ፈልግ

የ10ኛው የዓለም የቤተሰብ ቀን ስብሰባ አርማ ይፋ ሆነ። የ10ኛው የዓለም የቤተሰብ ቀን ስብሰባ አርማ ይፋ ሆነ። 

ቫቲካን ለዓለም የቤተሰብ ስብሰባ የተመረጠውን አርማ ይፋ አደረገች!

ለመጪው የዓለም የቤተሰብ ስብሰባ የሚሆን ኦፊሴላዊ አርማ ቫቲካን ይፋ ማድረጓ የታወቀ ሲሆን ይህ በአባ ማርኮ ኢቫን ሩፕኒክ የተሰራው አርማ በቃና ዘገሊላ የተደረገውን ሠርግ ከግምት ውስጥ ያስገባ አርማ እንደ ሆነም ተገልጿል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 10 ኛው የቤተሰብ ስብሰባ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዝግጅቱ ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ እ.አ.አ ከሰኔ 22 እስከ ሰኔ 26/2022 ዓ.ም ድረስ በሮም ከተማ ውስጥ ይካሄዳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ያለው ምስጢራዊ የተቀደሰ ፍቅር በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያኑ መካከል ያለው የማይፈታ ፍቅር እና አንድነት ነፀብራቅ ነው - ኢየሱስ ደሙን ለእሷ አፍሷልና” የሚለው መሪ ቃል ከአሥረኛው የዓለም የቤተሰብ ስብሰባ ኦፊሴላዊ አራማ በስተጀርባ ያለው ትርጉም ነው።

“ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው” የሚል ርዕስ ያለው ለዓለም የቤተሰብ ስብሰባ ይሆን ዘንድ ይፋ የሆነው አርማ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች ከጻፈው መልእክቱ 5፡32 ላይ የተወሰደ ሲሆን የስነ -መለኮት ትምህርት ምሁር እና አርቲስት በሆኑ የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል አባት ማርኮ ኢቫን ሩፕኒክ እንደ ተዘጋጀ ተገልጿል።

አርማው በቃና ዘገሊላ ተደርጎ የነበረውን ሰርግ የሚያንጸባርቅ ሲሆን ከሙሽራው እና ሙሽሪት በስተጀርባ በግራ ጎን ያለው ስፍራ በመጋረጃ ተሸፍነዋል። ማርያም ልጇ ለሆነው ለኢየሱስ “የወይን ጠጅ እኮ አለቀባቸው” ባለችበት ሰዓት ኢየሱስ እና ማርያም አንድ ሆነው ይታያሉ። በፊት ለፊቱ ላይ የቅዱስ ጳውሎስ የፊት ገጽታ ጥንታዊ በሆነ የአሳሳል ዘይቤ ተስሎ የምናገኝ ሲሆን በእጁ መጋረጃውን የሚያከፍተው እና “ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው” በማለት ስለሠርጉ የሚናገረው ቅዱስ ጳውሎስ ነው፣ እኔ ግን የምናገረው ስለክርስቶስ እና ስለቤተክርስቲያን ጥምረት ነው!” በማለት የአርማው ሰዓሊ እና የስነ -መለኮት ትምህርት ምሁር እና አርቲስት የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል አባት ማርኮ ኢቫን ሩፕኒክ ተናግረዋል።

ይህ አባ ማርኮ ይፋ ይዳረጉት አርማ ለእርሳቸው ሦስተኛው ኦፊሴላዊ የሆነ አርማ ነው። ከኦፊሴላዊው ጸሎት እና አርማ ጋር እ.አ.አ 2022 ዓ.ም ለሚካሄደው የዓለም የቤተሰብ ስብሰባ እንዲረዳ ታስቦ ይፋ የሆን አርማ ሲሆን በቤተሰብ ሕይወት ላይ ለማሰላሰል እና ለቤተሰብ የሚደርገው ሐዋርያዊ የሆነ እንክብካቤ ላይ የማሰላሰያ መሳሪያ ይሆን ዘንድ ታስቦ ይፋ የሆነ ነው።  ዝግጅቱን በቫቲካን የቅድስት መንበር የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት ጉዳዮችን በበላይነት በሚከታተለው ጳጳሳዊ መክር ቤት እና የሮም ሀገረ ስብከት ጋር በትብብር የሚዘጋጅ የዓለም የቤተሰብ ስብሰባ ሲሆን በላቲን ቋንቋ “አሞሪስ ላቲሲያ” (የፍቅር ሐሴት) በሚል አርዕስት የዛሬ ስድስት አመት ገደማ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር በመግለጽ ይፋ ያደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት ስድስተኛ ዓመት የሚዘከርበትን ቀን ምክንያት በማደረግ እና እንዲሁም አሁንም በላቲን ቋንቋ “Gaudete et exsultate” (ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርዕስት ቅዱስነታቸው ይፋ አድርገው በነበረው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ላይ የተመረኮዙ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደ ሚከናወኑ ከወዲሁ ተገልጿል።

አሥረኛው የዓለም የቤተሰብ ስብሰባ እንደ “ሁለገብ እና ስፋ ያሉ ቅርጾችን” በመያዝ የተለያዩ ልኬቶችን በመጠቀም ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ቀመሮችን እንደ ሚያካትት ከወዲሁ እየተገለጸ ይገኛል። የሮም ከተማ ዋናው የስብሰባው ማዕከል ቦታ ትሆናለች ፣ ነገር ግን በዓለም አቀፉ የቤተስበ ስብሰባ የቤተክርስቲያን ዝግጅት ቀናት እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ለራሱ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች አካባቢያዊ በሆነ ደረጃ ስብሰባዎችን ማደረግ ይችላል። በዓለም ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ቤተሰብ ዋና ተዋናይ ሊሆን ይችላል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የስብሰባውን ያልተለመደ መልክ ባቀረቡበት እ.አ.አ ባለፈው ሐምሌ 2/2021 ዓ.ም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት “ወደ ሮም መምጣት የማይችሉትን ጨምሮ ሁሉም ሰው መሳተፍ ይችላል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸው ይታወሳል። ብፁዕ አባታችን እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት  ማኅበረሰቦችን በተቻለ መጠን በማንቀሳቀስ የስብሰባውን ጭብጥ መሠረት በማድረግ ተነሳሽነቶችን እንዲያቅዱ አሳስበዋል - “የቤተሰብ ፍቅር - ጥሪ እና የቅድስና ጎዳና” እንደ ሆነም አክለው መግለጻቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ አክለው እንደገለጹት “ይህንን ከቤተሰቦች ጋር በማደራጀት ተለዋዋጭ ፣ ንቁ እና የፈጠራ ችሎታ እንዲኖራችሁ እጠይቃለሁ” ማለታቸውም የሚታወስ ሲሆን “ይህ ከትዳር አጋሮች ፣ ከቤተሰቦች እና ከቀሳውስት ጋር ለቤተሰብ አገልግሎት በጋለ ስሜት ራሳችንን የምናቀርብበት አስደናቂ አጋጣሚ ነው” በማለት መናገራቸውም ይታወሳል።

30 July 2021, 15:02