ፈልግ

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን   (ANSA)

ካርዲናል ፓሮሊን፡ ስሎቫኪያ ዓለም እንዲለወጥ ልትረዳ ትችላላች ማለታቸው ተገለጸ!

በቅድስት መንበር የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የአውሮፓ ህብረት ሀገር በሆነችው ስሎቫኪያ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ጉብኝት እውን የሆነው በአከባቢው የጳጳሳት ጉባኤ ግብዣ መሰረት እንደ ሆነም ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.አ.አ ከመስከረም 14 እስከ 16/2023  ድረስ በስሎቫኪያ ጉብኝት የሚያደርጉት ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን ወደ አራት ከተሞች ማለትም ብራቲስላቫ ፣ ሻሺቲን ፣ ኮሺስ እና ክሎኮቾቭን ይጎበኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህ ጉብኝታቸው ከሶስት አስፈላጊ በዓላት ጋር ይገጣጠማል - የስሎቫክያ ሪፐብሊክ እና ቅድስት መንበር ከ30 አመት በፊት ያደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ይታደሳል፣ ቅዱሳን ቄሬሊዮስ እና መቶድየስ ወደ ሀገሩ የገቡበት 1,160ኛው የምስረታ በአል እና አምላክ የለሽ በሆኑ እና የክርስትና እምነት ጠል በሆኑ ሰዎች ሁለት የስሎቫክ ዜጎች ተደብድበው የሰማዕታትነት ዋጋ የከፈሉ ሰማዕታት እ.አ.አ በ2003 ዓ.ም በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሰማዕትነት ማዕረግ የተቀበሉበት መታሰቢያ የሚከበርበት እለትን አስመልክተው ነበር ወደ እዚያ እንዲያቀኑ የተጋበዙት። 

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብጽዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር የሚከተልውን ቃልለ ምልልስ ያደርጉ ሲሆን በቃለ ምልልሳቸው ይህ ጉብኝት ለአለፉት ሦስት ዓመታት ያህል የታቀደ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን  በተለያዩ ምክንያቶች ለሌላ ጊዜ ሲተላለፍ እንደ ቆየ እና አሁን ግን እውን የሆነ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ገልጿል። በቅድስት መንበር እና በስሎቫክ ሪፐብሊክ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደገና የጀመረበት 30ኛ ዓመት፣ የቅዱሳን ወንድማማቾች ቄሬሊዮስ እና መቶድየስ በታላቋ መንፈሳዊ ቅንዓት የዛሬ  1160 አመት በፊት ወደ ሞራቪያ ስሎቫኪያ የመጡበት እና ሁለት የስሎቫኪያ ሰምዕታት ስመተ ሰማዕታትነት የተቀበሉበት 20ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ ለመገኘት አቅደው ወደ እዚያው እንደ ሚጓዙ ገልጸው ነበር።

በዚሁ ወር እ.አ.አ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 15/2021 ዓ.ም የተካሄደውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ አገሪቱ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሁለተኛ ዓመት ይከበራል። ይህ ቀን የተመረጠበት ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ይህ ነው ሲሉ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ገልጿል።

የሐዋርያዊ ጉብኝቱ ዋና ዓላማዎቹም በእዚያ በስሎቫኪያ የሚገኙ ምዕመናን እምነት ለመካፈል፣ ሕብረታቸውን ለማጠናከር፣ ብፁዕ አባታችን በሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ያስተላለፉትን መልእክት እንደገና ማስጀመር፣ በቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ላይ መሳተፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ለእመቤታችን በጋራ መጸለይ ነው። ለሀገር እና ለሊቀ ጳጳሱ ልብ ቅርብ ለሆኑት ታላቅ ዓላማዎች በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ ለሰላም በጋራ ለመጸልይ ነው ወደ እዚያው የምጓዘው ብለዋል።

በጉዞው ወቅት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የውይይት ጊዜያትን እና ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር በቅድስት መንበር እና በስሎቫኪያ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደ ማህበራዊ ፍትህ፣ አብሮነት፣ ወንድማማችነት እና ሰላም ያሉ እሴቶችን ማጎልበት ውይይት እንደ ምያደርጉ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አክለው ገልጿል።

