዘጋጅ ተወስኗል፤ ይህም መጀመሪያ ለዕረፍት የተወሰነ ቀን ነበር። አርብ ጧት ለምእመናን በሚቀጥለው ዓመት ከስብሰባው በፊት ለቀጣዩ የሲኖዶሱ ሂደት የውሳኔ ሃሳቦችን ለማሰባሰብ ይተጋል። “ይህን ተጨማሪ ጉባኤ ለማቅረብ የተደረገው ውሳኔ በድምፅ ተወስኗል” በማለት የቫቲካን የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሩፊኒ የተናገሩ ሲሆን “በስብሰባው ላይ 347 ሰዎች ተገኝተዋል። ፍጹም አብላጫ ድምፅ 174፣ የድጋፍ ድምጽ የሰጡ ሲሆን፣ በድምጹ የተስማሙት 252 ናቸው፣ ተቃዋሚዎች 95 ናቸው። ስለዚህ ሃሳቡ ፀድቋል እና በጥንቅር ሰነድ ላይ የሚደረገው ውይይት ነገ ቀኑን ሙሉ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ካርዲናል ፕሬቮስት፡ የላቲን አሜሪካ ልምድ

አሜሪካዊው ካርዲናል ሮበርት ፍራንሲስ ፕሪቮስት፣ የላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት፣ በፔሩ የቺክላዮ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የቅዱስ አውጉስቲን ትእዛዝን ለመጀመሪያ ጊዜ አስታውሰዋል። ቅዱስ አውግስጢኖስ እና የተቀደሰው ሕይወት ለቤተክርስቲያን የሚያቀርቡት ብዙ ነገር እንዳላቸው እርግጠኛ ነበር። በፔሩ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሮም ከመጥራታቸው በፊት ለዘጠኝ ዓመታት ያህል በጳጳስነት ባገለገሉበት በሲኖዶስ ዓይነት ጉባኤዎች ከማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ ከአድባራት፣ ከገዳማዊያን/ገዳማዊያት እና ከካህናት የተውጣጡ ተወካዮች  ጉባኤዎች መካሄዳቸውን የገለጹ ሲሆን  ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋት ሕብረት እና አንድነት ነው ብለዋል፣ አክለውም ለድሆች እና ከቤተክርስቲያኗ ርቀው ላሉ ሰዎች ለመድረስ ነው የተጠራነው ብለዋል።

ከዚህ አንፃር የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት የማስተዋወቅ ሲኖዶሳዊ ዘይቤ በላቲን አሜሪካ የታወቀ ነው ብለዋል ካርዲናል። የአሁኑን ሲኖዶስ በተመለከተ ሁሉንም ማዳመጥን መማር፣ በመተማመን መነጋገር፣ ሁል ጊዜ እውነትን መፈለግ እና ጌታ ከቤተክርስቲያን የሚፈልገውን ለመረዳት መጣር አስፈላጊ መሆኑን ብፁዕ ካርዲናል አሳስበዋል። እንደማንኛውም የሰው ልጅ ልምድ ችግሮች መኖራቸው ተፈጥሯዊ ነው ሲሉም አክለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ንዛፓላይንጋ፡ በሰላም ስም

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የባንጉዊ ሊቀ ጳጳስ እና የሲኖዶስ ሴክሬታሪያት መደበኛ ምክር ቤት አባል የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ዲዩዶንኔ ንዛፓላይንጋ፣ በእነዚህ ጊዜያት በግጭት ከምትመሰቃቅለው በጦርነት ከምትታወቅ ሀገር እንደመጡ አበክረው ተናግረዋል።

ጦርነቱ ቀድሞውንም እንደነበረ ገልጿል “የሲኖዶሱን ጉዞ ፕሮቴስታንቶች እና ኮቶሊኮች አብረን ነበር የጀመርነው። በሰላማዊ መንገድ ትጥቃቸውን እንዲያስቀምጡ ተማጽነን በጋራ ልናናግራቸው ወደ አማጽያኑ ሄድን። ካርዲናሉ አክለው እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የባንጉዊን ካቴድራል ቅዱስ በር በከፈቱበት ወቅት፣ “በአገሪቱ ታላቅ ስሜት የተሞላበት ወቅት ነበር፣ ለዚህም ምስጋና ይግባውና ሁላችንም በተለይ ደግሞ አማፂያኑ የተደረገውን ጉዞ እና እያንዳንዱ ሰው ያበረከተውን አስተዋፅዖ ተረድተናል" ብሏል።

