ፈልግ

የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም)   (© Vatican Media)

የቫቲካን ባንክ እ.አ.አ በ 2022 ዓ.ም 29.6 ሚሊዮን ዩሮ የተጣራ ገቢ ማግኘቱን ሪፖርት አድርጓል

የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ በማድረግ ያሳተመ ሲሆን "ከፍተኛውን የሥነ ምግባር እና የቁጥጥር ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን" ለማክበር ያለውን ቁርጠኝነት በማጉላት እና የ Moneyval (Moneyval የገንዘብ እጥበትን የሚቆጣጠር እና የገንዘብ ማሸሽ እርምጃዎችን የሚገመግም እና  የሽብርተኞችን የፋይናንስ ፍስተ የሚቆጣጠር የባለሙያዎች ኮሚቴ የተለመደ እና ኦፊሴላዊ ስም ነው። ሞኒቫል የአውሮፓ ምክር ቤት የሚከታተል አካል ሲሆን 47 አባል ሀገራት በቀጥታ ለዋናው አካል ለአውሮፓ ምክር ቤት የሚኒስትሮች ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባል) ደረጃ አሰጣጥ "ተቋሙን እንደ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ያደርገዋል። በዓለም ላይ ካሉት ምርጥ ተቋማት አንዱ” እየሆነ መምጣቱም ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ በቅርቡ ባወጡት መመሪያ እንደተደነገገው የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (Istituto per le Opere di Religione" or IOR) እንቅስቃሴዎች ላይ ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የቅድስት መንበር ተንቀሳቃሽ ሀብቶች እና ከቅድስት መንበር ጋር የተገናኙ ተቋማት ሥራ አስኪያጅ እና የበላይ ጠባቂ” ማክሰኞ ግንቦት 29/2015 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገልጿል።  

ከሪፖርቱ መውጣት ጋር ተያይዞ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው የተጣራ ገቢ 29.6 ሚሊዮን ዩሮ (ከቀደመው ዓመት 18.1 ሚሊዮን ዩሮ ጋር ሲነጻጸር) የተጣራ የትርፍ ህዳግ + 3.7 በመቶ፣ የተጣራ ኮሚሽን ህዳግ + 20.9 በመቶ፣ እና የMoneyval ደረጃ አሰጣጥ ደንብ መሰረት የቫቲካን ባንክ “በዓለም ላይ ካሉት ከፍተኛ ደረጃ ካላቸው ተቋማት” ውስጥ መመደቡ ተገልጿል።

መግለጫው “ለአስራ አንደኛው ተከታታይ ዓመት” ይላል መግለጫው “የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) እ.አ.አ በ2022 ዓመታዊ ሪፖርቱ የፋይናንስ መግለጫዎችን በ IAS-IFRS ዓለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎች መሠረት ይፋ ድርጓል።

መግለጫው ሲቀጥል "እነዚህ የፋይናንስ መግለጫዎች ከኦዲተር Mazars Italia S.p.A. ንጹህ አስተያየት ተቀብለዋል እና እ.አ.አ በየካቲት 25/2023 የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) የበላይ ቁጥጥር ቦርድ ተልኮ በህግ በተደነገገው መሰረት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል እናም ከዚያም ወደ ካርዲናሎች ኮሚሽን ተልከዋል፣ የእነሱ ግምገማም ታክሎበታል” ሲል ይፋ ድርጓል።

እ.አ.አ "የ2022 የፋይናንስ መግለጫዎች ጤናማነት እና የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) የካፒታል መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የካርዲናሎች ኮሚሽን በትርፍ ክፍፍል ላይ ወስኗል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ “የልማት ግቦቹን በረጅም ጊዜ ውስጥ ማስቀጠል እንዲችል” የቁጥጥር ቦርዱ የካርዲናሎች ኮሚሽን “እንደ እ.ኤ.አ. በ2022 የትርፍ ክፍፍል ላይ አስተዋይ ፖሊሲ” እንዲይዝ መክሯል። ይህ አካሄድ በዩናይትድ ስቴትስ እና በአውሮፓ በቅርቡ በተከሰቱት የባንክ ቀውሶች እና ተቋሙ ከሚሠራበት ልዩ አውድ አንጻር የረጅም ጊዜ ጥበቃ አስፈላጊነት ተጠናክሯል ይላል ዘገባው። እ.ኤ.አ. በ2022 የተገኘውን ትርፍ በተመለከተ ቦርዱ 5.2 ሚሊዮን ዩሮ የትርፍ ክፍፍል እንዲከፋፈል ለካርዲናል ኮሚሽኑ አቅርቧል።

ምክር ቤቱ የትርፍ ድርሻው በሚከተለው መልኩ እንዲከፋፈል ሐሳብ አቅርቧል።

  - 3 ሚሊዮን ዩሮ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሃይማኖታዊ ሥራዎች ይሆን ዘንድ ተመድቧል።

