ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና በቅድስት መንበር የሞንጎሊያ አምባሳደር ወይዘሮ ጄረልማ ዳቫሱረን በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና በቅድስት መንበር የሞንጎሊያ አምባሳደር ወይዘሮ ጄረልማ ዳቫሱረን በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

የሞንጎሊያ አምባሳደር የጳጳሱ ጉብኝት በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ያበረታታል አሉ!

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ አገራቸው ሞንጎሊያ መሄድ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት በቅድስት መንበር የሞንጎሊያ አምባሳደር ወይዘሮ ጄረልማ ዳቫሱረን ቅዱስነታቸው ታሪካዊ ጉብኝት በማድረግ ሞንጎሊያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳየት እና የሃይማኖቶች ውይይት እና ልዩ ልዩ እምነቶችን መከባበርን እንደሚያበረታታ ተናግሯል።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመንጎልያ የምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት "በአካባቢያችን እና በአለም ላይ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ትልቅ አስተዋፅዖ አለው" ብሏል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በቅድስት መንበር የሞንጎሊያ አምባሳደር ወይዘሮ ጀረልማ ዳቫሱረን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅድስት መንበር እና በሞንጎሊያ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ ከ30 ዓመታት በኋላ እ.አ.አ በታህሳስ 2022 ነበር የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት።

የሞንጎሊያ ቡዲስቶች የልዑካን ቡድን ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ይፋዊ ጉብኝት በቫቲካን ባደረጉበት ወቅት እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አቀባበል የተደረገለት ይህ በዓል በቫቲካን ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል።

አምባሳደር ዳቫሱረን ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ስለምተገኘው ስለ ሀገራቸው ደስታ ተናግረዋል።

በሞንጎሊያ ምድር ላይ እግራቸውን የምያሳርፉ የመጀመሪያው ሮማዊ ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው መገኘት የተገለጸውን በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ፍሬያማነት እና ብዝሃነትን መከባበርን አጉልተው አሳይተዋል፣ እናም ለዚህ ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉዞ ትሩፋት እንደሚተብቁ ተናግሯል። ከቫቲካን ዜና ገር በነበራቸው ቆይታ የቀረበላቸው የመጀርያው ጥያቄ የሚከተለው ነበር...

ጥያቄ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በታሪክ ወደ ሞንጎሊያ የተጓዙ የመጀመሪያው ጳጳስ ናቸው። አገራችሁ እሳቸውን ለመቀበል ስትዘጋጅ ምን ይሰማችኋል?

በመጀመሪያ ለዚህ እድል በጣም አመሰግናለሁ እናም እንደ ሞንጎሊያ አምባሳደር ፣ እኛ ሞንጎሊያውያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ አገራችን ስንቀበል ክብር ይሰማኛል። ይህ ታሪካዊ ጉብኝት ከቅድስት መንበር ጋር ባለን የሁለትዮሽ ግንኙነት ትልቅ ምዕራፍን የሚወክል እና ሞንጎሊያን በአለም አቀፍ ደረጃ በማሳየት የአለምን ትኩረት በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ በማድረስ ትልቅ ፋይዳ አለው።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአገራችን መገኘት በተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች መካከል ሰላምን ፣ ውይይትን እና መግባባትን ለማስፋፋት ቁርጠኝነትን ያሳያል ። ቅዱስነታቸው ሞቅ ባለ መስተንግዶ እና ከፍተኛ አክብሮት ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነን።

ጥያቄ፣ አዎ እርሶ እንዳሉት ከሆነ የእርሳቸው በመንጎሊያ መገኘት በአገሮ ላይ አለም አቀፍ ትኩረትን ይፈጥራል። ጎልቶ እንዲታይ የሚፈልጉት የተለየ ገጽታ አለ?

ሞንጎሊያ ቡድሂዝም ስር የሰደደባት እና በተለያዩ ሃይማኖቶች እና በካቶሊኮችም ጨምሮ በማህበረሰቦች መካከል ሰላማዊ አብሮ የመኖር ባህል ያዳበርንባት ሀገር እንደሆነች ይታወቅ ይሆናል።

ከዚህ አንፃር የዛሬዋ ሞንጎሊያ በሞንጎሊያ ግዛት ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት የተለያዩ ሃይማኖቶች በሰላም አብረው እንዲኖሩ ያደረገው እሴት እና ወግ እንደ ቀጠለ መመልከት ይቻላል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት የተለያዩ የሞንጎሊያን ማኅበረ-ፖለቲካዊ ገጽታዎች ለማጉላት ልዩ እድል ይሰጣል። በሞንጎሊያ ሕገ መንግሥት በተደነገገው የዓለማቀፉ ትኩረት በበለጸገ የባህል ብዝሃነታችን እና ህዝቦቻችን በሚያገኙት የእምነት ነፃነት ላይ እንዲያተኩር እንፈልጋለን። የሞንጎሊያ ቁርጠኝነት ለተለያዩ ሃይማኖቶች ሃይማኖታዊ መቻቻል እና ሰላማዊ አሠራር የብሔራዊ ማንነታችን አስፈላጊ ገጽታ እና የእድገት እሴቶቻችን ማሳያ ነው።

