ፈልግ

ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በትብብር ስምምነቱ ላይ ተገኝተዋል። ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በትብብር ስምምነቱ ላይ ተገኝተዋል።  (Vatican Media)

የካቶሊክ የጤና አጠባበቅ ተቋማት የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አራት የኢጣሊያ ካቶሊካዊ የጤና አጠባበቅ ተቋማት አቅማቸውን በማስተባበር የተራቀቁ የሕክምና ዘዴዎችን ለመጠቀም የሚረዳ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ተቋማቱ ስምምነቱን በቫቲካን የተፈራረሙት፥ በኅብረት እንዲሠሩ በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ላቀረቡት ጥሪ ምላሽ በመስጠት እንደሆነ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በጣሊያን የሚገኙ አራት ካቶሊካዊ የጤና አጠባበቅ ተቋማት ሃብታቸውን በምርምር ሥራ፣ በእንክብካቤ እና በሕክምና ስልጠና ዘርፎች ለማስተባበር የተስማሙት፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ በምስጠት ሲሆን፥ የስምምነቱ ዓላማ በተለያዩ በሽታዎች ለተጠቁ ሰዎች በሳይንስ የላቁ የሕክምና ዘዴዎችን በመጠቀም አገልግሎት ለማበርከት ያለመ እንደሆነ ታውቋል።

የትብብር ስምምነቱ ቫትካን ውስጥ የተፈረመው የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደነበር ተነግሯል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባምቢኖ ጄሱ የሕፃናት ሕክምና ሆስፒታል IRCCS፣ የአጎስቲኖ ጄሜሊ IRCCS ዩኒቨርሲቲ ፖሊ ክሊኒክ ፋውንዴሽን፣ የጄሜሊ ኢሶላ ቲቤሪና ሆስፒታል እና የቅዱስ ልብ ኢየሱስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አዳዲስ የጤና እንክብካቤ ሞዴሎችን ማዘጋጀት

በዕለቱ በቀረበው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት፥ አራቱ ካቶሊካዊ ተቋማት፥ ክርስቲያናዊ ተነሳሽነት ያላቸው የጤና አጠባበቅ ባህሪያትን የሚያሳዩ እሴቶችን በመለየት፥ ለካቶሊክ ተቋማት ጥያቄዎች እና ወቅታዊ የጤና አጠባበቅ ሁኔታ ተጨባጭ ምላሽ ለመስጠት አስበዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በፊርማው ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ቅድስት መንበር የትብብር ስምምነቱ መልካም ውጤት እንደሚያመጣ ያላትን ተስፋ ገልጸው፥ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕዝባዊ የሕግ አካላት የጤና ዘርፍ ጳጳሳዊ ኮሚሽን ተግባር ጋር በጥሩ ሁኔታ የሚስማማ መሆኑንም ተናግረዋል።

የትብብር ስምምነቱ ለሁሉም ሰዎች የተሻለ የጤና እንክብካቤን የሚያረጋገጡ ውጤቶችን እንደሚያመጣ ተስፋ እናደርጋለን" ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን አክለውም፥ በዩኒቨርሲቲ ትምህርት መስክ ውጤታማ እና አዳዲስ ሞዴሎችን ለወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቅም ለማስተዋወቅ በነደፈው ግብ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግሯል።

የትብብር ስምምነቱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ሚያዝያ 13/2023 ከሃይማኖት የማኅበራዊ ጤና ተቋማት (ARIS) አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ላቀረቡት ግብዣ ምላሽ ለመስጠት እንደሚገልግ ታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ ካቶሊካዊ የጤና አጠባበቅ ተቋማት የተመሠረቱባቸውን እሴቶች እንዲመሰክሩ፥ በብቁ እና ግልጽ አስተዳደር፣ ምርምርን፣ ፈጠራን እና ቁርጥኝነትን ከጠቅላላ ራዕያቸው ጋር በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች ለማሳየት የሚያስችል ድፍረት እንዲኖራቸው፥ ኅብረታቸውን በማስተባብረ ከማንኛውም የውድድር መንፈስ በመራቅ፥ ችሎታቸውን እና አቅምቅቸውን  አንድ እንዲያደርጉ ጋብዘዋል።

 

07 September 2023, 14:33