ፈልግ

ተመራጩ ካርዲናል ፍራንሷ ዣቭየር በስቲሎ ተመራጩ ካርዲናል ፍራንሷ ዣቭየር በስቲሎ 

ከፈረንሳይዋ አጃቺዮ የተመረጡት ካርዲናል ቡስቲሎ ምዕመኑን ከጳጳሱ ጋር በተለየ ሁኔታ ያቀራርባሉ ተባለ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በመጪው መስከረም 19, 2016 ዓ.ም. ካርዲናል አርገው ከሚሾሙዋቸው 21 ጳጳሳት መካከል በፈረንሳይ በኮርሲካ የሚገኘው የአጃቺዮ የውደብ ከተማ ጳጳስ የሆኑት ተሿሚ ካርዲናል ፍራንሷ-ዣቪየር ቡስቲሎ ይገኙበታል። በመመረጣቸው መገረማቸውን እና ኃላፊነታቸውም ከጳጳሱ እና ከፈረንሳይ ሀገረ ስብከታቸው ሕዝብ ጋር ተቀራርቦ መሥራትን እንደሚጨምር መገንዘባቸውን ገልጸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በፈረንሳይ ኮርሲካ ደሴት የአጃቺዮ ጳጳስ የሆኑት ተመራጩ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንሷ ቡስቲሎ ፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንስስኮስ ባለፈው እሁድ ዕለት እኩለ ቀን ላይ የገለጹትን በካርዲናልነት ስለመመረጣቸው ዜና በስልክ ሲነገራቸው በጣም መገረማቸውን ተናግረዋል። ይሄንንም ሁኔታ ሲገልፁ “መጀመሪያ ላይ የሆነ ሰው በኔ ላይ መቀለድ ፈልጎ ሊሆን ይችላል ብዬ አስቤ ነበር” ብለዋል።
   “ለዚህ ዜና ምንም ዝግጁ አልነበርኩም”
የፍራንቺስካዊያን ማህበር አባል የሆኑት ስፔናዊው ተመራጭ ካርዲናል የአጃቺዮ ሃገረ ስብከት ጳጳስ ሆነው ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል። መስከረም 19 2016 ዓ.ም. ላይ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እንደሚሾሙ እና ካርዲናል ሆነው መመረጣቸውን በስልክ ከተነገራቸው በኋላ ፥ አሁን ለእኔ የተሰጠኝ ኃላፊነት ጫናው ምን ያክል እንደሆነ እገነዘባለው በማለት ለቫቲካን ዜና ዘጋቢ ዣቪየር ሳርቴ ተናግረዋል።
ለጊዜው ካርዲናል መሆን ምን ማለት እንደሆነ በተጨባጭ አገላለጽ በትክክል መግለጽ እንደማይችሉ ፥ ነገር ግን ይህ ኃላፊነት ‘ከቅዱስ አባታችን ጋር በደንብ መቀራረብ እና ታማኝ ሆኖ መሥራት’ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን እገነዘባለሁ ብለዋል።
ካርዲናል መሆን ከሚያካትታቸው ጠቃሚ ነገሮች አንዱ እንደ ኮርሲካ ኤጲስ ቆጶስ ከተወሰነ ሕዝብ ወይም ሀገረ ስብከት ጋር የመቀራረብ ዕድል ግንኘት መሆኑን ተመራጩ ብፁዕ ካርዲናል አስታውቀዋል።
"የሮማው ቅድስት መንበር እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚጠይቁኝን ነገር ለመታዘዝ ዝግጁ እንደሆንኩ እና በአሁኑ ጊዜ እዚህ ኮርሲካ ውስጥ ያለኝን ኃላፊነት በቀጥታ ከአጃቺዮ እና ከሀገረ ስብከቱ ሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት በትህትና እና በሚዛናዊነት ለመፍጠር መሞከር አለብኝ” ሲሉ ተናግረዋል።
ካርዲናል ከአቺዮ ግዛት ሲሾም ይህ በታሪክ የመጀመሪያው ነው። የቅዱስ አባታችንን ውሳኔ ለማስረዳት ተመራጩ ካርዲናል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያላቸውን ሙሉ “ነፃነት” ጠቅሰዋል።
“ማንንም አናስገድድም ፥ ካርዲናል ለመሆንም አንጠይቅም” ሲሉም ጠቁመዋል።
“ነገር ግን ልክ በእኔ እንደሆነው ፥ ቅዱስ አባታችን አንዳንድ ጊዜ ‘ከትናንሽ ሃገረ ስብከቶች ጳጳሳትን’ ይመርጣሉ” በማለትም ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
 

11 July 2023, 13:05