ይህን ታሪካዊ ክስተት ለማየት፣ የባህል ልውውጥን እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል  ውይይት ለማድረግ ብዙ ካቶሊኮች በአቅራቢያው ካሉ ሀገራት ወደ ሞንጎሊያ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ታሪካዊ ጉብኝት የሞንጎሊያ መንግሥት እ.ኤ.አ. 2023-2025 ሞንጎሊያን የመጎብኘት ዓመታት መሆኑን ካወጀበት እውነታ ጋር ይገጣጠማል ። ይህ ጅምር የሞንጎሊያን የበለፀገ ታሪክ፣ ባህል እና የተፈጥሮ ውበት ለአለም ለማሳየት ቱሪስቶችን እና ተጓዦችን በመጋበዝ የሀገራችንን ድንቅ ስራዎች ለማሳየት ያለመ ነው።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጉብኝት ለዚህ ዘመቻ ሌላ ጠቃሚ ነገርን ይጨምራል፣ ይህም ጎብኚዎች የሞንጎሊያን መስተንግዶ እና ወግ እያዩ አንድ ትልቅ ክስተት እንዲመለከቱ ልዩ እድል ይሰጣል። በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ እስያ ወደብ የሌላት ሀገር ያጋጠሟትን ተግዳሮቶች በዘላቂ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ የምናደርገውን ጥረት አፅንዖት ለመስጠት ተስፋ አደርጋለሁ። ጉብኝቱ ልዩ ባህላዊ ቅርሶቻችንን የመጠበቅን አስፈላጊነት እና ኃላፊነት የሚሰማቸው የአካባቢ ልማዶች ዓለም አቀፋዊ ጠቀሜታ ትኩረት ሊስብ ይችላል።

ጥያቄ፡ አዎ እርሶ እንዳሉት ከሆነ በዋነኛነት የረዥም የቡድሂስት ባህል ያላት ሀገር ነች እና የካቶሊክ እመነት ተከታዮች ቁጥር በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአንዲት ትንሽ ቤተ ክርስቲያን፣ ደካማ ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ቅርበት እያሳዩ ነው። ስለዚህ ጉዳይ ሀሳብ አሎት ወይ?

አዎን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሞንጎሊያ ለሚገኘው የካቶሊክ ማህበረሰብ ያላቸውን ቅርበት ለማሳየት ስለመረጡ በጣም እናመሰግናለን። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሞንጎሊያን በመጎብኘት በሃይማኖት ተቋማት መካከል መነጋገር እና መረዳዳት ባለው ጥቅም ላይ ያላቸውን ጥልቅ እምነት አሳይተዋል። የእርሳቸው መገኘት የካቶሊክ ማህበረሰብንም ሆነ ሰፊውን የሞንጎሊያን ማህበረሰብ ብዝሃነትን እንዲቀበሉ እና የተለያዩ እምነቶችን እንዲያከብሩ እና የበለጠ ሁሉን አቀፍ እና እርስ በርሱ የሚስማማ የወደፊት ጊዜ እንዲመጣ በጋራ ለመስራት እንደሚያነሳሳ አምናለሁ።

ጥያቄ፡ አምባሳደር፣ በቅድስት መንበር እና በሞንጎሊያ መንግሥት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተፈጠረ ከ30 ዓመታት በኋላ የሹመት ደብዳቤዎትን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እ.አ.አ በ2022 አቅርበዋል። ዛሬ እነዚያን ግንኙነቶች እንዴት ይገልጹታል?

እ.ኤ.አ. በ1992 በሞንጎሊያ እና በቅድስት መንበር መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመሥረቱ በሁለትዮሽ ግንኙነታችን ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነበር። ሞንጎሊያ ከቅድስት መንበር ጋር ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላት ከመደበኛው ምስረታ ከረጅም ጊዜ በፊት አስፈላጊ መሆኑን ማስተዋል እፈልጋለሁ። በሞንጎሊያ ግዛት ዘመን በሞንጎሊያውያን እና በሊቃነ ጳጳሳት መካከል ያሉ ግንኙነቶች በክልሎቻችን መካከል ያለውን ዘላቂ ባህል እና መንፈሳዊ ልውውጥ የሚያንፀባርቁ ግንኙነቶች እንደነበሩ ታውቅ ይሆናል።

ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከቅድስት መንበር ጋር ያለን ግንኙነት እየጠነከረ እና እየጠነከረ መጥቷል፤ በትምህርት፣ በጤና እና በባህል ጉዳዮች ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ተባብረናል። በእነዚህ አካባቢዎች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምታደርገው አስተዋጽኦ በብዙ ሞንጎሊያውያን በተለይም በተጋላጭ ቡድኖች ውስጥ ባሉ ሰዎች ሕይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል።