ስሎቫኪያ ትንሽ አገር ናት ለዓለም ምን ሊሰጥ ይችላል? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ሲመልሱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ ወደ ሞንጎሊያ ያደረጉት ጉዞ ራሳችንን በቁጥር ወይም በእውነታው መጠን መገደብ የለብንም የምለውን ጠቃሚነቱንና ተጽኖውን ለመገምገም በግልፅ ያሳየን ይመስላል በማለት ምላሽ መስጠት የጀመሩ ሲሆን የስሎቫኪያም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው፣ መጠነኛ አገር ብትሆንም መጠኑ ከበለጸገ ታሪኳ፣ ከባህሉ፣ ከክርስቲያናዊ ቅርሶቿ፣ ለመንፈሳዊ እሴቶቿ ካለው ቁርጠኝነት እና መከባበርና ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ አብሮ መኖርን ከማስተዋወቅ ጋር ተያይዞ ለአለም እና ለለውጡ ትልቅ አስተዋፅኦ ከማድረግ አያግዳትም ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

ቅዱሳን ቄሬሊዮስ እና መቶድየስ የሀገሪቷን ባሕል መላበሳቸው እና የሲኖዶሳዊነት ታላቅ ምሳሌ ናቸው። በዛሬው ጊዜ መልእክታቸውን እንዴት ማካተት እንችላለን? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ምላሽ የሰጡ ሲሆን 'የስላቭ ሕዝቦች አባቶች' በመባል የሚታወቁት የቅዱሳን ቄሬሊዮስ እና መቶድየስ ተልእኮ እና የእነርሱ የመጀመሪያው ደቀመዝሙር የነበረው ቅዱስ ጎራዝድ በኤጲስ ቆጶስነት የቅዱስ መቶድየስ ተከታይ ክርስትና በተሳካ ሁኔታ እንዴት እንደሚዋሃድ አስደናቂ ምስክርነት ይሰጠናል። የተለያዩ ባህሎች - በትክክል የሚታወቅ ጽንሰ-ሐሳብ እንደ 'መፍጠር' ሳይሆን ከባሕል ጋር የተዋሀደ ክርስትና እንዴት ማስፋፋት እንደ ሚችላ ያስተምሩናል ብሏል።

ለዘመናችን ከእንዲህ ዓይነቱ ምስክርነት የሚወጡት አግባብነት ያላቸው ጉዳዮች የሚመስሉኝ ለምሳሌ የአንድነት ልዩነትን ማድነቅ፣ መከባበር፣ በባህል እና በሃይማኖቶች መካከል ያለ ውይይት አስፈላጊነት... ወዘተ የመሳሰሉትን ለመገንባት አስፈላጊ ናቸው በማለት ምላሽ የሰጡት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ነገር ግን የእምነታችንን ይዘት ወደ ዘመናችን እና ከሁሉም በላይ ለወጣቱ ትውልዶች ተደራሽ በሆነ ቋንቋ ለመተርጎም ከሚደረገው ጥረት ሁሉ በላይ ይህ ሁሉ እርስ በርሳችን ለመደማመጥ ትልቅ አቅምን ይጠይቃል ይህም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያስቀመጡልን የሲኖዶሳዊ መንገድ ነው ሲሉ አጽነቶ ሰጥተው ተንግሯል።

በስሎቫክያ ብዙ ሕያው፣ ጸሎተኛ፣ አማናዊ ጉባኤያት፣ እምነታቸውን የሚያከብሩ እና የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት በመመገብ፣ በምስጢረ ቁርባን ውስጥ መሳተፍ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ለድንግል ማርያም መሰጠት የእዚህ ሕዝብ ባሕል እና እምነት አካል ነው ያሉት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን እነዚህ ነገሮች በስሎቫክ ሕዝቦች ሃይማኖታዊ ሂደት ውስጥ ልዩ ቦታ አላቸው ሲሉ ተናግሯል።

እናም ሁሉም እንዲሳተፉ፣ ከጌታ ጋር ያለንን ጥብቅ ግንኙነት እንድናጠናክር፣ ለእርሱ ያለንን ፍቅር እና ጥልቅ ምክንያቶችን እንድናገኝ ግብዣዬን አቀርባለሁ። ቤተክርስቲያን በእውነት ለሁሉም ብርሃን እንድትሆን እና ህብረተሰቡን በወንጌል እርሾ እንድትለውጥ በአለም ላለው ቁርጠኝነት ፣ለጎረቤታችን በጎ አድራጎት ፣ማህበራዊ ፍትህ እና ለሌሎች አገልግሎት መስጠት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው ካሉ በኋላ ካርዲናል ፓሮሊን መልዕክታቸውን አጠናቋል።

15 September 2023, 11:58