ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር  

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር የተባበሩት መንግስታት የልማት ግቦች የሰውን ልጅ ማዕከል ማድረግ አላባቸው አሉ!

ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት የእያንዳንዱን ሰው ክብር እንዲጠብቁ እና በዘመናችን ያሉ ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ለመፍታት በጋራ እንዲሰሩ አሳሰቡ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቫቲካን ከተለያዩ የውጭ አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በኒዮርክ በመካሄድ ላይ ባለው የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት  ከፍተኛ የፖለቲካ መድረክ ላይ ተገኝተዋል። እ.አ.አ የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ማደስ ላይ ያተኮረው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አስተባባሪነት እ.አ.አ ከመስከረም 18 እስከ 19 ተካሂዷል።

ሊቀ ጳጳሱ በመግለጫቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ የ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳ መቀበላቸውን “የተስፋ ምልክት” በማለት የገለጹበትን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.ኤ.አ. በ2015 ያደረጉትን ንግግር አስታውሰዋል።

በዚያን ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዲያው ለይስሙላ ብቻ ቢሮክራሲያዊ በሆነ መልኩ የተቀመጡት "ረጅም ጥሩ ሀሳቦችን - ግቦችን ፣ ዓላማዎችን እና አሀዞችን (ስታቲስቲክስን) በማዘጋጀት በቢሮክራሲያዊ ልምምድ ውስጥ ያለ ይዘት" የመቆየት አደጋን አስጠንቅቀዋል ።

ይልቁንም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕያው ሆኖ እንዲቀጥልና “ነገሮችን እንዲከሰት የሚያደርግ እና ሕይወትን የሚቀይር” ተስፋ መስጠት አለበት ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ።

ተጠቅሞ የመጣል ባህል አደጋዎች

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት እድገትን እንዲያፋጥኑ አሳስበዋል “ዓለምን ወደ ዘላቂ እና ቋሚ በሆነ መንገድ” ለማሸጋገር ዓለም አቀፋዊ ትብብር አስፈላጊ ነው ብሏል።

የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ስብሰባ “የዘመናችንን ታላላቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት ተጨባጭ እርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ የረቂቅ መግለጫዎች” መድረክ ሆኖ ማገልገል የለበትም ብለዋል ።

ሊቀ ጳጳሱ ጦርነትና ግጭት፣ ድህነትና ረሃብ፣ ዓመፅ፣ ማኅበራዊ መገለል፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ መራቆት እና የተንሰራፋውን ‘ተጠቅሞ የመጣል ባህል’ ተግዳሮቶች አጽንኦት ሰጥተው ተናግሯል።

“ሰዎች በተለይ ድሆች ወይም አካል ጉዳተኞች ሲሆኑ ለመንከባከብ እና ለመከባበር እንደ ትልቅ እሴት የማይታዩበት” እና “ገና የማይጠቅም” - እንደ ፅንስ ልጅ ወይም “አይጠቅምም” እየተባሉ የሚጣሉበትን የመወርወር ባህል ማስወገድ እንደ ሚገባ ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር አስጠንቅቋል።

የሰውን ልጅ በህብረተሰቡ ማዕከል ማስቀመጥ

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር እንዳሉት እ.አ.አ የ2030 አጀንዳ ትግበራ በዋናነት የሰው ልጅን ማዕከል ያደረገ፣ በጋራ ጥቅም ላይ ያተኮረ እና በፍትህ፣ በአብሮነት እና በሥነ ምግባራዊ መርሆች ላይ የተመሰረተ አዲስ የእድገት ሞዴል ማምጣት ነው፣ ለእዚህም የጋራ ኃላፊነት አለብን ብሏል።

ሊቀ ጳጳሱ በማጠቃለያው የመንግስታቱ ድርጅት ዘላቂ የልማ መረዓ ግብሮች ስብሰባ ስኬት የሚወሰነው ሀገሮች ለባለብዙ ወገንተኝነት ባላቸው እውነተኛ ቁርጠኝነት ላይ ነው ሲሉ የተናገሩ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት የእያንዳንዱ ሰው ተፈጥሯዊ ክብር የሚከበርበት፣ የድሆች እና በተጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ወገኖች ፍላጎቶች የሚሟሉበት እና ከአካባቢው ጋር የተጣጣመ ግንኙነት ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመጣ ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

21 September 2023, 13:17