ፈልግ

በቫቲካን በመካሄድ ላይ የሚገኘው 16ኛው የሲኖዶስ ጉባኤ በቫቲካን በመካሄድ ላይ የሚገኘው 16ኛው የሲኖዶስ ጉባኤ  (ANSA)

የሲኖዶሱ የተግባር ሠነድ ምዕራፍ ሁለት ቁ. አንድ ስለ ምን ይናገራል?

የሲኖዶሱ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች በዚህ ሳምንት ውስጥ በተግባር ሠነዱ ምዕራፍ ሁለት ቁጥር አንድ ላይ እየተወያዩበት ሲሆን የውይይታቸውን ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች እንደሚከተለው አቅርበነዋል:-

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

አንድነት፣ ተልዕኮ እና ተሳትፎ የሚሉት ርዕሦች ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቅድሚያ የምትሰጥባቸው ጉዳዮች ናቸው። "በአንድ አካል ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉን የሰውነት ክፍሎቹም ሥራ አንድ እንዳልሆነ ሁሉ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በእርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው የሰውነት ክፍሎች ነን" ሮሜ 12:4-5) ).

43. በመጀመርያው ምዕራፍ ከተመዘገቡት የሲኖዶሳዊ ጉዞ ፍሬዎች መካከል በተለይም በአህጉራዊ ጉባኤዎች ግንባር ቀደም ሆነው ለተገለጹት ሂደቶች ምስጋና ይግባውና፥ በጥቅምት ወር 2016 ዓ. ም. ለሲኖዶስ ጉባኤ የቀረቡ ሦስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ተለይተዋል። እነዚህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አንድ እርምጃ ወደፊት ለመራመድ እና በየደረጃው ባለው ሲኖዶሳዊ አካል እና በብዙ እይታ ለማደግ ራሷን የምትለካባቸው ተግዳሮቶች ናቸው። ከሥነ-መለኮት እና ከቀኖና ሕግ አንጻር እንዲሁም ከሐዋርያዊ እንክብካቤ እና መንፈሳዊነት አንጻር ሊታዩ ይገባቸዋል። ሀገረ ስብከት የሚያቅዱበትን መንገድ እና እያንዳንዱን የእግዚአብሔር ሕዝብ አባላት የዕለት ተዕለት ምርጫ እና የአኗኗር ዘይቤን ጥያቄ ውስጥ ያስገባሉ። እነርሱን ለማነጋገር እንደ ሕዝብ፣ ከሁሉም አባላት ጋር በኅብረት መጓዝን ስለሚጠይቅ በእውነትም ሲኖዶሳዊ ናቸው። ሦስቱ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የሲኖዶሱ ቁልፍ ቃላት፡ ማለትም ኅብረት፣ ተልዕኮ፣ ተሳትፎ ጋር በማያያዝ ይገለጻሉ። ይህ የሚደረገው ለአቀራረብ ቀላልነት እና ግልጽነት ሲባል ቢሆንም፣ ሦስቱን ቁልፍ ቃላት አንዱን ከሌላው ለይቶ እንደ ሦስት ቃላት አድርጎ ማቅረብ አደጋ አለው። ይልቁንም በሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ኅብረት፣ ተልዕኮ እና ተሳትፎ በግልጽ፣ አብረው የሚሄዱ እና የሚደጋገፉ ናቸው። ይህንን ውህደት ግምት ውስጥ በማስገባት ዘወትር አንድ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል።

