ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒየስ 12ኛ ስለ ‘የቤተሰብ እናቶች እና አባቶች’ የፃፉት ጽሁፍ

የቫቲካን ዜና ኤዲቶሪያል ቦርድ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ መፅሐፍ የሆነው እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሚስጥራዊ አካል እንደሆነች የሚገልጸውን መጽሃፍ (ኢንሳይክሊካል) በአማሪኛ ጥሬ ትርጉሙ “ሚስጥራዊ አካል” (“Mystici Corporis”) 80ኛ ዓመትን በማስመልከት አስተንትኖ አርጓል።

    አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

 በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ የተፃፈው ጽሁፍ ‘ሚስትሪኪ ኮርፖረስ’ አንዱ ምዕራፍ ውስጥ በተለይ በቤተሰቡ ውስጥ ያለው የእምነት ሥርጭት ችግር ውስጥ ያለበት እና ቤተክርስቲያን ዓላማው ተልእኮውን ማስፈፀም በሆነበት የሲኖዶሳዊነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ የምትገኝበትን እና የምትለማመድበትን የሚገልጽ አንቀፅ አለ።
ሰኔ 22 ቀን 1935 ዓ.ም. በታተመው ኢንሳይክሊካል ውስጥ ፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ ቤተክርስቲያንን ‘በሥነ ሰውነታዊ’ እና ‘በስልጣን ተዋረድ’ የተዋቀረ የክርስቶስ አካል እንደሆነች ገልፀዋታል። የቤተክርስቲያኑ ኦርጋኒክ አወቃቀር ተዋረዳዊ አካላትን ብቻ እንደሚይዝ እና ከእነሱም ጋር የተሟላ እንደሆነ ወይም በተቃራኒው አስተያየት ፥ የካሪዝማቲክ ወይም በግርማ ሞገሳዊ ስጦታዎች ከሚደሰቱት ብቻ የተዋቀረ ነው ብለን እንዳናምን ይጋብዘናል (ምንም እንኳን ተአምራዊ ኃይል ያላቸው ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ባይጎድሉም) ።
በአንድ በኩል ኤጲስ ቆጶሳት እና ቀሳውስት ብቻ አይደሉም ፥ በሌላ በኩል ደግሞ ልዩ ሞገስ ያላቸው ሰዎችንም ያካትታል።
ጳጳሱ አክለውም “በተለይ በእኛ ዘመን በቤተሰብ ውስጥ ያሉ አባቶች እና እናቶች ፣ በጥምቀት የክርስትና አባቶች የሆኑት እና በተለይም የመለኮታዊውን ቤዛ መንግሥት በማስፋፋት ረገድ ከቤተክርስቲያን ተዋረድ ጋር በመተባበር የሚሰሩ የምእመናን አባላት፣ በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ የተከበሩ ፥ ብዙ ጊዜ ዝቅ ያለ ቦታ ቢይዙም፣ እና እነርሱ በእግዚአብሔር ግፊት ሥር እና በእሱ እርዳታ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የገባለትን፣ ቤተክርስቲያንን ፈጽሞ የማይፈልግ የቅድስና ከፍታ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ” ብለዋል።
‘በእኛ ዘመን’ ማለትም በ1935 ዓ.ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተከሰተው አስከፊ አሰቃቂ ሁኔታዎች የሚገለፁት ዓመታት የጴጥሮስ ተተኪ የሆኑት ‘የቤተሰብ አባቶች እና እናቶች’ የሚይዙትን (ወይም ሊይዙት የሚገባውን) ‘የክብር ቦታ’ የክርስቲያን ሕይወት እና የቅዱስ ቁርባን ሥርዓትን የሚሠሩ እና የሚኖሩ የእግዚአብሔር ሰዎችን ያመላክታል።
ፒዮስ 12ኛ ለእነሱ የቅድስና መንገድን ማስታወስ ብቻ ሳይሆን ፥ ለመንግሥቱ መስፋፋት ማለትም ለተልእኮው የሚያደርጉትን መሠረታዊ አስተዋጽኦንም አበክረው ገልጸዋል።
ዛሬ ምናልባት ከሰማንያ ዓመታት በፊት ከነበረው በላይ ስለ እምነት የመመስከር ተልእኮ የተሰጣቸው የአባቶች እና የቤተሰብ እናቶች የዕለት ተዕለት እና ድብቅ ምስክርነት ነው።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የሲኖዶሱን መዋቅር በአዲስ መልክ በመቅረጽ እና ከጳጳሳት ጎን ለጎን ምእመናን የሚያበረክቱትን ውጤታማ አስተዋፅዖ እንዲያሳድጉ ክፍት በማድረግ ከረጅም ጊዜ በፊ የመጣውን እና ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የማዕዘን ድንጋይ የነበረውን ግንዛቤ አጠናክረው ቀጥለዋል።
 

30 June 2023, 15:47