  - 2 ሚሊዮን ዩሮ ለካርዲናል ኮሚሽን የበጎ አድራጎት ተግባራት እንዲውል።

  - 200,000 ዩሮ በቅድስት መንበር አስተባባሪነት ለሚደረገው የበጎ አድራጎት ተግባር እንዲውል ተወስኗል ።

ካርዲናል ሳንቶስ አብሪል ያ ካስቴልሎ የካርዲናሎች ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት በመግቢያው ላይ እንዳስታውሱት፣ “እ.አ.አ በ2022 የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) ለተፈፀመው ግፍ ፍትህን ለመፈለግ ያቀረበው የመጀመሪያው የህግ ሂደት ተጠናቋል። በተጨማሪም በህግ ፊት ኢንስቲትዩቱ በመጨረሻው የተዘረፉ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተመልሶ ገቢ እንዲሆን መደረጉ ጠቃሚ ስኬት አስመዝግቧል ፣ ይህም ባለፉት ጊዜያት የኢንስቲትዩቱን ገጽታ ያበላሹትን እስከ መጨረሻው ለማሳደድ ያለውን ፍላጎት ያረጋግጣል ። እነዚህ በቫቲካንም ሆነ በውጭ አገር ያሉ ግልጽ ሂደቶች ናቸው። እ.አ.አ ከ2014 በፊት ከኢንስቲትዩቱ በህገ ወጥ መንገድ የተወሰደ 17,229,882 ዩሮ ከረዥም የህግ ሂደት በኋላ ተመልሷል።

የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) ዋና የበላይ ጠባቂ የሆኑት የኔታ ባቲስታ ሪካ ማስታወሻዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ  “ተቋሙ በጣም ትልቅ እና የበለጠ አስፈላጊ አካል እንደሆነ እና ይህ አካል የገንዘብ ዓለም ሳይሆን የቅድስት መንበር እንደሆነ ግንዛቤ ነበር። ይህ ግንዛቤ በድርጊት ነፃ የመሆንን እና ከማንኛውም መደበኛ ሁኔታ ነፃ የመሆንን ሀሳብ በከፍተኛ ደረጃ ከፍ አድርጎታል። ከዚህም በላይ ቀደም ባሉት ጊዜያት የተከሰቱት እውነተኛ አደጋዎች ዓይኖቻችንን ለመክፈት ምንጊዜም ዝግጁ እንድንሆን አድርገውናል” ብሏል።

በአስተዳደር ዘገባው ውስጥ የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) ፕሬዝዳንት ዣን ባፕቲስት ደ ፍራንሷ እንደ ገለጹት “እ.አ.አ በ2022 የኢንስቲትዩቱ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ተመልክቷል፡ የኢንቨስትመንት አስተዳደር ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣ የስነምግባር ፖሊሲዎች መስፋፋት፣ አዲስ የአይቲ መድረክን ማስተዋወቅ፣ ተጨማሪ ባለሙያዎችን መቅጠር እና ግልጽ እና የተዋቀረ የስራ አፈጻጸም ላይ የተመሰረተ የክፍያ ስርዓት የሚያስተዋውቅ 'የሰራተኞች ግምገማ እና ማበረታቻ ስርዓት' ፖሊሲ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ብሏል።

በሪፖርቱ የክዋኔ መረጃ ክፍል ውስጥ የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት (በተለምዶ የቫቲካን ባንክ በመባል የሚጠራው ተቋም) ዋና ዳይሬክተር ጂን ፍራንኮ ማምሚ እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 31 ቀን 2022 ጀምሮ “የባንኩ የሂሳብ መዝገብ ንብረቶች 2.8 ቢሊዮን ዩሮ ነበር” ሲሉ ዘግቧል። ማምሚ ለቫቲካን መገናኛ ብዙሃን እንዳስረዱት “በዚህ የባንክ ዘርፍ ውስጥ እርግጠኛ ባልሆነበት ወቅት የቫቲካን ባንክ ከፍተኛ የካፒታል ጥንካሬ እና ጠንካራ ፈሰት ያለው ነው” በማለት መለኪያዎች “ከቁጥጥር መስፈርቶች በጣም የላቀ ነው ፣ ይህም በዓለም አቀፍ ካሉ በጣም ጠንካራ ተቋማት ውስጥ አንዱ ያደርገዋል" ሲሉ ተናግሯል።

ዋና ስራ አስኪያጁ በመቀጠል "በአጠቃላይ የባንክ እና የኢንቨስትመንት አገልግሎቶችን በስፋት በማስፋፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን እና ተፈላጊ ደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት ተችሏል ያሉ ሲሆን ይህ ሊሆን የቻለው ኢንስቲትዩቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳዲስ የፈጠራ መድረኮችን እና ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በዲጂታላይዜሽን ላይ ኢንቨስት ማድረጉን በመቀጠሉ ነው ብሏል።

በመጨረሻም ማሚ እንዳስታወሱት ከሆነ “የሃይማኖት ሥራዎች ኢንስቲትዩት በዓለም ላይ በቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎት ላይ የሚገኝ ብቸኛው የገንዘብ ተቋም እንቅስቃሴውን በካቶሊክ ሥነምግባር ላይ የተመሠረተ እንጂ ከፍተኛውን ትርፍ በሚያስገኝ መርህ ላይ የተመሠረተ አይደለም። ዓለም አቀፍ የባንክ ደረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማክበር ላይ ይገኛል” ብሏል።

07 June 2023, 12:48