ፈልግ

በሞንጎሊያ ዋና ከተማ ኡላንባታር የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ካቴድራል በሞንጎሊያ ዋና ከተማ ኡላንባታር የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ካቴድራል  

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ ለቤተክርስቲያን የምዕመናን ቁጥር መብዛት ብቻውን እንደ መስፈርት አይታይም አሉ

የቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ጥቅስ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ወደ ሞንጎሊያ የሚያደርጉትን ጉዞ ምክንያቶች ለመረዳት ይረዳናል። ጳጳሱ በአውሮፓ እና በእስያ መካከል በምትገኘውን ሞንጎሊያ ፥ በኡላንባታር ከተማ ከነሃሴ 25 እስከ 29 2015 ዓ.ም ድረስ ሃዋሪያዊ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ለብዙ ጊዜ ‘ሲናፍቁት’ የነበረውን እና ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሚስዮናውያን በሃገሪቷ የክርስቲያን ማህበረሰብን ካቋቋሙ በኋላ ሃዋሪያዊ ጉብኝት ሊያደርጉ አስበው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈጸሙ ዕቅዶች ውስጥ ቢካተቱም ፥ ብፁዕነታቸው በዘመናቸው ሊያሳኩት ወደ ሞንጎሊያ ሊያቀኑ ነው። በእስያ እምብርት የቅዱስ ጴጥሮስን ተተኪ የምትቀበለው ቤተክርስቲያን “በቁጥር ትንሽ ነገር ግን በእምነት ህያው እና በበጎ አድራጎት ታላቅ” የሆነች ቤተክርስቲያን ነች። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የአገሪቱን 1,500 ካቶሊኮች ብቻ ሳይሆን የሚያገኙት ሁሉንም "ክቡር" እና "ጥበበኛ" የሆኑትን የሞንጎሊያውያን ህዝቦችን ከታላቁ የቡድሂስት ባህላቸው ጋር ያገኟቸዋል።
ጳጳሱ ለምን ወደ ሞንጎሊያ ይሄዳሉ? ለምንድነው ለአምስት ቀናት በሚቆየው መርሃ ግብር (የሁለት ቀን ጉዞ እና ሶስት ቀናትን በጉብኝት) ይህን አነስተኛ ቁጥር የሆነውን የካቶሊኮች ማህበረሰብን ለመጎብኘት የሚውለው? ከሩሲያ ፌዴሬሽን እና ከቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ ጋር ወደምትዋሰነው ሀገር ጉዞ ስለሆነ የሚሄዱት “ጂኦፖሊቲካዊ” እንድምታ ይኖረው ይሆን? በእውነቱ ከሆነ ወደ እስያ ዳርቻዎች ለመጓዝ ያለው ተነሳሽነት ምንም “ጂኦፖለቲካዊ” አንድምታ የለውም ፥ እንዲሁም በእርግጠኝነት የጆርጅ ማሪዮ ቤርጎሊዮ ጵጵስና መገለጫ ባህሪም አይደለም።
እ.አ.አ. ህዳር 30 ቀን 1970 ዕለተ ሰኞ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ወደ ሚገኙት የሳሞአን ደሴቶች ላይ ረጅም ጉዞ አድርገው በስፍራው ደረሱ። በኡፑሉ ደሴት ሰሜናዊ ምዕራብ የባሕር ጠረፍ ላይ በምትገኘው ሉሉሞኤጋ ቱዋይ መንደር ውስጥ የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ሲደረግ ፥ በዚያን ጊዜ ሊቃነ ጳጳሳት ይጠቀሙበት የነበረውን “እኛ” የሚለውን ግርማ ሞገሳዊ ቃል ወደ ጎን በመተው “የጉዞ ፍላጎት ወይም የግል ጥቅም አይደለም ወደ እናንተ የሳበኝ ፥ እኔ የመጣሁት ሁላችንም ወንድሞችና እህቶች ስለሆንን ነው ፥ ወይም በሌላ አነጋገር እናንተ ወንድ እና ሴት ልጆቼ ናችሁ እናም እኔ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቤተሰብ አባት እንደመሆኔ መጠን እያንዳንዱን ሰው እኩል የመውደድ ግዴታ እንዳለብኝ ማሳየት ተገቢ ነው። ‘ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን’ የሚለውን ትርጉም ታውቃላችሁ? ይህ ማለት ቤተክርስቲያን ለዓለም ሁሉ ነች ፥ እሷ ለሁሉም ነች፣ የትም ቦታ እንግዳ አይደለችም ማለት ነው። እያንዳንዱ የሰው ልጅ አገሩ፣ ዘሩ፣ ዕድሜው፣ ትምህርት ቤቱ ምንም ይሁን ምን በቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ ይኖረዋል” በማለት ተናግረዋል።
ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም የሚሆን ቦታ አላት። ቅድሚያ የሚሰጠው ለቁጥር ሳይሆን ማንም ባዕድ የማይሆንባት ቤተ ክርስቲያን የትኛውንም ቋንቋ፣ ባህል፣ ሕዝብ ወይም ብሔር ይኑረው ሁሉም እኩል ነው። ይህንንም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በሊዝበን “ፓራ ቶዶስ” በማለት ተናግረውታል ፤ ይህም ‘ቤተክርስቲያን ለሁሉም ናት’ እንደማለት ነው። የዘንድሮው የዓለም ወጣቶች ቀን ተከብሮ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሮማው ጳጳስ ወደ መንገድ ተመልሰው በሞንጎሊያ ላሉ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው “እንደ የሁሉም የሰው ልጅ ወንድምነቴ በመካከላችሁ ለመገኘት በመምጣቴ ደስተኛ ነኝ” ለማለት ዳግመኛ ሃዋሪያዊ ጉዞ ሊያደርጉ ዝግጅት ላይ ናቸው።
 

29 August 2023, 11:30