ፈልግ

2023.08.22 Mongolia, Ulaanbaatar, Ulan Bator, Sukhbaatar Statue

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በሞንጎሊያ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ የክቶሊክ ምዕመናንን የምያቅፍ ጉዞ እንደ ሚሆን ይጠበቃል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ማቴዮ ቡሩኒ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ሞንጎሊያ የምያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ በተመለከተ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በቅርቡ ቅዱስነታቸው በኢሲያ አህጉር ውስጥ የምትገኘውን ሞንጎሊያን በመጎብኘት የመጀመሪያው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይሆናሉ ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ማክሰኞ ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ማትዮ ብሩኒ ከመጪው ከነሐሴ 25 እስከ ነሐሴ 29/2015 ድረስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ሞንጎሊያ የምያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ በተመለከተ በዝርዝር ተናግሯል። ይህ የቅዱስ አባታችን 43ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ቅዱስነታቸው የጎብኟቸው አገራት በአጠቃላይ 61 ሀገሮች ናቸው።  

የሞንጎሊያ አቀማመጥ በዩክሬን ጦርነት በተገለጸው ታሪካዊ ወቅት ጂኦፖለቲካዊ ተምሳሌታዊ ነው። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሦስት ቀናት የጉዞ ቆይታቸው ከሚያቀርቧቸው አምስት ንግግሮች መካከል የተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማዊ እና ማህበራዊ እውነታዎችን ሳይጎበኙ አይቀርም ብሏል።

የጉዞው ሁሉ እምብርት ግን በቁጥር ትንሽ ወይም ሕዳጥያን ከሆኑ የካቶሊክ ማህበረሰብ ጋር መገናኘት ይሆናል፣ ወደ 1,500 የሚጠጉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ብቻ ናቸው በሞንጎሊያ የሚገኙት። "ጳጳሱ በዋናነት እነሱን ለማነጋገር ወደ ሞንጎሊያ ይሄዳሉ፣ የማበረታቻ ቃላትን ያቀርባሉ እና በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ጠቃሚ አስተዋፅኦ ላለው ለዚህ ውብ እውነታ ተስፋ ያደርጋሉ" ብለዋል አቶ ማቴዮ ብሩኒ።

የሞንጎሊያ ቤተክርስቲያን በ 4 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የመጀመሪያው ጳጳስ በተሾመበት ጊዜ የሞንጎሊያ ግዛት የቻይናን ክፍል ሲጨም፣ ከዚያም በኮሚኒስት አምባገነናዊ አገዛዝ ዓመታት ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋ ድረስ ለብዙ መቶ ዘመናት የክርስቲያኖች በአካባቢው መኖር እየቀነሰ ሄደ።

እ.አ.አ ከ1992 ጀምሮ ቤተክርስቲያን 'እንደገና ገብታ' እና 'በእዚያው አገር እንድትቆይ ተጋበዘች፥ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ በሚስዮናውያን ታላቅ ስራ፣ በመጀመሪያ እና በዋናነት በኮንሶላታ ሚስዮናውያን፣ በማሕበሩ ታላቅ ሥራ ቤተክርስቲያኑ እንደ ገና ብርታት አገኘች። የመጀመሪያው እና ብቸኛው የሞንጎሊያው ካርዲናል ጆርጂዮ ማሬንጎ፣ የኡላንባታር ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ፣ ባለፈው ዓመት ስመተ ካርዲናልነትን መቀበላቸው ይታወሳል።

ከካቶሊክ ማህበረሰብ እና ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር መገናኘት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በነሐሴ 28/2015 ቀን እስቴፔ አሬና በሚባለው ሥፍራ የሚመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ በጉዞው ላይ በተለይም የቤተክርስቲያንን ታሪካዊ ዳራ እና የቤተክርስቲያንን ትንሽ ነገር ግን በማህበራዊ መስክ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት ረገድ ማዕከላዊ ቦታ አለው - ስለዚህም በቅድስት መንበር እና በመንጎሊያ መንግሥት  መካከል የተደረገ ስምምነት ለክርስቲያን ማሕበረሰቡ ጥበቃና መብት የሚሰጥ እንደ ሆነም ተገልጿል።

