ፈልግ

ሮም በሚገኝ ቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ የተካሄደ የማታ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት ሮም በሚገኝ ቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ የተካሄደ የማታ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት 

የሊዮኑ ኢሬኔዎስ የዶክተርነት ማዕረግ ለክርስቲያኖች አንድነት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ

በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ሕብረት ማጠናከሪያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ፣ ሮም በሚገኝ ቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ በተካሄደው የማታ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ብጹዕ ካርዲናል ኮክ ለክርስቲያኖች አንድነት በተዘጋጀው የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ወደ ሙሉ አንድነት የሚያቀርበን “በእግዚብሔር ምስጢር ፊት ለመንበርከክ የሚያስችል” ሥነ-መለኮታዊ መንገድ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ወደ ዓለማችን የገባው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁላችንንም የሚነካ እና የበለጠ ጥልቅ በሆነ ጸሎት ላይ እንድንተባበር ያደርገናል” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ኮክ፣ “ጨለማውን ለማብራት የሚያስችል ብርሃን ለማግኘት በፍቅር ስሜት መቀስቀስ ያስፈልጋል” ብለዋል። የክርስቲያኖችን አንድነት የሚያበረታታ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ፣ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ በዓል ሁለተኛ ምዕራፍ ማብቂያ ለክርስቲያኖች አንድነት በተዘጋጀው 55ኛው የጸሎት ሳምንት መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር አድረገዋል። ብጹዕ ካርዲናሉ በንግግራቸው፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስጊ እና አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ጊዜ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ ተገኝተው የጋራ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት በመምራታቸው ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። በመቀጠልም በመካከለኛው ምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት የተመረጠው እና “ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ለእርሱ ልንሰግድለት መጣን” የሚለውን የዘንድሮ የክርስቲያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት መሪ ሃሳብ አስታውሰው፣ “ዛሬም ታላቅ የጨለማ ጊዜን እያቋረጠ የሚገኘውን የእስያ አህጉርን” በጸሎታቸው አስታውሰዋል።  

ወደ ክርስቶስ ተመልሶ በአንድነት እድገት

ብፁዕ ካርዲናል ኮክ፣ ሰብዓ ሰገል “የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ የሚያበስር ኮከብ ተከትለው ጉዞ እንደ ጀመሩ ሁሉ፣ ክርስቲያኖችም የግል ኮከባቸውን ካልተከተሉ በቀር በአንድነት ጎዳና ላይ ሊራመዱ እንደማይችሉ፣ አንድ ላይ ሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን የሚመልስ እና ወደ ሙሉ አንድነት የሚያቀርብ “በእግዚብሔር ምስጢር ፊት መንበርከክ የሚያስችል” ሥነ-መለኮታዊ መንገድ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል። “እኛ ክርስቲያኖች አንድነትን የምናገኘው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን፣ በደቀ መዛሙርቱ አንድነት ለመመራት ስንፈቅድ ብቻ ​​ነው” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ኮክ አክለውም፣ የክርስቲያኖች አንድነት እንቅስቃሴ ተገልጦ የማይታይ ቢሆንም በተለያዩ አገሮች እና አህጉራት ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት አብረው የሚጸልዩበት ገዳም” መሆኑን አስረድተዋል።

የሊዮኑ ቅዱስ ኢሬኔዎስ የክርስቲያኖች አንድነት ምልክት ነው

በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ኅብረት ማጠናከሪያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፣ ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ በመጨረሻም፣ በአንድነት እና በእርቅ መንገድ መጓዝ እንዲቻል ላደረጉት የማያቋርጥ ድጋፍ ርዕሠ ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን አመስግነው፣ ለሊዮኑ ኢሬኔዎስ “ዶክተር ዩኒታቲስ” የሚል መጠሪያ በመስጠት የቤተክርስቲያን ዶክተር ብለው በማወጀቸው ምስጋናቸውን በድጋሚ አቅርበውላቸዋል። ለብጹዕ ካርዲናል ኮክ ይህ የቅዱስነታቸው ማበረታቻ ለክርስቲያኖች አንድነት የተስፋ ምልክት” እንደሆነ ታውቋል። 

26 January 2022, 14:08