ፈልግ

በአውሮፓውያኑ 2023 የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል አርማ በአውሮፓውያኑ 2023 የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል አርማ 

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፌስቲባል ባልደረባ ብጹዓን ይፋ ሆኑ

የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት በየትኛውም ዘመን የሚገኙትን ወጣቶች እንደሚሞላ እና እንደሚያድን፣ በአውሮፓውያኑ 2023 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የሚደግፉ አሥራ ሦስቱ ባልደረባዎች መመስከራቸውን፣ የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል፣ ግንቦት 10/2014 ዓ. ም. ይፋ ባደረገው መግለጫው አስታውቋል። ጋዜጣዊ መግለጫው መሠረቱን ያደረገው በዓሉ የሚከበርበት የሊዝቦን ከተማ ፓትርያርክ ብጹዕ ካርዲናል አማኑኤል ክሌሜንቴ፣ በቅዱስ ጳውሎስ አሳታሚ ድርጅቶች ለሚያሳትሙት አዲስ መጽሐፍ በላኩት የመግቢያ ገጽ ጽሑፍ እንደሆነ የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ለዘመናችን የሚሆኑ አሥራ ሦስት የቅድስና መብራቶች፣ ከሐምሌ 25 – 30/ 2015 ዓ. ም. ድረስ በፖቱጋል ሊዝበን ከተማ ሊካሄድ የታቀደውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ለወጣቶች የጠቆማቸው መሆኑ ታውቋል። እያንዳንዱ የፖርቱጋል ሀገረ ስብከት፣ በየሀገረ ስብከቱ አውድ ዋቢ የሚሆኑ ቅዱሳንን መምረጡ ታውቋል። ይህም በ2015 ዓ. ም. በፖርቱጋል ሊዝቦን ከተማ በሚከበር ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ወጣቶች እንዲገኙ ለመርዳት መሆኑ ታውቋል።

ኢየሱስን ወደ ዓለም ሁሉ መውሰድ

ወጣቷ ድንግል ማርያም፣ የእግዚአብሔር ልጅ እናት መሆንን በጸጋ የተቀበለች መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን፣ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ሌሎች ዘንድ በማምጣት፣ የእርሱን የመዳን መልካም ዜናን በመጠባበቅ ላይ በሚገኝ ዓለም ውስጥ አርአያ መሆኗ ይታወቃል። ከእምነት ጀግኖች መካከልም ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፌስቲቫልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቁት የቀድሞ ር. ሊ. ጳ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሲገኙ፣ ቅዱስ ዶን ቦስኮ፣ ቅዱስ ቪንሴንት፣ የስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዲያቆን እና ሰማዕት ከዚያም ከሊዝበን ከተማ ተነስተው ወንጌልን ለዓለም ለማድረስ የተጉ ቅዱሳን፣ ቅዱስ አንጦኒዮስ፣ የሰማዕታቱ ቅዱስ፣ ቅዱስ ቤርቶሎሜዎስ እና የብሪቶ ቅዱስ ጆቫኒ ይገኙባቸዋል።

የሊዝቦን ከተማ ብጽዓን ወጣቶች

በ 2015 ዓ. ም. የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የሚሳተፉ ወጣቶች፣ እንደ ፖርቱጋላዊቷ ዮሐን፣ ከዘውድ ይልቅ የገዳም ሕይወትን የመረጠችው የንጉሥ አልፎንሶ አምስተኛ ሴት ልጅ፣ እ. አ. አ በ 1570 ዓ. ም. በሚስዮናዊነት ወደ ብራዚል ሲሄድ በካናሪ ደሴቶች ማዶ ሰማዕት የሆነው ወጣት ጆቫኒ ፈርናንዴዝ፣ የሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጅ ማሪያ ክላራ ጨምሮ፣ ወላጅ አልባ ለሆኑ እና ለተረሱት ሕጻናት "እናት" ለመሆን የወሰነች፣ የንፅህት ቅድስት ማርያም ፍራንሲስካውያን የሕክምና ማኅበር መሥራች ወጣት፣ የሊዝቦን ከተማ ብጽዓን ወጣቶች መሆናቸው ታውቋል።

 የዘመናችን ብጹዓን ወጣቶች

በመጨረሻም፣ የቅድስና ሂደቱ እየተካሄደ የሚገኘው ብፁዕ ፒየር ጆርጆ ፍራሳቲ ከሊዝቦን ከተማ ብጹዓን መካከል አንዱ ሲሆን፣ ተራሮችን እየወጣ ድሆችን እያገለገለ በ24 ዓመቱ በቱሪን ከተማ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ወንጌልን በደስታ፣ በታታሪነት እና በበጎነት ሲያገለግል የኖረ መሆኑ ይታወሳል። እ. አ. አ በ1945 ዓ. ም. በማውታዘን ማጎሪያ ካምፕ የሞተው ብፁዕ ማርቼሎ ካሎ፣ ብጽዕት ኪያራ ባዳኖ እና ብጹዕ ካርሎ አኩቲስ በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል የሐዋርያነት አገልግሎታቸውን ያበረከቱ፣ በዘመናችን ብሩህ የሆኑ የእምነት ምስክርነቶችን በመስጠት፣ መከራን ከተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የኖሩ መሆናቸው ይታወቃል።

19 May 2022, 18:08