ፈልግ

የቫቲካን የጠፈር ምርመር ማዕከል የዓለማችን ጠፈር እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል ማለቱ ተገለጸ! የቫቲካን የጠፈር ምርመር ማዕከል የዓለማችን ጠፈር እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል ማለቱ ተገለጸ! 

የቫቲካን የጠፈር ምርመር ማዕከል የዓለማችን ጠፈር እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል ማለቱ ተገለጸ!

የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ ስለ አዲስ የጠፈር ድንበሮች፣ የጠፈር ጉዞ እና የጋራ ቤታችን የሆነችውን አለማችንን ሙሉ በሙሉ የመንከባከብ አስፈላጊነትን በተመለከተ ሊደርጉ ስለሚገባቸው እንክብካቤዎች መናገራቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ሚዲያዎች የሚያቀርቧቸው አርዕስተ ዜናዎች በጠፈር ተመራማሪዎች እና በሕዋ አፍቃሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጠፈርን ለመጎብኜት ፍላጎት እያሳዩ የመጡ በርካታ ቱሪስቶች ወደ ጠፈር ለመሄድ እያቀረቡት የሚገኘው ጥያቄ በመጨመሩ የተነሳ በዘርፉ የሚደርገው ከፍተኛ የሆነ የንግድ ውድድር መጨመሩን እየዘገቡ እንደ ሆነ ለመረዳት ይቻላል።

በሐምሌ ወር ውስጥ ብቻ ሁለት የጠፈር ኩባንያዎች ጠፈርን ለመጎብኘት ፍላጎቱ እና አቅም ላላቸው ሰዎች ፍላጎታቸውን እውን ለማደረግ ይቻል ዘንድ የሚረዱ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ፣ የተለያዩ የማስታወቂያ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።  እ.ኤ.አ. ከ 2022 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጠፈር ለምካሄዱት መደበኛ የንግድ በረራዎች እስከ አሁን ድረስ የተሸጡት 600 ያህል ትኬቶች እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ  ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የተነሳ በርካታ የጠፍር ጎብኚዎች በመጠባበቂያ ዝርዝ ውስጥ ስማቸው ተመዝግቦ ቀጠሮ እንዲይዙ ተደርጓል።

ይህንን በአሁኑ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የጠፍር ቱሪዚም በተመለከተ ስለጉዳዩ ዘርዘር ያለ መረጃዎችን ለማቅረብ በማሰብ የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ የሆነችው ሊንዳ ቦርዶኒ ይህንን ጠፈርን ለመጎብኜት የሚደርገውን ውድድር ወደ አዲስ ድንበሮች መጓዝ ስለሚያስከትለው አንድምታ እና ስለ ቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል በተመለከተ ያለውን አሁናዊ ሁኔታ ለማሳወቅ በማሰብ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወንድም ጋይ ኮንሶልማኞ ጋር ቆይታ አድርጋ እንደ ነበረ ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ “Laudato si” ‘ላውዳቶ ሲ’ (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) በሚል አርዕስት ይፋ ባደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት የጋራ የመኖሪያ ቤታችን መንከባከብን እንደሚያስተምሩን ሁሉ ለጠፍር እንክብካቤ ማድረግን እንደ ሚያካትት ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል።

ጠፈር የአዲስ ግኝቶች አንዱ መስክ ነው

የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ ከልጅነታቸው ጀምሮ በነበራቸው ባካበቱት ልምድ እና ለጠፈር ካላቸው ፍቅር የተነሳ በመስኩ ከፍተኛ የሆነ ጥናት ማድረጋቸውን ገልጸው ይህንን ቱባ የሆነ እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን ለቫቲካን ሬዲዮ አካፍለዋል።

በሳይንስ መስኩ እየተገኘ በመጣው እድገት ምክንያት ሰዎች በእውነቱ ወደ ጠፈር በመሄድ ናሙናዎችን ይዘው መመለሳቸውን ያብራሩት ዳይሬክተሩ አንዳንዶቹ ናሙናዎች በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስትል ጋንዶልፎ ውስጥ ባለው በቫቲካን የጠፈር ምርምር ላቦራቶሪ ሊመረመሩ እንደ ሚችሉ አክለው ገልጸዋል። ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ከአንድ ሺህ በላይ ከሰማይ የወረዱ ስባሪ አለቶች ስብስብ መመርመራቸው አስደሳች እንደሆነና ከሌሎች የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ጋር በመተባበር እነዚህ ዐለቶች በሕዋ ውስጥ ከሚገኘው ጋር ተመሳሳይ በሆነ በጣም ዝቅተኛ የሙቀት መጠን እንዴት እንደሚለወጡ መለካት መቻሉን የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ ገልጸው እነዚህ ናሙናዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ አድገዋል ፣ ተለውጠዋል እና ተሻሽለዋል በማለት ተናግረዋል።

“ሰማያዊው ሰማይ ከላይ ከሌላው ከተቀረው ዓለም የሚሰውረን ወይም የሚጋርደን ሊሰበር የማይችል እንቅፋት አለመሆኑን ያስታውሱናል” ብለዋል።

