ፈልግ

አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ከፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር በተገናኙበት ወቅት አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ከፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር በተገናኙበት ወቅት 

አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ዓለም አቀፍ የነገረ-መለኮት ማዕከል ሊመሠረት መሆኑን አስታወቁ

በጳጳሳዊ አካዳሚ የነገረ-መለኮት ተቋም ፕሬዝዳንት ብጹዕ አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ በኢስታንቡል ከቁንስጥንጥንያው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ከሆኑት ከብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ከፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር ተገናኝተው ባደረጉት ንግግር፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሁል ጊዜ በጦርነት ከተጎዱት የዩክሬን እና ሩሲያ ሕዝብ ጎን ነው" ብለው፥  በፕሬዝደንትነት የሚመሩት ጳጳሳዊ አካዳሚያቸው ከማኅበረሰቡ ከተገለሉት ጀምሮ ለሁሉም ሰው የቆመ ተከታታይ ሥነ-መለኮታዊ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

"እግዚአብሔር እና የሰዎች ዓመፅ በሃይማኖቶች እና በክርስትና እምነት መካከል" በሚል አርዕስት በኢስታንቡል በተዘጋጀው መድረክ የጳጳሳዊ ሥነ-መለኮት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ብጹዕ አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ከቁስጥንጥንያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ዓለም አቀፍ የሥነ-መለኮት ማዕከል ሊመሠረት መቃረቡን ገልጸዋል።

የደበዘዘ የሚመስል ያለፈ ታሪክ

በዩክሬን በመካሄድ ላይ የሚገኘው ጦርነት “ብዙዎች ጊዜ ያለፈበት ነው” ብለው የሚያምኑት እና ያለፈ የክርስትና ታሪክ እንደገና እንዲያገረሽ ያደረገ፣ እግዚአብሔርም ከሕዝቡ ጎን ሊቆም እንደሚችል እምነት የተጣለበት እንደሆነ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ ተናግረው በመስቀል ላይ የሞተው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፊት የተገለጠበት መሆኑን አስረድተዋል። ከጳጳሳዊ የሥነ መለኮት አካዳሚ ይፋ የሆነው መግለጫ እንደገለጸው፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁል ጊዜ በጦርነት አደጋ ከተጎዱት የዩክሬን እና የሩሲያ ሕዝቦች ጎን እንደሆነ፣ ሁሉም ሰው በፍቅር ትዕዛዙ ይቅርታን በማድረግ ወዳጅነትን እና ወንድማማችነትን ማሳደግ ይገባል" ብሏል።

በአመጽ የተበላሸው የእግዚአብሔር ቅዱስ ስም

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ "በእግዚአብሔር ስም ግፍን መሥራት ሰይጣናዊ ተግባር ነው" ማለታቸውን በሙላት የሚጋሩት የቁስጥንጥንያው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ር ዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እውነተኛ ወንድም ናቸው” ማለታቸው ይታወሳል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት ማኅበራዊ ችግሮች በተጨማሪ በእስያ እና አውሮፓ ውስጥ የሚታዩ ጂኦ ፖለቲካዊ ችግሮች እና የዩክሬን ውስጥ ጦርነትም ጭምር በእግዚአብሔር ስም የሚነሱ የሥነ-መለኮት ችግሮች ዘወትር የተጠላለፉ እና የእግዚአብሔርን ስም የሚያበላሹ እንደሆነ ይነገራል።

መልካም ውጤት እያስገኘ ያለው ሥነ-መለኮት

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1204 ዓ. ም. የታየው የቁንስጥንጥንያ ማመሳከሪያው የመሳሰሉት አንዳንድ ታሪካዊ እውነታዎች ወይም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1453 ዓ. ም. የባይዛንታይን ዘመነ መንግሥት ሲፈርስ በክርስቲያኖች ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ እና ሌሎችም አሳዛኝ ክስተቶች በእግዚአብሔር ስለ መካሄዳቸው፣ እግዚአብሔር ጥበቃውን የሚጠይቁ ሰዎች ጸሎት የማይሰማው ለምንድን ነው?” የሚሉ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሱ መሆናቸው ተነግሯል።

የእግዚአብሔር እና የክርስቲያናዊ መገለጥ ለተከታታይ ተነሳሽነቶች እምብርት በመሆን ከማኅበረሰቡ ከተገለሉት ጀምሮ ለሁሉም ሰው የቆመ ተከታታይ ሥነ-መለኮታዊ ሥራዎችን እየተከናወነ እንደሚገኝ ጳጳሳዊ የሥነ መለኮት አካዳሚውን በፕሬዝደንትነት የሚመሩት ብጹዕ አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ከቁንስጥንጥንያው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ከብጹዕ ወቅዱስ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር በስታንቡል በተገናኙበት ወቅት ገልጸዋል።

01 July 2023, 17:06