44. ሦስቱ ቃላት የሚታዩበት የተለያዩ ቅደም ተከተሎች አሉ። ተልዕኮው ማዕከላዊ ቦታን የሚይዝ እና በመጀመሪያው ምዕራፍ ውስጥ በተፈጠሩት አገናኝ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ነው። በተለይም ኅብረት እና ተልዕኮ እርስ በርስ የተሳሰሩ እና አንዱ የሌላውን ገጽታ የሚያሳዩ ናቸው፣ አስቀድሞም በቀድሞው ር ዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አስተምህሮ፡- “ኅብረት እና ተልዕኮ እርስ በእርስ የተሳሰሩ ናቸው፣ እርስ በእርስ ይግባባሉ፣ እርስ በእርስ ይገናኛሉ። ኅብረት ሁለቱንም ማለትም ምንጭን እና የተልዕኮ ፍሬን ይወክላል። ኅብረት ለተልዕኮ ኃይልን በመጨመሩ ተልዕኮ በኅብረት ይፈጸማል” ማለታቸው ይታወሳል። ኅብረት በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ ያለውን አንድነትን የሚገልጽ በመሆኑ፥ ኅብረት ከሁለትዮሽ ግንዛቤ ወጥተን በኅብረት የምናከናውነው የወንጌል ምስክርነት ተዓማኒነት ቅድመ ሁኔታ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አጉልቶ ያሳያል። ይህ ግንዛቤ በወጣቶች፣ እምነት እና በማስተዋል ላይ የተመሠረተ ጥሪ በሚለው በ15ኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን ያስታውሰናል። ከዚሁ ጎን ለጎን የክርስቲያን ማኅበረሰብ የውስጥ አደረጃጀት፣ የሥራ ድርሻ እና የሃላፊነት ክፍፍል፣ ተቋማት እና የመዋቅሮች አስተዳደር፣ የተልዕኮ አቅጣጫ ብቸኛው በወንጌል የተመሠረተ መስፈርት እንደሆነ ግንዛቤ እያገኘ መጥቷል። ተሳትፎን መረዳት የሚቻለው ከኅብረት እና ከተልዕኮ ጋር በተገናኘ መንገድ ነው። በዚህም ምክንያት ከሌሎች ሁለት ቃላት ቀጥሎ የሚቀርብ መሆን አለበት። በአንድ በኩል ለአሠራር፣ ለደንቦች፣ ለአወቃቀሮች እና ለተቋማት ትኩረት መስጠት፥ ተልዕኮ በጊዜ ሂደት እንዲጠናከር እና ኅብረትን ከስሜታዊነት ነጻ በማድረግ ተጨባጭ አገላለጽ ይሰጣቸዋል። በሌላ በኩል ከአንድነት ይልቅ መበታተንን ወደሚያስከትሉ የግለሰብ መብት ጥያቄዎችን በመዳረግ በሰዎች መካከል ልዩነት እንዲገጠር ያደርጋል።

45. የጉባዔውን የውይይት ዝግጅት እና አወቃቀር ለማያያዝ በዚህ ክፍል መጨረሻ ላይ የሚገኙ አምስት የውይይት ርዕሦች ተዘጋጅተዋል። እነዚህ ርዕሦች በአህጉራዊ ውይይቶች ወቅት ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያን የሕይወት ገጽታዎች ጋር የተያያዙ ቢሆኑም አጋዥ አመለካከቶችን የያዙ ናቸው። በዚህ ላይ ሦስቱ አንቀጾች የሚዛመዱ እንጂ እንደማይገናኙ ትይዩ አንቀጾች ተወስደው መነበብ የለባቸውም። ይልቁንም ተመሳሳይ እውነታን የሚያበሩ የብርሃን ጮራዎች ናቸው። ይህ የቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ሕይወት ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመነሳት ያለማቋረጥ እርስ በእርስ እየተገናኙ እና እየተረዳዱ ለዕድገት የሚጋብዙ ናቸው።

ምዕራፍ 2 ቁ. 1. የሚያበራ ኅብረት፡- በግልጽ በሚታይ የቤተ ክርስቲያን ኅብረት “ከእግዚአብሔር እና ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር የአንድነት ምልክት እና መሣሪያ እንዴት መሆን እንችላለን?”

46. በሲኖዶሳዊ አገላለጽ ኅብረት ማለት፥ እንደ ቡድን አባልነት አንድ ላይ የመሰብሰብ የማኅበረሰብ አገላለጽ አይደለም። ነገር ግን ከሁሉም በላይ የቅድስት ሥላሴ አምላካዊ ስጦታ ነው። እንደዚሁም ሳይታክት "እኛ" ብለን የምንጠራውን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የመገንባት ተግባር ነው። በአህጉራዊ ጉባኤው ወቅት እንደተመከተው፥ “የሕዝቦች ብርሃን” የተሰኘው ሐዋርያዊ ሠነድ ኅብረትን “ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አንድነት” እና “የሰው ልጆች ሁሉ አንድነት” በማለት ይገልጸዋል። የቤተ ክርስቲያን ኅብረት እንድናድግ የተጠራንበት ጉዞ ነው፣ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ፍጽምናው እስክንደርስ ድረስ ነው” (ኤፌ 4፡ 13)

47. የቤተ ክርስቲያን ምድራዊ ጉዞ ኅብረትን የምትለማመድበት፣ የምትመግበው እና የምትታጽጽበት ጊዜ መሆኑን በስርዓተ አምልኮ እንገልጻለን። ሥርዓተ አምልኮ በእውነቱ “ምእመናን በሕይወታቸው ውስጥ የሚለማመዱበት እና ለሌሎችም የሚገልጹበት፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ምስጢር እና የእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ተፈጥሮ የሚገልጹበት ልዩ መንገድ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በጋራ የሚከናወን ሥርዓተ አምልኮ እና በተለይም ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚደረግ ጸሎት ቤተ ክርስቲያን ሥር ነቀል የሆነ አንድነቷን የምትለማመድበት ሲሆን ይህ ጸሎት በልዩ ልዩ ቋንቋዎች እና ሥርዓቶች አማካይነት የሚገልጽ መሠረታዊ የሲኖዶሳስ ነጥብ ነው። ከዚህ አንፃር፣ በአንዲት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የአምልኮ ሥርዓቶች በአህጉራዊ ጉባኤዎች ወቅት እንደታየው ጥበቃ ሊደረግላቸው እና ሊበረታቱ የሚገቡ እውነተኛ በረከቶች ናቸው።

