ፈልግ

ቫቲካን ከሌሎች ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በዋናነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ቫቲካን ከሌሎች ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በዋናነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር   (AFP or licensors)

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወኔ ለሰላም ያደረጉትን ጥረት አስታወሰዋል!

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወኔ ለሰላም ያደረጉትን ጥረት አስታወሰዋል! ቫቲካን ከሌሎች ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በዋናነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር በጣሊያንኛ ቋንቋ “ከዩክሬን ትምህርት” (ከዩክሬይን የተቀሰመ ትምህርት እንደ ማለት ነው) በሚል ርዕስ አዲስ መጽሐፍ ይፋ በሆነበት ወቅት ንግግር ያደረጉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተለይም በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርጉትን ጥረት አጉልተው ገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በጣሊያን ጂኦፖለቲካዊ ግምገማ በጣሊያነኛ ቋንቋ “ሌሲዮኒ ሁክራይና ” (የዩክሬን ትምህርት) መጽሐፍ ዝግጅት ላይ ንግግር ያደረጉት ቅድስት መንበር ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር “በቅዱስ አባታችን የተወሰደው አቋም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የዩክሬን ጦርነት እና ለቃላቶቹ እና ምልክቶች የተሰጠው ትርጓሜ በጥንቃቄ ማቅረባቸውን" አድንቀዋል።

“ዩክሬናውያን ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መግለጫ የሰጡት ምላሽ ጥልቅ የሆነ ብስጭት የሚያንፀባርቅ መሆኑን መቀበል የማይታበል ነገር ነው” በማለት ተናግሯል። ይህ በዩክሬን መንግስት ባለስልጣናት እና በተለያዩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና የቤተክርስቲያን ማህበረሰቦች የሃይማኖት ተወካዮች፣ በአንዳንድ ሁኔታዎችም በቅርብ ጊዜ ውስጥም ተገልጧል። ለሊቀ ጳጳሱ የአደባባይ ንግግሮች እና ምልክቶች ምላሽ መስጠት እና ትርጓሜያቸው በነጻነት እና በማስተዋል በትክክል ሊሰጥ ይችላል” ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር አክለው ገልጸዋል።

የውይይት እና የሰላም ፍላጎት

ይሁን እንጂ ሊቀ ጳጳሱ “የባዶ ሰላማዊ ድርጊቶች” በማለት መተርጎምና ‘የቲያትር ዘውግ ‘የቀና የምኞት’ መግለጫዎች’ በማለት የቅዱስ አባታችንን ራዕይና ዓላማ የሚጻረሩ በመሆናቸው ፍትሐዊ እንደማይሆን ጠቁመዋል። በተለይም ደግሞ ራሳቸውን ከጦርነት ለማላቀቅ እና በሰላም ለማመን ግትር ሐሳብ ያላቸው ሰዎች የሰለም መፍጠሪያ መሳሪያዎች እና ሰላምን መገንባት የሚችሉ የእደ ጠበብ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ጋብዘዋል።

በመቀጠልም “ቅዱስ አባታችንን የሚያነሳሳው “ቤተ ክርስቲያን የኢየሱስን ቋንቋ እንጂ የፖለቲካ ቋንቋ መጠቀም የለባትም” በሚለው መርህ በመነሳት ውይይትና ሰላም እንዲሰፍን ካለው ፍላጎት በቀር ሌላ አይደለም ብለዋል።

በመቀጠልም ሁሉም ሰው ሊገነዘበው የሚገባው “የቅዱስ አባታችን ርምጃዎች እና ንግግሮች “የሰላም ንግግሮች” ብቻ ሳይሆኑ ጠንካራ እና ደፋር የሆነ “የሚያምር የሰላም ንግግር” ብቻ ሳይሆን የማይቀር ነው ተብሎ የሚታሰበው የጦርነት እና የጦርነት እውነተኝነትን የሚፈታተን መሆኑን ነው ብሏል።

ይህን ትንቢት ግን ከመቀበል እና ከመደገፍ ይልቅ ብዙ ጊዜ ውድቅ እና የተወገዘ እንዲሆን መደረጉን አምኗል።

አንድነት እና ክርስቲያናዊ መቀራረብ

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር በዩክሬይን የሚገኙ የቫቲካን ኤንባሲ ሐዋሪያዊ እንደራሴ  በዩክሬን ዋና ከተማ እንዴት እንደቆዩ አስታውሰው ሌሎች ኤምባሲዎች ወደ ሊቪቭ ተዛውረዋል ይህም "ለሰማዕቱ ሕዝብ ተጨባጭ ክርስቲያናዊ ቅርበት እና ሰላምን ለመደገፍ" መንገድ የሚከፍት ነው ብሏል።

ከዚህ አንፃር “በተጨማሪም በካርዲናል ኮንራድ በዩክሬን የተከናወኑትን በርካታ ተልእኮዎች ሳይዘነጉ፣ የአካባቢው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ የላቲንና የምስራቅ ሥነ ሥርዓት፣ እንዲሁም የተለያዩ የካቶሊክ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ በተለይም በሰብአዊነት መስክ ያደርጉት ተሳትፎው ትኩረት የሚስብ ነው” ሲሉ ተናግሯል።

እነዚህን ጥረቶች "የበጎ አድራጎት ማቀፍ" በማለት ሊቀ ጳጳሱ ጋላገር የተናገሩ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የዩክሬን ሕዝብ እየደረሰባቸው ባለው ስቃይ እና አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ብቻቸውን እንዳልተዋቸው ገልጿል።

ይህ "ሁላችንም ለእውነት ያለብንን ግዴታ .... (እና) ለአሁኑ አሳዛኝ ሁኔታ አወንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚረዱትን ነገሮች ሁሉ የማስተዋወቅ የጋራ ሀላፊነት" ግንባር ቀደም ያደርገዋል ሲሉ ተናግሯል።

 

14 July 2023, 10:59