አሁን ባለው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ “እዚህ የመጣነው የብዙዎችን ሥቃይ በቦታው ካሉ ወንድሞችና እህቶች ጋር ለመካፈል ነው” በማለት በድጋሚ ተናግሯል። ምክንያቱም ብፁዕ ካርዲናል እንደተመለከቱት፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሰማበት ዝምታ፣ ከእኛ በፊት ያሉትን በትሕትና ማዳመጥ በሲኖዶስ ውስጥ አስፈላጊ ናቸው። በዚህ መንገድ ብቻ ነው የሌላውን ውበት ማወቅ፣ ዝምታን በመፍጠር ብቻ ሀብታቸውን መሰብሰብ እንችላለን። ከዚህ የጋራ መበልጸግ በመነሳት “የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ምን መሆን አለባት የሚለው ህልም” እውን ሊሆን ይችላል ሲሉ ንግግራቸውን ደምድሟል።

ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ፡ የሠራዊቱ አባላት ሰላምን ይፈልጋሉ

የዩናይትድ ስቴትስ የወታደራዊ አገልግሎት ሊቀ ጳጳስ ቲሞቲ ብሮሊዮ እና የዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት በቅድስት መንበር የዲፕሎማቲክ አገልግሎት ልምዳቸውን በማካፈል ጀመሩ። “እያንዳንዱ ሕያው የቤተክርስቲያን መገለጫ የክርስቶስ አካል በመሆን መገለጥ ነው” እና “ከተለያዩ ወጎች ብልጽግና መሳብ እንችላለን” ሲሉ ተናግሯል።

ከዚያም ስለ አስራ አምስት አመታት ያሕል በአሜሪካ ጦር ኃይሎች የሐዋርያዊ አገልገሎት ተግባራቸውን ማጋራት የጀመሩ ሲሆን በሲኖዶሱ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች የመደማመጥና የመነጋገር ልምድ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል። ብዙ ካዳመጥን ለሰዎች የበለጠ ክፍት የሆነ እና ለሰው ልጅ ክብር ያለው ዓለም ሊኖረን እንደሚችል ገልጿል። ብሮሊዮ የቅርብ ጊዜ ልምዳቸውን በመጥቀስ “ጦር ሠራዊቱ ከሁሉ የላቀ የሰላም ፍላጎት አለው” ምክንያቱም “ጦርነት ምን እንደሆነና ዋጋው ምን እንደሚመስል ስለሚገነዘቡ” ሲል አረጋግጧል። ከዚህ አንፃር በሲኖዶስ ውስጥ ያለው የመደማመጥ እና የውይይት ድባብ “ዓለም ለማየትና ምናልባትም የዓለምን ግጭቶች ለመፍታት ምሳሌ ሊሆን ይችላል” ሲሉ ተናግሯል።

ኖንተራህ፡ የአፍሪካ ሴቶች ጥበብ

ለአፍሪካ ሲኖዶስ ሂደት ምስክር በመሆን በጠቅላላ ጉባኤው ስራ ላይ እየተሳተፈ ያለው ጋናዊዋ የሃይማኖት ምሁር እና የዩኒቨርስቲ መምህር ዶክተር ኖራ ኮፎኖቴራ ኖንተራህ በመቀጠል ንግግር አድርገዋል። በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ምዕመን፣ እንደ ሴት እና እንደ አፍሪካዊ ሴት ድምጻችን እንደተሰማ ተሰምቶኛል ብለዋል፣ ይህም ቀደም ባሉት ጊዜያት ለአፍሪካውያን ሴቶች ጥበብ ድምጽ የማይሰጥ እና የማይጠቅም ነበር። “ወደ ሲኖዶስ ስመጣ ግን ተስፋ፣ ደስታ፣ ህልም፣ ጭንቀት፣ ዋይታ፣ ነገር ግን የአፍሪካ ሴቶች፣ የአህጉሪቱ ምእመናን ጽናት ይዤ ወደ ሲኖዶስ መጥችስለው” ስትል ተናግራለች። እናም እንዲያውም፣ መላው ቤተ ክርስቲያን፣ ይህ ሁልጊዜ በንግግሩ ማዕድ መሃል ላይ መቀመጥ አይችልም” ነበር እሁን ግን ይህ ሕያው ሆኗል ብለዋል።  

