ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባዘጋጀው መድረክ ላይ 

ቅድስት መንበር ወንድማዊ ማኅብረሰብን በእውነተኛ ውይይት መገንባት እንደሚገባ ገለጸች

ቅድስት መንበር በቤተ እምነቶች እና በባሕሎች መካከል የውይይት መኖር አስፈላጊነትን አስመልክቶ በኒውዮርክ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ ላይ፥ በምሥራቁ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ግንኙነት መፍጠር እንደሚገባ ገለጸች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በኒውዮርክ በሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ፥ "ሰላም እና አንድነትን ለማስፈን በሕዝቦች መካከል ግንኙነት ማበጀት የኃላፊነት ግዴታ ሆኗል" ብለዋል።

ኒውዮርክ በሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ እንደ ራሴ እና ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ሰኔ 7/2015 ዓ. ም. በተዘጋጀው መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በልዩ ልዩ ሃይማኖቶች ምዕመናን መካከል ያለውን አዎንታዊ ግንኙነት በምሕረት ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ውይይት እንደሆነ ይመለከቱታል” ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል አክለውም፥ በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ የጋራ ውይይት የጋራ እሴቶቻችንን እንድናውቅ ያስችለናል" ብለዋል።

አቡነ ገብርኤል በማጠቃለያቸው፥ መድረኩ በእውነተኛ ውይይት ላይ በተመሠረተ የወንድማማችነት ጎዳና ላይ ለመጓዝ እንደሚረዳ ተስፋ በማድረግ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

17 June 2023, 17:22