48. የሲኖዶስ ጉባኤን እንደ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም እንደ ሕግ አውጭዎች ምክር ቤት አድርጎ መውሰድ አይችልም። ይልቁንም ከሥርዓተ አምልኮ ጉባኤ ጋር በማመሳሰል እንድንረዳው ተጠርተናል። የጥንት ትውፊት እንደሚነግረን፥ ሲኖዶስ ሲከበር በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ተጀምሮ በእምነት እንደሚቀጥል እና የቤተ ክርስቲያንን ኅብረት ለማረጋገጥ ወይም እንደገና ለመመሥረት የጋራ ውሳኔ ላይ ይደርሳል። በሲኖዶሳዊ ጉባኤ መካከል ኢየሱስ ክርስቶስ ይሠራል። እርሱ ታሪክን እና ዕለታዊ ሁነቶችን ይለውጣል። ቤተ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዴት መጓዝ እንዳለባት፥ የጋራ መግባባትን እንድታገኝ እና የሰው ልጅ ሁሉ ወደ ታላቅ አንድነት እንዲሸጋገር ለመርዳት መንፈስ ቅዱስ ተሰጠን። ቅዱስ ቃሉን፣ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እየሰማን በአንድነት መመላለስ ማለትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና የጋራ ስምምነትን በመፈለግ በአንድ መንፈስ በወልድ በኩል ወደ እግዚአብሔር አብ ዘንድ ምስጋናን ማቅረብ ይገባል። በሲኖዶስ ጉባኤ ወቅት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚሰበሰቡት ቃሉን በማዳመጥ፣ እርስ በእርሳቸው የሚደማመጡ፣ በማስተዋል መንፈስ ቅዱስን የሚገነዘቡ፣ የሰሙትን ለሌሎች የሚናገሩ እና መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን የኅብረት ጉዞ ብርሃን እንደሆነ ይገነዘባሉ።

49. ከዚህ አንጻር ሲኖዶሳዊ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን የማደራጀት ስልት ሳይሆን ልዩነትን ሳይሽሩ አንድነትን የማግኘት ልምድ ነው። ምክንያቱም እምነት በእግዚአብሔር አንድነት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ሃሳብ ሳያቋርጥ የኅብረት ወሰንን ለማስፋት የሚያግዝ አበረታች ኃይል አለው። ነገር ግን ከታሪካዊ ቅራኔዎች፣ ከወሰኖች እና ከቁስሎች ጋር የሚስማማ መሆን አለበት።

50. የሲኖዶሱ ሂደት የመጀመሪያው ጉዳይ መነሻው ይህ ነጥብ ላይ ነው። ተጨባጭነት ያላቸው ታሪካዊ እውነታች ኅብረትን መጠበቅ እና ማሳደግ በልዩነት ውስጥ አንድነት እንዳለ መቀበልን ይጠይቃል (1ቆሮ. 12)። ታሪክ መለያየትን ይፈጥራል። ይህም መፈወስ ያለባቸውን ቁስሎች እንዲድኑ እና ለእርቅ መንገድ እንዲፈጠሩ ያግዛል። በዚህ አውድ ውስጥ በቅዱስ ወንጌል ስም ጉድጓዶችን እና አጥሮችን ለማሸነፍ የትኛው ማሰሪያ መጠናከር እንዳለበት፣ የትኛውን መጠለያ እና ጥበቃ መገንባት እንደሚያስፈልግ እና ማንን መጠበቅ እንዳለብ እንገነዘባለን። የትኞቹ ክፍሎች ውጤታማ አይደሉም? ቀስ በቀስ ኅብረትን ወደ ፍፃሜው የሚደርሰው መቼ ነው? እነዚህ የንድፈ ሃሳብ ጥያቄዎች ይመስላሉ። ነገር ግን በመጀመሪያው ምዕራፍ በተመከሩት የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ተጨባጭ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በእርግጥም ሰዎችን እና ቡድኖችን ለመቀበል ያለን ፍላጎት ገደብ አለው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ያሳስበናል። ማንነታችንን ሳንነካ ከባሕሎች እና ሀይማኖቶች ጋር እንዴት መወያየት እንዳለብን እና በማኅበረሰቡ ለተገለሉት ሰዎች ድምጽ በመሆን ከኅብረት ጉዞ ማንም ወደ ውጭ እንዳይገፋ በድጋሚ ማረጋገጥ አለብን። አምስቱ የውውይት ገጾች ለእነዚህ ጥያቄዎች ቅድሚያን በመስጠት ከአምስት አጋዥ ዕይታዎች ጋር በማድረግ ለመቃኘት ይሞክራሉ።

11 October 2023, 17:38