ፈልግ

የአየር ንብረት ተሟጋቾች በሄግ የሚገኘውን አውራ ጎዳና በሰልፍ ሲዘጉት የአየር ንብረት ተሟጋቾች በሄግ የሚገኘውን አውራ ጎዳና በሰልፍ ሲዘጉት  (REUTERS)

ሲኖዶስ፥ በመጪው ጠቅላላ ሲኖዶስ ላይ የማይጠፋ አሻራ ለመተው እንደሚፈልግ ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚለው የሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ሁለተኛውን ክፍል ይፋ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት፥ የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መስከረም 23/2016 ዓ. ም. የሚጀመረውን ዘላቂ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ማክሰኞ መስከረም 8/2016 ዓ. ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፥  ለፍጥረት ጥበቃ አዲስ ቁርጠኝነት ያለው መሆኑን አስታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይፋ የሚያደርጉት አዲሱ "ውዳሴ ላንተ ይሁን” ሐዋርያዊ ሠነድ ቀድሞ ይፋ የሚሆነው ውጥኑ በመጪው 16ኛው የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደ መወያያ ርዕሥ የሚነሳውን የካርበን ልቀት ለማካካስ የያዛቸውን ምርጫዎች በማካተት እንደሆነ መግለጫው አስታውቋል።

ጋዜጣዊ መግለጫው በማከልም፥ ይህ እውነታ የ “ኤስኦኤስ ፕላኔት ፋውንዴሽን” ከ “ላይፍጌት” ቴክኒካል እውቀት ጋር በመተባበር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2019 ዓ. ም. የተካሄደው የሲኖዶስ ጉባኤ የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጿል።

ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መሰጠት

ሲኖዶሱ ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጠው ትኩረት ፖሊሲን ማውጣት ብቻ ሳይሆን የጋራ መኖሪያ ቤታችንን መጠበቅን በተመለከተ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን!” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ላይ ያስተማሩት ትምህርት ነጸብራቅ እንደሆነ ታውቋል።

ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ውስጥ እንደጻፉት፥ “ባለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ እንዳደረግነው በጋራ ቤታችን ያን ያህል ግፍና በደል ፈፅሞ አድርሰን አናውቅም። ነገር ግን ምድራችን እርሱ በወደደው ጊዜ የፈለገውን ትሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መሣሪያዎች እንድንሆን ተጠርተናል። እግዚአብሔርም ምድርን ከሰላሙ ጋር በውበት እና በሙላት ፈጥሯታል” ብለዋል።

የካርበን ልቀትን ለማካካስ የተመረጠው ፕሮጀክት በናይጄሪያ እና በኬንያ ውስጥ በተግባር እየተሠራበት እንደሆነ ሲታወቅ፥ ሥነ ምህዳራዊ ጥበቃን ፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎን እና በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ላሉ ግለሰቦች ሕይወት ተጨባጭ ድጋፍ እንደሚሆን ታውቋል። ዋና ግቡ ቀልጣፋ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎችን እና የውሃ ማጣሪያ ቴክኖሎጂዎችን ለቤተሰብ፣ ማኅበረሰቦች እና ተቋማት ማስተዋወቅ እንደሆነ ታውቋል።

በማኅበረሰቡ ለተገለሉ ሰዎች

ሲኖዶሱ፥ የጅምሩ ዋና ዓላማ ታዳሽ ያልሆኑ ባዮማስ እና ቅሪተ አካላትን ለምግብ ማብሰያ እና የውሃ ማጣሪያ ፍጆታን በእጅጉ ለመቀነስ ያለመ እንደሆነ ገልጿል። ይህ ሽግግር የአየር ብክለት መጠንን በእጅጉ እንደሚቀንስ እና በመተንፈሻ አካላት ጤና እና በተለይም እንደ ሴቶች እና ህጻናት ባሉ የተገለሉ ሕዝቦች ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ሁሉን አቀፍ አቀራረብ የአካባቢ ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸውን ማኅበረሰቦች አጠቃላይ ደህንነትን ያሻሽላል ተብሏል።

ዘላቂነት ያለውየ የገንዘብ ድጋፍ

የዚህ ፕሮጀክት ፈጠራ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎች ዘላቂነቱን የሚያሳይ መሆኑን ሲኖዶሱ የተመለከተ ሲሆን፥ ከካርቦን ክሬዲት ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ከላይ የተጠቀሱትን ቴክኖሎጂዎች በማምረት፣ በማሰራጨት እና በመጠገን ንቁ ተሳትፎ ያላቸውን የሀገር ውስጥ አጋሮችን ለመደገፍ እንደገና ኢንቨስት ይደረጋል ተብሏል።

የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በማጠቃለያው፥ አጀማመሩን “መንፈሳዊነትን ከተግባር ጋር በማዛመድ ፍጥረትን ለመጠበቅ የተወሰደውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” በማለት፥ በምድራችን ሰላም፣ ውበት እና የተሟላ ሕይወት እንዲሰፍን ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር እንድትመጣጠን የቀረቡትን ጥሪዎች በምሳሌነት አሳይቷል።

 

20 September 2023, 16:36