ፈልግ

ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር መቃውም እንደሚያስፈልግ፣ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር መቃውም እንደሚያስፈልግ፣ 

አውቶማቲክ የጦር መሣሪያዎች የሰውን ልጅ ሕሊና እና መርሆዎች የሚጻረሩ ናቸው

ጀኔብ በሚገኝ በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ፣ አውቶማቲክ የጦር መሣሪያዎችን መጠቀም የሰውን ልጅ ሕሊና እና መርሆዎች የሚጻረር መሆኑ አስታወቀ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅድስት መንበር አውቶማቲክ የጦር መሣሪያዎችን በማስመልከት ከዚህ በፊት በተደረጉት ውይይቶች ተቃውሟን ስታሰማ መቆየቷን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎች የሚያቀርቡት ተግዳሮቶች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ መስክ ብቻ ሳይገደብ በሰላም እና መረጋጋት ጥረት ላይ ከባድ እንድምታዎች እንዳሏቸው ቅድስት መንበር በየጊዜው ስታሳስብ መቆየቷን በመንግሥታቱ ድርጅት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ልኡካን አስታውቋል።

የቅድስት መንበር ልኡካን እ. አ. አ በ2021 ዓ. ም በጀኔቭ ባደረገው አውቶማቲክ የጦር መሣሪያ ስርዓቶች ላይ ከተደረገው የኤክስፔርቶች ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫ፣ በተወሰኑ የጦር መሣሪያዎች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል። ሆኖም ግን በቅድስት መንበር እንደተገለጸው፣ የውይይቱ አጀንዳ ሰብአዊ መብቶችን ያካተተ ዓለም አቀፍ ሕግ ገጽታ ያለው እንደነበር እና በሦስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በመመርኮዝ የራሷን አስተንትኖ በማዳበር ያቀረበች መሆኗ ታውቋል።

ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግን ያክብሩ

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ ስምምነቶች በጥንቃቄ በተገለጹ መግለጫዎች የተሞሉ ሲሆኑ፣ ለምሳሌ በመልካም እምነት እና ጥንቃቄ የተሞላ ፍርድ መሠረታዊነት የሚያመለክት “አላስፈላጊ ጉዳት እና ሥቃይ” የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል።

እነዚህ ገጽታዎች በከፊል የሰዎች ምክንያታዊ ጣልቃ ገብነትን የሚጠይቁ ድርጊቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ለመርሆዎች የሚሰጥ አክብሮት እና አተገባበር ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ ሆነው የሚታዩ መንገዶችን ማወቅ እና ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘትን ይጠይቃል። ሕጋዊ እና ሥነ ምግባራዊ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ፣ የሕጎቹንም መንፈስ ለማዳን ብዙውን ጊዜ የሕጎቹን ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ እንደሚጠይቅ ይታወቃል። በዚህ ረገድ ፣ በራስ የመማር ወይም ራስ-ተኮር ችሎታዎች የተላበሱ የራስ ገዝ የጦር መሣሪያ ስርዓቶች ፣ ለተወሰነ ያልተጠበቀ ደረጃ ቦታን መተው አለባቸው። ለምሳሌ ውጤታማነትን ለማሳደግ በውጊያ ላይ ባልተሳተፉ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ እርምጃዎች መርህ መጣስ የሚል ይገኝበታል።

ስለዚህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ መልዕክተኛ ቡድን ድሮንን የመሳሰሉ አነስተኛ እና የራስ-ገዝ ችሎታ ያሏቸው የጦር መሣሪያ ሥርዓቶች የመከተል ዕድል ላይ ተወያይቷል። እነዚህ ጦር መሣሪያዎች ቀጥተኛ ባልሆነ የሰዎች ቁጥጥር የሚሰሩ ከሆነ የታለመውን ኢላማ በመሳት ስህተት ሊሠሩ ይችላሉ።  ያለ ሰው ቁጥጥር የሚንቀሳቀስ የጦር መሣሪያ ጽንሰ-ሀሳብ አደጋውን የበለጠ ያባብሰዋል። ዓለማቀፉን የሰብአዊ ሕግ በግልጽ የሚቃረን በመሆኑ የጦር መሣሪያው ጉዳቶችን በማስከተል አድሏዊ ውጤቶችን ሊያመጣ ይችላል።

የጦር መሣሪያን በሰው ሰራሽ አእምሮ መጠቀም ይቁም

ቅድስት መንበር የምትከተለው ይህ አቅጣጭ በታዋቂ ሳይንቲስቶች፣ በመሐንዲሶች፣ በተመራማሪዎች፣ በወታደራዊ ባለሥልጣናት፣ በሥነ-ምግባር እና በሰፊው የሲቪል ማኅበረሰብ መካከልም ከፍተኛ ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ ታውቋል። በሥነ-ምግባር ምክንያቶች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ የተወሰኑ ፕሮጄክቶችን የሚቃወሙ የሰራተኞች እና ሥራ ፈጣሪዎች ጉዳይ እየበዛ መምጣቱን፣ በመንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ መልዕክተኛ ቡድን አስታውቋል። እያደገ የመጣው የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በእርግጥ በሕዝባዊ ግንዛቤ ላይ ለውጥን በማምጣት በዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ አፈፃፀም እና ልማት ላይም አንቀሳቃሽ ኃይል ይሆናል።

በራስ ኃይል የሚንቀሳቀስ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶች ስታትስቲካዊ ትርጉም እንደተለመደ ተደርጎ በመቆጠር ተቀባይነት ያለው ተደርጎ ሊወሰድ ቢችልም ፣ በግልጽ ባይከለከልም ፣ በሥነ ምግባር ፣ በመንፈሳዊ እሴቶች ፣ በልምድ እና በወታደራዊ ድንጋጌዎች እንደተከለከሉ ይቆያሉ በማለት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ መልዕክተኛ ቡድን አስታውቋል።

07 August 2021, 16:43