ፈልግ

የሲኖዶሳዊ ጉዞ ዓርማ የሲኖዶሳዊ ጉዞ ዓርማ 

የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሲኖዶሱን የሥራ ሠነድ አጸደቀ

መደበኛ ጉባኤው የሲኖዶሱን የመጀመሪያ ጉባኤ የሥራ ሰነድን እና የአሠራር መንገድን አጸደቀ። በያዝነው ሳምንት ውስጥ በታላቅ የወንድማማችነት ድባብ፣ የጸሎት ጊዜ እና የግል አስተያየቶች በቀረቡበት የቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በሮም ተገናኝቶ በጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ የሥራ ሰነድ ላይ ውይይት አካሂዷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ሊታተም የተዘጋጀው የሥራ ሰነዱ በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር በሚካሄድ ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ለውይይት እንደሚቀርብ፣ በኋላም ጉባኤው ለሁለተኛ ዙር ውይይት የሚሰበሰብ መሆኑ ታውቋል። በስብሰባቸው ወቅት የምክር ቤቱ አባላት ከተለያዩ አማካሪዎች ጋር በመሆን የሥራ ሰነዱን ከገመገሙ በኋላ አሻሽሎ በማጽደቅ በመጪው ጉባኤ ላይ የሚቀርብ የአሠራር መንገድንም ወስኗል።

ለጠቅላላ ጉባኤ የሚረዳ መንፈሳዊ ዝግጅት

ተሳታፊዎቹ በተለይም በጉባኤው ወቅት በሚደረግ ሱባኤ፣ መንፈሳዊ ዝግጅቶች እና አስቀድሞ በዋዜማው በሚቀርብ የአብያተ ክርስቲያናት የጋራ ጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይም ተወያይቷል። “በአንድነት ለ 2023 ዓ. ም.” የሚለው ተነሳሽነት የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰሙበት ጊዜ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እና የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች ወጣት ተወካዮችን ለምስጋና እና ለጸጥታ ጸሎት ለማሰባሰብ ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል። ተጨማሪ መረጃን  www.together2023.net ከሚለው ድረ-ገጽ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

የሲኖዶሱ ጠቅላላ ጉባኤ የሲኖዶሱን የአከባበር ሂደትንም የተመለከተ ሲሆን፣ ከመጀመሪያው የዝግጅት ምዕራፍ አንስቶ በልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መመካከርን እና ተከትሎም የማስተዋል ደረጃዎችን ያካተተው ቀጣይነት ያለው ሂደት እንደሆነ ታውቋል። ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በገለጻው፣ በሚቀጥለው ዓመት በጥቅምት ወር በሚካሂደው ጉባኤ መሠረት የሚሆነው የሥራ ሠነዱ በሁሉም የቤተ ክርስቲያን እርከኖች የተካሄደ የማዳመጥ ሂደት ፍሬ መሆኑን አስረድቷል።

13 May 2023, 17:16