ለጠፈር እንክብካቤ ማድረግ ያስፈልጋል።

የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ በመቀጠል እያደገ ስላለው የጠፈር ጉዞ መስክ ተናግሯል ፣ ብዙ ገጽታዎች ገና ቁጥጥር ያልተደረገባቸው መሆኑን ጠቅሷል። ሳተላይቶች እርስ በእርስ እንዳይጋጩ እና በሁሉም መስክ ጥፋት እንዳይፈጥሩ “የሁሉንም ሐሳብ የገዛ እና ሁሉም የሚስማማበት” የጉህ ወይም የጠፈር መስመር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በላቲን ቋንቋ “ላውዳቶ ሲ” (ውዳሴ ላንተ ይሁን) ከሚለው ጳጳሳዊ መልእክት እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አንጻር የጋራ ቤታችንን ለመንከባከብ ያቀረቡት ጥሪ አጅግ በጣም አስፈላጊ እንደ ሆነ የገለጹት ዳይሬክተሩ ብዙውን ጊዜ ዓለምን ለማመልከት የሚያገለግል የግሪክ ቃል “ኮስሞስ” መሆኑን አስታውሰዋል። በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ - ጨረቃም ይሁን ፣ ከምድር አቅራቢያ ያለው በማርስ እና በጁፒተር መሃል የሚገኙ ፀሐይን የሚዞሩ ትናንሽ ፕላኔቶች በእንግሊዜኛው “አስትሮይድ” ወይም ከባቢ አየር ምህዋር በላይ የሚሽከረከሩ ዛቢያዎች፣ ወይም በየቀኑ የምንራመድበት ቦታ ሁሉ እንከባከበው ዘንድ  በአደራ የተሰጡን የእግዚአብሔር የእጁ ፍጥረታት መሆናቸውን አስረድተዋል።

በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከምንም ነገር ይልቅ አንድ ነገር መኖሩ ምክንያታዊ በሆነ በሚያምር ሁኔታ በፈጠረው አምላክ - አርማዎች - ብቻ ሊብራራ የሚችል ምስጢር መኖሩን የሚያመለክት መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

ወደ ጠፈር የሚደረጉትን ጉዞዎች በገንዘብ መደገፍ

ወደ ጠፈር የሚደረጉትን ጉዞዎች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ በማሰብ በዘርፉ ፈሰስ የተደረገው ገንዘብ፣ ግዙፍ ሀብቶች እና እየቀረቡ የሚገኙትን ድጋፎችን ለመመገብ ወይም ለተሻለ ጥቅም ለማዋል እንዴት እንደ ሚቻል  ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ ከግዙፉ የገንዘብ ድጎማ ሊጠቀሙ የሚችሉ ሌሎች ተነሳሽነትዎች እንዳሉ አምኖ የተቀበሉ ሲሆን “እኛ መብላት ከሚፈልጉ እንስሳት በላይ ነን እንዲሁም ነፍሳችንን መመገብ አለብን” ብለዋል።

“እኛ በእንጀራ ብቻ አንኖርም” በማለት አክለው የገለጹት ዳይሬክተሩ ስለሆነም የሰው ልጅ “እኔ ማን እንደሆንኩ እና ከየት እንደመጣሁ ያንን ጉጉት ለመዳሰስ እና ለማርካት እድሉ መከልከል ትክክል አይደለም ፣ እናም ከዚህ ፍጥረት ጋር የምቆራኘው እንዴት ነው?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ እንደ ሆነ አክለው ገለጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የበለጠ ሲያብራሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የፍጥረት ታሪክን ያስታውሳሉ ፣ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቀናት ሁሉ እኛ የምንኖርባት ፕላኔት መኖሯን ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰዋል። ሆኖም ፣ “የፍጥረት የመጨረሻው ግብ እግዚአብሔርን እና እግዚአብሔርን ፍጥረትን በማሰላሰል የምናሳልፈው ቀን ሰንበት ነው በማለት የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ ተናግረዋል።

ድሃው ማሕበረሰብ በሳይንስም ይሁን በኪነ-ጥበብ በኩል ፍጥረትን ለማሰላሰል የሚችልበት እድል እንዲኖር ይህንን ለማድረግ ተጠርተናል ፣ ድሆችን እንድንመግብ ተጠርተናል በማለት አክለው ገልጸዋል።

አንዳንድ የጥበብ ቃላትን በማካፈል አሉ የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል የሆኑት እና የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወንድም ጉይ ኮንሶሎማኞ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ ሁሉም ሰው በሌሊት ወደ ውጭ እንዲወጣ እና ስለ ከዋክብት እና ስለ ጨረቃ በማሰላሰል ጥቂት ጊዜዎችን እንዲያሳልፍ እና “የዕለት ተዕለት ጭንቀታችን ከሚያስፈልገው በላይ ዓለም እንደ ምትበልጥ ለመረዳት እንችላለን” የሚለውን ሰዎች ሁሉ እንዲያስታውሱ ጋብዘዋል።

30 July 2021, 15:05