ፈልግ

FILE PHOTO: Illustration shows Google, Microsoft and Alphabet logos and AI Artificial Intelligence words

ካርዲናል ሜንዶንካ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ሰው ሰራሽ አብርሆት በፈጠራ ችሎታ መቀበል አለባቸው አሉ!

በቅድስት መንበር የባህል እና የትምህርት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ሆሴ ቶለንቲኖ ዴ ሜንዶንካ ስለ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲዎች የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ ባደርጉት ቃለ ምልልስ እንደ ተናገሩት ከሆነ "ታድሶ እና ግንዛቤ" የሚሉት ቁልፍ ቃላት በሳይንሳዊ ምርምር ውስጥ የቴክኖሎጂ አተገባበር መመሪያ አድርገው ጠቅሰዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ብፁዕ ካርዲናል ሆሴ ቶለንቲኖ ደ ሜንዶንካ በቅድስት መንበር የባህል እና የትምህርት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አብርሆት) በተመለከተ በተደርገው ሳይንሳዊ ስብሰባ ላይ ባደርጉት ንግግር ይህንን በመቀበል ረገድ ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልተዋል።

“ታድሶ እና ግንዛቤ፡ ስለ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች የወደፊት እጣ ፈንታ ማሰብ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዝግጅት በካቶሊክ የምርምር ዩኒቨርስቲዎች ስትራቴጂክ ጥምረት (SACRU) የተዘጋጀ ሲሆን ሚላን በሚገኘው የቅዱስ ልብ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ  ውስጥ ስብሰባው መካሄዱ ተገልጿል።

ብፁዕ ካርዲናል ደ ሜንዶንሳ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች በፈጠራ ሥራ ውስጥ እንዲመሩ እና በታዳጊ አዝማሚያዎች እንዲሳተፉ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግሯል። የውይይት አስፈላጊነት፣ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን መፍታት እና ቀጣይነት ያለው ታድሶ በግንዛቤ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አሳስበዋል።

አግባብነት ያላቸውን የቤተ ክርስቲያን ሰነዶች በመጥቀስ፣ የወደፊቱን ጊዜ በመቅረጽ ረገድ የእነዚህ ተቋማት መሠረታዊ ሚና ላይ አጽንዖት ሰጥቷል።

ቴክኖሎጂን በተገቢው ስነምግባር መቀበል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሰው ሠራሽ አብርሆት (AI) ላይ የሰጡትን አስተያየት በዋቢነት በመጥቀስ ዩኒቨርስቲዎች የሥነ ምግባርን አንድምታ እያጤኑት ያለ ፍርሃት ሰው ሥራሽ አብርሆት እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እንዲቀበሉ አበረታተዋል።

የግለሰቦችን ደህንነት ማስቀደም እና የሞራል እሴቶችን ማክበር ካርዲናሉ አጽንዖት የሰጡባቸው ቁልፍ መርሆች ናቸው።

ስለ የሰው ሰራሽ አብርሆት (AI) ሰነ-ሰብዕአዊ (አንትሮፖሎጂያዊ) እንድምታዎች፣ ካርዲናል ደ ሜንዶንካ ሲገልጹ የሰውን ልጅ ያማከለ ሁለንተናዊ አቀራረብን አስፈላጊነት አጉልተዋል። በግለሰቦች ሕነጻ ላይ መዋለ ነዋይ ፈሰስ እንዲደረግ፣ የግንዛቤ፣ የፈጠራ፣የመንፈሳዊ እና የስነ-ምግባር አቅማቸውን ማሳደግ እንዳለበት አሳስቧል።

ካርዲናሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከህብረተሰቡ ጋር መቀራረብ እና ከተለያዩ ባህሎች ጋር መገናኘት ያላቸውን ጠቀሜታ አጉልተዋል። በጠንካራ እሴቶች ላይ የተመሰረተ የፈጠራ እውቀት እና ማስተዋል እንደ አስፈላጊ ባህሪያት ተለይቷል።

'የሰው ሠራሽ አብርሆት ስልታዊ ቀመር ሥነ-ምግባር'

ካርዲናል ዴ ሜንዶንካ በካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሰው ሠራሽ አብርሆት (AI) በመተግበር ላይ ያለውን ኃላፊነት አበክረው ገልጸው፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይፋ የተደረገውን “የሰው ሠራሽ አብርሆት ስልታዊ ቀመር ሥነ ምግባር” ጽንሰ-ሐሳብ ጠቅሰዋል። በሰው ሠራሽ አብርሆት  አመራረት እና አጠቃቀም ላይ ስነ-ምግባርን የሚያረጋግጡ ማህበራዊ አወቃቀሮችን ጠይቋል።

ስብሰባው በተለያዩ መስኮች የሰው ሠራሽ አብርሆት መተግበሪያዎችን ተግዳሮቶች እና እድሎች ዳስሷል። በተለይ ለአካል ጉዳተኞች የሚደርገውን ስልጠናን በማሳደግ ረገድ ትብብር እና አካታች እድሎች ጎልተው ታይተዋል።

የፍትሃዊነት፣ የምስጢራዊነት እና የመረጃ ማረጋገጥ አስፈላጊነትን በማጉላት የቴክኖሎጂ እድገት ፈጣን ሂደት ላይ ስጋት ተነስቷል። ይሁን እንጂ ተሳታፊዎች በሰው ሰራሽ አብርሆት ለዘላቂ ማህበረሰቦች አስተዋፅኦ ለማድረግ እና አዳዲስ ሙያዎችን ለማስተዋወቅ አቅም እንዳለው ተስማምተዋል።

የስብሰባው ውጤቶቹ የሰው ሰራሽ አብርሆት ግንኙነት እና በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች የተከበሩ እሴቶችን በሚመለከት ይፋዊ በሚደረግ ሰነድ ይጠቃለላል።

የአለም አቀፉ የካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች ፌደሬሽን በሚቀጥለው አመት የተመሰረተበት መቶኛ አመት ሊሞላው ሲቃረብ፣ ይህ ስብሰባ የሰው ሰራሽ አብርሆት ልምምዶች ውስጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ በማካተት እና ለተሻለ የወደፊት ጊዜ አስተዋፅኦ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ሰጥቷል።

 

14 July 2023, 11:02