አክለውም “በእመቤታችን እናት ማርያም የእናትነት ሚና ተመስጬ የአፍሪካ ሴቶች ቤተክርስቲያንን ለሁሉ እናት መሆን እንዴት ለልጆቿ ሁሉ ባለራዕይ እናት መሆን እንደሚችሉ ማስተማር እንደሚችሉ አምናለሁ” ያሉ ሲሆን ዶ/ር ኖንተራህ በመቀጠል፣ “የእኔ እምነት ሲኖዶሳዊነት ለወንጌል እውነተኛ ምስክርነት መስጠት የምትችል ቤተ ክርስቲያን ለመኖር ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። ነገር ግን፣ እንደ ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን እንድንወጣ፣ በእኔ እምነት፣ በመንፈስ ውስጥ በውይይት ላይ የተመሠረተ እውነተኛና ትክክለኛና ጥልቅ አሠራር ሲኖረን ብቻ ነው። መንፈሱ ደግሞ ልዩነቶቻችንን እንድናከብር ይጋብዘናል እንጂ ለመደበቅ ሳይሆን አውቀን እንድናከብር ነው። ለዚሁ ጉዳይ አስፈላጊ የሆነው በእኔ እምነት በቤተ ክርስቲያን የትምህርት ዘርፍ ለምእመናን እንደ ነገረ መለኮት፣ ቀኖና ሕግ፣ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮዎች፣ የአመራር አገልግሎት የመሳሰሉ ተመራጭ አማራጭ መስጠት አለብን። ይህ የሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና አሠራር መሆን አለበት›› ብለዋል።

የነገረ መለኮት ምሁሯ የአፍሪካን ሴቶች ጥበብ በማስታወስ ለአፍሪካዊት እናት በተዘጋጀ መዝሙር አጠቃለዋል።

ሲኖዶሱ መንፈሳዊ ልምድ ነው።

ለካርዲናል ፕሬቮስት የቀረበ ጥያቄ ምእመናንን በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ላይ በመመካከር የማሳተፍ አቅምን ይዳሣል። የጳጳሳትን ጉዳይ በበላይነት የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ለካርዲናል ፕሬቮስት እንዳሉት፣ ምንም እንኳን ሂደቱ በተወሰነ ደረጃ የተያዘ ቢሆንም፣ በኤጲስ ቆጶስነት ሹመት ላይ በሚደረገው ምክክር ላይ ብዙ ምእመናን እና ሃይማኖተኞችን ለማካተት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፕርቮስት በሲኖዶሱ ስለተገለጸው ክፍፍል ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ከመለያየት ይልቅ የሐሳብ ልዩነት እንዳለ አስረድተዋል። ከአክብሮት ጋር መደማመጥ ነበር፣ ይህም ከተለያዩ ተሳታፊዎች አንጻር ወሳኝ ነበር። አንድነት ሁሌም የሚፈለግ እንጂ ይህ ማለት ደግሞ ወጥነት ማለት አይደለም። ሊቀ ጳጳስ ብሮሊዮ ወደፊት የበለጠ ተሳትፎን የማበረታታት አስፈላጊነት ተመልክቷል። ብፁዕ ካርዲናል ንዛፓላይንጋ አክለውም ልዩነቶች ሽባ የሚያደርጉን ነገሮች ሳይሆኑ የብልጽግና ምንጭ መሆናቸውን ገልጸው የተለያዩ አመለካከቶች ከጠላትነት ጋር የሚመሳሰሉ ሳይሆኑ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

ስለ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ማሻሻያ ለተነሳው ጥያቄ ብፁዕ ካርዲናል ፕርቮስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ብዙ ገፅታዎች እንዳሏት አስታውሰው ይህ ሲኖዶስ ግን ተቋማዊ ጉዳዮችን በቀጥታ የሚመለከት ሳይሆን ይልቁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ካሪዝማቲክ፣ መንፈሳዊ፣ ሰዋዊ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሲያተኩር መቆየቱን አስታውሰዋል።  ሁሉንም ሰው ለመቀበል በቂ እንደሆነ ተናግሯል።

26 October 2023, 15:42