ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ እና የምስራቅ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ከያኔው የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሲሞን ፔሬዝ እና የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እ.አ.አ ሰኔ 8 2014 ር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ እና የምስራቅ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ከያኔው የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሲሞን ፔሬዝ እና የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እ.አ.አ ሰኔ 8 2014 

በቅድስት ሀገር ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ቅድስት መንበር በደስታ እንደምትቀበል አስታወቀች

የቫቲካን የግዛቶች ግንኙነት ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምን ለማስፈን በአዲስ መልክ በሚደረገው ጥረት ቅድስት መንበር ቅድሚያ የምትሰጣቸው ጉዳዮች እንደሆኑ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ቅድስት መንበር በቅድስት ሀገር ለሚደረገው ሰላም የሚደረገውን ማንኛውንም ተነሳሽነት በትክክል የምትቀበለው በእስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን መካከል እንዲሁም በአጠቃላይ በአካባቢው ያለው ሰላም መላውን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደሚጠቅም በፅኑ እምነት ስላላት ነው።
በዚሁ ጊዜ የቫቲካን የግዛቶች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግንኙነት ፀሐፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ማንኛውም የሰላም ተነሳሽነት የአካባቢውን ህዝብ መጠበቅ እና ለተለያዩ ወገኖች ህጋዊ ከለላዎችን ማቅረብ እንዳለበት አመላክተዋል።

የቅድስት መንበር ቀዳሚ ጉዳዮች

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት የቅድስት ሀገርን ጉዳይ በተመለከተ የቅድስት መንበር ቀዳሚ ጉዳዮች በተለይም ከኢየሱስ ሕይወት ጋር የተያያዙ ለ600 ዓመታት ለካቶሊክ መነኮሳት በአደራ የተሰጣቸው ቅዱሳን ቦታዎች በመኖራቸው እንዲሁም ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ የክርስቲያን ማህበረሰብ በአከባቢው በመኖራቸው ቅድስት መንበር በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ለሚነሱ ጉዳዮች ቅድሚያ ትሰጣለች ብለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ቅድስት መንበር “የሁለት ሀገራት መፍትሄ” የሚባለውን የሰላም ተነሳሽነት ለመደገፍ ያደረገችውን ጥረት ካስታወሱ በኋላ ፥ የኢየሩሳሌም ከተማ አስተዳደር ጥያቄን አጉልተው ገልጸዋል። በአይሁዶች፣ በሙስሊሞች እና በክርስቲያኖች እንደ ቅድስት ከተማ ተደርጋ እውቅና ያገኘችው እየሩሳሌም ፥ ሁሉም “በመከባበር እና በጋራ ጥቅም” አብረው የሚኖሩባት “የጋራ ቦታ” ልትሆን ትችላለች።

እየሩሳሌም ሁሉም በጋራ የሚኖርባት ከተማ

በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ሊቀ ጳጳስ ጋላገር እንዳሉት “በኢየሩሳሌም አንዳንድ የአይሁድ ጽንፈኞች በቅርቡ በክርስቲያኖች ላይ የፈጸሙትን ያለመቻቻል ድርጊትን በኢየሩሳሌም ማየት በእውነት በጣም ያሳዝናል” በማለት የእስራኤል መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም መንግሥታት ድርጊቱን እንዲያወገዙት ጠይቀዋል። አክለውም በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ጥቃት “ጉዳዩን ወደ ህግ በማምጣት እና ወደፊትም ወንድማማችነትን በማስተማር ቀድሞ መከላከል አለበት” ብሏል።
ኢየሩሳሌም ለተወሰነ ጊዜ ቅድስት መንበር ባፈለቀችው ሃሳብ “ዓለም አቀፍ ስምምነት ባለው ‘ልዩ ሕግ’ የተጠበቀች “የጋራ ከተማ” ተብላ እንድትታወቅ ጠይቀዋል።
ቅድስት መንበር የኢየሩሳሌምን ከተማ የሚያስተዳድር ማንኛውም ሰው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጡ መርሆችን እንዲከተል ጽኑ እምነት አላት ፤ ይህም “በአንድ አምላክ የሚያምኑ የሦስቱ ሃይማኖቶች አማኞች (ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች እና ሙስሊሞች) እኩል የሆኑ መብቶች እና ግዴታዎችን ጨምሮ ፥ ፍፁም የሆነ የሃይማኖት ነፃነት እና በቅዱሳን ቦታዎች የመገኘት እና የማምለክ ዋስትና እና ነባራዊ ሁኔታ አገዛዝ (Status Quo regime) የሚተገበርበት አከባቢ መሆን አለበት ብለዋል።

የውይይት አስፈላጊነት

በመጨረሻም ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በእስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን መካከል ቀጥተኛ ውይይት እንዲደረግ ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥሪ እንዲተገበር አሳስበዋል።
እ.አ.አ. በ2014 የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሺሞን ፔሬዝ እና የፍልስጤም ፕሬዝዳንት የሆኑት መሀሙድ አባስ በቫቲካን ያደረጉትን ስብሰባ አስታውሰው ፥ ሁለቱ መሪዎች ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጋር በመሆን የሰላም ተስፋን የሚወክል የወይራ ዛፍ በአትክልት ቦታዎች ከተከሉበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን አንድም ነገር እንዳልተተገበረ ጠቁመዋል።
ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ሲያጠቃልሉ “ነገር ግን ፥ የሁለቱም ሃገራት ፕሬዚዳንቶች ከባለስልጣኖቻቸው ጋር በመሆን የሰላም ፍሬዎችን ለማጨድ ተመልሰው እንዲመጡ በመጠባበቅ ያንን የወይራ ዛፍ ማጠጣታችንን እንቀጥላለን” ብለዋ።
 

20 September 2023, 14:17