ፈልግ

የኡልማ ቤተሰብ የኡልማ ቤተሰብ 

በቅድስት መንበር የእስራኤል አምባሳደር "የኡልማ ቤተሰብ መስዋዕትነት'ለሁሉ ሰው ብርሃን' ይሆናል አሉ

በቅድስት መንበር የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ራፋኤል ሹትዝ እንደተናገሩት የኡልማ ቤተሰብ መስዋዕትነት ክፋትን በመቃወምማቸው ህይወታቸውን ያጡ የሰው ልጆች ባለውለታ መሆናቸውን በመጠቆም ፥ የከፈሉት መስዋዕትነት ለታሪክ ክለሳ መዋል እንደሌለበትም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የኡልማን ቤተሰብ ታሪክ ጊዜው የነበረበትን አውድ ሳይረዱ ሙሉ በሙሉ መረዳት አይቻልም።
በደቡብ ምሥራቅ ፖላንድ ውስጥ የምትገኘው ፥ በርካታ ትናንሽ መንደሮች ያሉባት እና በግብርና ሥራ ላይ የተሰማሩ ቤተሰቦች የሚኖሩባት ይህች ክልል ተለይታ የምትታወቅበት ነገር ብዙም ሀብት ባይኖራትም የአከባቢው ማህበረሰብ ከአይሁዶች ጋር እንደ ጓደኛ፣ ጎረቤትና አንዳንዴም እንደ ዘመዶች የሚኖሩባት ማኅበረሰብ ያለባት መንደር በመሆኗ ነው።

የማርኮዋ አይሁዶች

የማርኮዋ ከተማን በኡልማ ሙዚየም ውስጥ የሚታዩት ፎቶግራፎች ፣ ሰነዶች እና ቅርሶች እንደሚያሳዩት ብዙ አይሁዶችን በማህበራዊ ህይወት ትሥሥር ውስጥ ያዋሃደች ከተማ እንደሆነች ነው የሚገልጹት።
ሙዚየሙ አይሁዶችን ከናዚዎች ጭካኔ ለማስመለጥ ከለላ ለሆኑዋቸው እና ለረዷቸው ፖላንዳዊያን ሁሉ ክብር ይሰጣል።
ያ ታሪክ አይሁዶችን በሰገነት ላይ፣ በጓዳ ውስጥ ወይም በሌሎች ሚስጥራዊ ቦታዎች በመደበቅ ከአይሁዶች ጋር ለመወገን ከፍተኛ ዋጋ በከፈሉ የፖላንድ ቤተሰቦች ደም የተጻፈ የማይሻር ውርስ ትቷል።

የናዚ ህጎችን መጣስ

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በማርክዋ ከተማ ከነበሩት 120 አይሁዳውያን ነዋሪዎች መካከል 21 ያህሉ በዚህ የፖላንዳዊያኑ በጎ ሥራ ምክንያት ከሞት መትረፍ ችለዋል።
በመንደሩ ውስጥ ያሉ የሌሎች አይሁዳውያን ነዋሪዎች አሳዛኝ እጣ ፈንታ የአይሁድ ስቃይ ታሪክ ዋና አካል ሆኖ አልፏል።
ሆኖም የበርካታ ፖላንዳውያን ጀግንነት የሚገለጸው እ.አ.አ. ጥቅምት 1941 የወጡትን የናዚ ሕጎች በተቃራኒው በመቆም አይሁዳውያንን የሚረዳ ማንኛውም ሰው የሞት ቅጣት እንደሚፈፀምበት መደንገጉን እያወቁ በሠሩት የህይወት መስዋዕትነትን የሚያስከፍል ሥራ ነው።
እ.ኤ.አ. በ1942 መገባደጃ ላይ በማርክዋ ከተማ በአይሁድ ህዝቦች የተፈፀሙትን አስከፊ እልቂትን ተከትሎ ፥ እስራኤላዊያኑ የጎልድማን እና የዛል ቤተሰቦች ፖላንዳዊያኑን የኡልማ ቤተሰቦች መጠጊያ ጠየቁ።
ጆሴፍ አስቀድሞ አይሁዶችን በመደገፍ ይታወቅ ነበር። ሌላ የሰራቸው ሥራዎችም በሰፊው ይታወቃል ፥ ምንም እንኳን በኡልማ ቤት ውስጥ መደበቂያ ቦታው እንዲገኝ ያደረጋቸው ትክክለኛ ተግባራት በተወሰነ ደረጃ ያልተገለጹ ቢሆኑም።

የእስራኤል ኤምባሲ ድምፅ

በቅድስት መንበር የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ራፋኤል ሹትዝ ለቫቲካን ዜና እንደተናገሩት የኡልማ ቤተሰብ መስዋዕትነት ሁሉም ሰው ሊከተለው የሚገባው መንገድ ላይ ብርሃኑን አብርቷል ሲሉ ፥ ሰዎች የታሪክ ክለሳ ውስጥ እንዳይገቡም አስጠንቅቀዋል።
"የኡልማ ቤተሰብ መስዋዕትነት የሰው ልጅ በውስጡ ያለውን ሰብአዊ ርህራሄ የሚያሳየን ሲሆን ፥ ይህ ቤተሰብ እና ሌሎቹም ህይወታቸውን እስከሚያጡ ድረስ ክፋትን በመቃወማቸው በተለታዩ ሀገሮች ውስጥ ያሉ ትክክለኛ ሥራ የሚሰሩ ጻድቃንን ያስታውሰናል" ብለዋል አምባሳደር ሹትዝ። የእነርሱ መስዋዕትነት ሁላችንም ልንከተለው የሚገባን መንገድን ያበራልናል እንጂ ለማንኛውም የታሪክ ክለሳ ልንጠቀምበት አይገባም በማለትም አክለዋል።

የኡልማ ቤተሰብን የከዳው ማነው?

የኡልማ ቤተሰብን ማነው አሳልፎ የሰጠው የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ የማርኮዋ ነዋሪ የሆነ መረጃ ሰጪ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለ።
ይሁን እንጂ የታሪክ ምሁር የሆኑት ማትየስ ስዝፒትማ እ.አ.አ. በ1944 የጻፉት የመቋወሚያ ሰነዶች ጉዳዩን ወደ ሌላ ፍንጭ ይጠቁማሉ።
በኡልማ ሙዚየም የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው “የደንብ ልብሳቸውን ቀለም በመንተራስ ‘ሰማያዊ ፖሊስ’ ተብለው ከተሰየሙት ፖሊሶች መሃል አንዱ መኮንን በግል ዓላማ ተነሳስቶ ሁለቱ የአይሁድ ቤተሰቦች ተደብቀው የነበረበትን ቦታ በጀርመን ክፍለጦር ውስጥ ላሉ ባልደረቦቹ ገልጾ ሊሆን ይችላል” ተብሎ ተጠቁሟል።
 

11 September 2023, 14:09