እ.ኤ.አ. በ 2000 እና 2011 የሞንጎሊያው ፕሬዝዳንት በቫቲካን ያደረጉት ጉብኝት እና የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ለምሳሌ ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት  ካርዲናል ፖል ጋላገር በዚህ አመት በሞንጎሊያ ያደረጉት ጉብኝት ፣የእኛን አስፈላጊነት እና ተለዋዋጭነት ማሳያ መሆናቸውን ማስተዋል እፈልጋለሁ። እነዚያ የከፍተኛ ደረጃ ልውውጦች ግንኙነታችንን የበለጠ አራዝመዋል እናም ለውይይት እና ለትብብር የጋራ ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

በተጨማሪም ሊቀ ጳጳስ ጆርጂዮ ማሬንጎ በሞንጎሊያ የመጀመሪያ ካርዲናል ሆነው መሾማቸው የግንኙነታችንን አስፈላጊነት ማሳያ መሆኑን ማስተዋል እፈልጋለሁ።

የወደፊቱን ጊዜ ስንመለከት፣ ከቅድስት መንበር ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኞች ነን።

አጋርነታችን አለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት እና የጋራ አላማችን የሆኑትን የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የማህበራዊ እድገቶችን ለመፍታት ትልቅ አቅም እንዳለው አምናለሁ።

ጥያቄ፡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በማህበራዊ ፕሮጀክቶች፣ በጤና እንክብካቤ ፕሮጀክቶች፣ በትምህርት፣ በልማት የምታደርገውን አስተዋጽኦ ጠቅሰዋል። በሞንጎሊያ ውስጥ ላሉ ድሆች እነዚህ ተግባራት ምን ያህል አስፈላጊ ናቸው?

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሞንጎሊያ የምትሰራቸው ፕሮጀክቶች ለሀገራችን ልማት በተለይም ለችግር ተጋላጭ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ላለባቸው ማህበረሰቦች ወሳኝ ናቸው። በሞንጎሊያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምታከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶች በጤና አጠባበቅ፣ በማህበረሰብ መሠረተ ልማት እና በዘላቂነት መተዳደሪያ ላይ ባሉ የተለያዩ ዘርፎች ላይ አወንታዊ ተጽእኖ አላቸው። እነዚያ ፕሮጀክቶች ለድህነት ከፍታ አስተዋፅዖ ከማድረግ ባለፈ ማህበራዊ ማካተት እና ለሁሉም ሞንጎሊያውያን እኩል እድሎችን ያበረታታሉ። ቤተክርስቲያኗ ለትምህርት እና ለልማት የሰጠችው ትኩረት ከመንግስታችን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የሚጣጣም ሲሆን ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታችን የሚያደርጉትን አስተዋፅዖ ከልብ እናደንቃለን።

ጥያቄ፡ አምባሳደር በመጨረሻ፣ ከጉብኝቱ ምን ትጠብቃላችሁ? ምን ፍሬዎችን እንደሚያፈራ ተስፋ ያደርጋሉ?

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጉብኝት የምንጠብቀው ብዙ እና ከቆይታቸው አጭር ጊዜ በላይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ጉብኝቱ በሞንጎሊያ እና በቅድስት መንበር መካከል ያለውን ወዳጅነት እና መግባባት ያጠናክራል፣ ይህም በትምህርት፣ በማህበራዊ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ባሉ የተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ያመጣል ብዬ አምናለሁ።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ጉብኝት በመጠባበቅ፣ በሃይማኖቶች መካከል የሚደረጉ ውይይቶችን ለማስተዋወቅ እና ለተለያዩ እምነቶች መካከል ያለውን አክብሮት እንደ ምያዳብር እንጠባበቃለን። ይህ ደግሞ በክልላችን እና በአለም አቀፍ ደረጃ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ትልቅ አስተዋፅዖ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም ጉብኝቱ ስለ ሞንጎሊያ የባህል ብልጽግና፣ ታሪካዊ ቅርሶች እና ልዩ ማንነት ዓለም አቀፍ ግንዛቤን እንደሚያሳድግ መጥቀስ እፈልጋለሁ። ባህሎቻችንን እና እሴቶቻችንን በማሳየት ሞንጎሊያ እንደ የጉዞ መዳረሻ እና የባህል ማዕከል የበለጠ ፍላጎት ለመሳብ ተስፋ እናደርጋለን።

ከምንም በላይ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት ጥልቅና ዘላቂ የሆነ የሰላም፣ የትብብር እና በጎ ፈቃድ ትሩፋት እንዲኖር እንጠብቃለን። ታሪካዊው ጉብኝቱ በሞንጎሊያ ዘላቂ ልማት፣ ማህበራዊ እድገት እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ አዲስ ጥረቶችን እንደሚያበረታታ ተስፋ እናደርጋለን።

የዚህ ታሪካዊ ጉብኝት ፍሬ ለአገራችን የበለጠ አንድነትና ብልፅግና እንዲኖረን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኃላፊነት የሚሰማውን አቋማችንን ያጠናክራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

በአጠቃላይ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት በአገራችን እና በሕዝባችን ላይ በጎ ተጽእኖ ይኖረዋል ብለን እናምናለን ወደ ሞንጎሊያም ሲመጡ እርሳቸውን ለመቀበል በጉጉት እንጠባበቃለን።

31 August 2023, 11:35