በሞንጎሊያ የሚኖሩት 1,500 የካቶሊክ ምዕመናን አማኞች 90% የሚሆኑት በዋና ከተማው የሚኖሩ፣ ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ታይላንድ፣ ካዛክስታን፣ ኪርጊስታን፣ አዘርባጃን እና ቬትናምን ጨምሮ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ አማኞችን ይቀላቀላሉ።

እንዲሁም እሁድ እለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሻማኒዝም (በሰሜናዊ አውሮፓ እና በሳይቤሪያ በሚገኙ የአገሬው ቀደምት ተወላጆች የሚተገበር ሃይማኖት ሲሆን በማይታየው የአማልክት፣ የአጋንንት እና የአያት መናፍስት ዓለም በማመን የሚታወቀው ለሻማኖች ብቻ ምላሽ የሚሰጥ እምነት ነው)፣ የሺንቶኢዝም (የጃፓን ጥንታዊው ቀደምት ተወላጅ ሃይማኖት ሲሆን መደበኛ ዶግማ የሌለው፣ በተፈጥሮ መናፍስት እና ቅድመ አያቶች ማክበር ተለይቶ ይታወቃል። የሰውን እጣ ፈንታ በሚቆጣጠረው ከተፈጥሮ በላይ በሆነ ኃይል ወይም ኃይሎች ላይ ጠንካራ እምነት ያለው ሐይማኖት ነው)፣ የቡድሂዝም (የምስራቅ እና የመካከለኛው እስያ ሃይማኖት ከሲዳራታ ጋውታማ ትምህርት ተነስቶ በማደግ ላይ ያለ ሀይማኖት በህይወት ውስጥ ስቃይ መኖሩን እና አንድ ሰው ጥበብን፣ በጎነትን እና ትኩረትን በማጎልበት ከእሱ ነፃ መውጣት እንደሚቻል የምያስተምር ሐይማኖት ነው)  የእስልምና ፣ የአይሁድ እምነት ፣ የሂንዱይዝም እና የሌሎች የእምነት ተቋማት ተወካዮች የሚሳተፉበት ሥነ-መለኮታዊ እና ሃይማኖታዊ ዝግጅቶችን ይመራሉ ።

ዝግጅቱ ለሰላማዊ አብሮ የመኖር ጥሪ ምልእክት ያቀርባል፣ አቶ ማትዮ ብሩኒ አፅንዖት ሰጥተው እደገለጹት ከሆነ  የሞንጎሊያን ህዝብ ለአስርተ አመታት ያሳወቁት መልካም እሴት እንደ ሆነ ገልጸው በስብሰባው ላይ የመንግስት ታዛቢዎች እና የዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች ይገኛሉ ሲሉ ተናግሯል።

በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት የግል ስብሰባዎች እንዳልታቀዱ ገልጸው የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ሕብረት እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚካሄደው ዝግጅት በሞንጎሊያ ውስጥ አብላጫ ሃይማኖት ተከታይ ያለው ቡድሂስቶችን ጨምሮ ሁሉም የሃይማኖት ቡድኖች እንደሚሳተፉ አስረድተዋል ።

የጎረቤት አገር የሆነችውን ቻይና በተመለከተ በተቻለ መጠን ማጣቀሻዎችን ያቀረቡ ሲሆን የፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር እሑድ ነሐሴ 21/2015 ላይ ከመልአክ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተናግረውት የነበረውን ቃል በማስታወስ "ጳጳሱ እሁድ እለት በጣም ግልጽ የሆነ መልእክት አስተላልፈው ነበር፣ ወደ ሞንጎሊያ እየሄዱ መሆናቸውን ተናግሯል፣ እርሳቸው በደስታ እና በታላቅ አክብሮት ከሁሉም ጋር ለመገናኘት እንደ ጓጉ ተናግረው ነበር” ብሏል። ከሰዎች ጋር ለመገናኘት በጣም ይፈልጋሉ። ሌላ ምንም አልጨምርም። ጉዞው ወደ ሞንጎሊያ ነው ካሉ በኋላ መግለጫቸውን አጠንቀዋል።

 

30 August 2023, 11:48