ፈልግ

“ቼንቴዚሙስ አኑስ” የተሰኘ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን ምሥረታ 30ኛ ዓመት መታሰቢያ “ቼንቴዚሙስ አኑስ” የተሰኘ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን ምሥረታ 30ኛ ዓመት መታሰቢያ  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ካርዲናል ፓሮሊን፥ የወቅቱ ቀውሶች ዓለም አቀፋዊ እና ወንድማዊ ምላሾችን የሚሹ መሆናቸውን ገለጹ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን “ቼንቴዚሙስ አኑስ” የተሰኘ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን ምሥረታ 30ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የሁለት ቀን በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በቫቲካን ውስጥ ሰኞ ግንቦት 28/2015 ዓ. ም. በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ ለተገኙት እንግዶች ባደረጉት ንግግር፥ እርስ በእርስ በመገናኘት ባሕል እና ለጋራ ጥቅም ድምጽ የመስጠት አስፈላጊነት ላይ ትኩረት በማድረግ በዓሉን መርቀው ከፍተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“እርግጠኝነት የጎደለው ዓለማችን መጠጊያን ለሚፈልጉ እና ሌሎች ችግሮች ትኩረት ባለመስጠቱ የተነሳ የዘመኑን ምልክቶች አንብቦ ምላሽ ለመስጠት ከምንጊዜውም በላይ ጥረት ማድረግ አለብን” ብለው፣ ስልጣንን የመተው ፈተና ፖለቲከኞችም ሊመርጡት የሚችሉት አደጋ መሆኑን ጠቁመው፣ ፖለቲከኞች በጋራ ጥቅም ራዕይ ላይ ከማተኮር ይልቅ በግል ፍላጎቶች ላይ እንዲያተኩሩ ሊገፋፉ እንደሚችሉ አስረድተዋል። ይህን አለማድረግ በድጎማ ላይ ላልተመሠረቱ አቀራረቦች እንደሚመራ እና ከሩቅ ላሉ ሰዎች በሚጨነቅ ዓለም አቀፍ ተብለው በሚገለጹ ውሳኔዎች ላይ የሚመሠረት መሆኑን ተናግረው፥ ቀጥለውም ወደ ከፍተኛ አንድነት እና ውህደት የሚመሩ ሁለት ነገሮች እንዳሉ፥ እነርሱንም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ማኅበራዊ ወዳጅነት” እና “የግንኙነት ባኅል” በማለት አጥብቀው የሚናገሯቸው ናቸው ብለዋል።

የሰላም ጥሪዎች ብቻቸውን በቂ አይደሉም

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊው ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን “ቼንቴዚሙስ አኑስ” የተሰኘ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን የተቋቋመበትን 30ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተናገሯቸው ሁለት ዋና ዋና እሴቶች ላይ ትኩረት አድርገዋል። የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በቫቲካን ውስጥ በሚገኝ ቀሌመንጤዎስ አዳራሽ ውስጥ ለተሰበሰቡት ታዳሚዎች ባደረጉት ንግግር፥ “ማኅበረሰብ” በሚለው ቃል ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን የስብሰባው መሪ ርዕሥም “የወደፊት ጊዜን ለመገንባት ከማኅበረሰብ አንፃር ማሰብ እና መተግበር” የሚል እንደነበር ተመልክቷል። ብጹዕነታቸው ለታዳሚዎቹ ባደረጉት ንግግር፥ "በአሁኑ ጊዜ ችግሮቹ እና መፍትሄን ማፈላለጉ ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚጠበቁት፣ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው እና እንደዚሁም ዓለም አቀፋዊ ምላሾችን የሚጠይቅ መሆኑን ማንም ሊገነዘበው የሚቻለው ነው" ብለዋል። እናም “ለኅብረተሰብ ጥቅም በጋራ ለመሥራት የሰላም ጥሪዎች፣ ኤኮኖሚያዊ ዕድገቶች ወይም አካባቢን የመጠበቅ እና የማክበር ጥሪዎች ብቻቸውን በቂ አይደሉም” ብለዋል።

ሁለቱ እሴቶች

“የጋራ ጥቅም ጽንሰ-ሀሳብን” መረዳት እና ምናልባትም መካተት አለበት ብለው፥ በሰዎች መካከል መገለልን ሊያስከትሉ ወይም መጥፎ እድሎችን ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ልዩ መፍትሄዎችን የሚያራምዱ ፖሊሲዎችን ወይም ተግባራትን ማስወገድ ይገባል ብለዋል። “ስለዚህም ማኅበራዊ ወዳጅነት እና የግንኙነት ባሕል፣ ተጨባጭ የጋራ ጥቅምን ለማሳካት ጠቃሚ አመለካከቶችን የሚያቀርቡ በመሆናቸው ሁለቱም ክፍት እና የወደፊት ተኮር ማኅበረሰብ መለያዎች ናቸው” በማለት አስርድተዋል። “ማኅበራዊ ወዳጅነት በተፈጥሮው ሁሉን አቀፍ እና በራሱ ማኅበረሰብ ወይም የትውልድ ሀገር ላይ ያልተገደቡ እንቅስቃሴዎችን ለማቀድ እንደሚረዳ፥ የግንኙነት ባሕል መድልዎን እንደሚያስወገድ ለማሳመን ከሚቀርቡ አታላይ የበጎ አድራጎት ተግባራት ማነቃቂያ በመራቅ፥ ይልቁንም የሁሉንም ሰው ክብር እና ነፃነት እንዴት ማክበር እንደሚገባ የሚያውቅ የአኗኗር ዘይቤ ነው” በማለት አስረድተዋል።

የሰዎች ሁሉ መረጋጋት

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1991 ዓ. ም. ይፋ የሆነው እና  በላቲን ቋንቋ “ቼንቴዚሙስ አኑስ” ወይም ሲተረጎም መቶኛ ዓመት የሚለው የቀድሞው ር. ሊ. ጳ. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሐዋርያዊ አስተምህሮ በታሪክ ውስጥ “እንደ ዴሞክራሲ እና ነፃነት ላሉ እሴቶች ትልቅ ጠቀሜታ” እንዳለው ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ገልጸው፥ አሁን ባለው ሁኔታም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” ባሉት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው፥ እንደ ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣ ፍትህ ወይም አንድነት የሚሉት ቃላት ታጠፈው እና ተቀርጸው የግዞት መሣሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረቡ ማንኛውንም ትርጉም የለሽ ድርጊት መለያን በማስረዳት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል አስረድተዋል።

ዛሬ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ውሳኔ ሰጪዎች ራሳቸውን የሚመዝኑባቸው “እሴቶች” በመዳከማቸው ጠቅላላ ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለመጠበቅ ጥንቃቄ የተሞላበት ማስተዋልን ይጠይቃል ብለዋል። የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፣ በመሠረቱ ውሳኔዎችን እና የጋራ ሃብቶችን የሚመራው “ኃላፊነት ነው” ብለው፥ “የሰው ልጆች በሙሉ ዕድገታቸው እና ምኞታቸው የተመሠረተው በክብራቸው እና በማንነታቸው ላይ ነው” በማለት አስረድተዋል።

06 June 2023, 15:31