ፈልግ

በቫቲካን ውስጥ የሚገኝ የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቫቲካን ውስጥ የሚገኝ የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባር ቁጥጥር፣ ውጤታማ ሥራን ለመሥራት የሚያግዝ መሆኑ ተገለጸ

ቫቲካን ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያደረገችው ጥረት ፍሬያማ ውጤት ማስገኘቱን ገምግሞ ፍርድ እንዲሰጥ የተሰየመው የባለሞያዎች ኮሚቴ ሪፖርት አረጋግጧል። ሕገ ወጥ ተግባራት ካሉ እንዲገመግም በቫቲካን የተጠየቀው ኮሚቴ ባቀውርበው የፍርድ ውሳኔ መሠረት፣ 5ቱ ከፍተኛ ውጤቶችን ማስገኘታቸውን እና 6ቱ አመርቂ የሚባሉ መልካም ውጤቶችን ማስገኘታቸውን የባለሞያዎች ኮሚቴ አረጋግጦ፣ ደካማ የተባሉ ጥረቶች አለመመዝገባቸውን ገልጿል። በዚህ መንገድ የሚካሄድ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባር ቁጥጥር ውጤታማ ሥራን እና አገልግሎትን ለማበርከት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት ያሉ እንደሆነ ገምግሞ ፍርድ እንዲሰጥ የተሰየመው የባለሞያዎች ኮሚቴ በቅድስት መንበር እና በቫቲካን ከተማ ግዛት ውስጥ ተግባሩን ሲያከናውን ይህ የመጀመሪያው መሆኑ ታውቋል። ኮሚቴው ፍተሻውን ካጠናቀቀ በኋላ በሰጠው የፍርድ ሂደት፣ ቅድስት መንበር እና የቫቲካን ከተማ ግዛት የገንዘብ ዝውውርን እና ሽብርተኝነትን ለመከላከል ያደረጉት ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን በሰጠው ፍርድ አረጋግጧል። የፍርድ ሂደቱን በቅርብ የተከታተሉት፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት ገምጋሚ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ በአስተያየታቸው፣ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት ገምጋሚ ኮሚቴ በቅድስት መንበር እና በቫቲካን ከተማ ግዛት ውስጥ ዓለም አቀፍ መርሆችን ተከትሎ ባካሄደው የቁጥጥር ተግባሩ 200 ገጾች ያሉትን የውሳኔ ሰነድ ይፋ ማድረጉን አስታውቀዋል። “Moneyval” በመባል የሚታወቅ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራት መርማሪ ኮሚቴ ከአውሮፓ አገሮች የተወጣጡ ከ30 በላይ አባላት ያሉበት መሆኑን ገልጸው፣ የአውሮፓ ምክር ቤት፣ የቅድስት መንበር እና የቫቲካን ከተማ ግዛት እ. አ. አ ከ2011 ዓ. ም ጀምሮ አባል የሆኑበት ድርጅት መሆኑን አስረድተዋል።

“Moneyval” በመባል የሚታወቅ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራት መርማሪ ኮሚቴ፣ በአውሮፓ አገራት የሚካሄዱ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራት ለመቆጣጠር ሁለት መንገዶችን እንደሚከተል የገለጹት የመርማሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ፣ መርማሪ ኮሚቴው የምርመራ ተግባሩን በሚያካሂድበት ዘዴው ቴክኒካዊ ተገዢነትን እና ውጤታማነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል። እነዚህን ዘዴዎችን ተከትሎ ባካሄደው የቁጥጥር ተግባሩ 200 ገጾች ያሉት የውሳኔ ፍርድ ሰነድ ያዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል።           

ቴክኒካዊ ተገዢነት ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራትን ለመከላከል፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን በመጠበቅ የሚካሄድ የቁጥጥር መንገድ መሆኑን የመርማሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ ገልጸው፣ የመሪማሪ ኮሚቴ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ዓለም አቀፍ ደንቦችን ያሟላ መሆኑን በሚያረጋግጡ እና አስራ አንድ ፈጣን ውጤቶችን በሚያመጡ ነጥቦች ላይ በመመርኮዝ የቴክኒክ ተገዢነት ውጤታማነትን በተደጋጋሚ የሚመለከት መሆኑን አስረድተዋል።

ቅድስት መንበር እና የቫቲካን ከተማ ግዛት ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራትን የሚፈትሽ ባለሞያዎችን ሲያሰማሩ ይህ የመጀመሪያ መሆኑ የገለጹት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ፣ የባለሞያዎች ቡድን ይፋ ያወጣው የግምገማ እና የፍርድ ሰነድ የተዘጋጀው በሁለት ሳምንታት ውስጥ መሆኑን እና እ. አ. አ ከ2019 ዓ. ም ጀምሮ ከመርማሪ ባለሞያ ቡድን ጋር  በመተባበር ጥልቅ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።

“Moneyval” በመባል የሚታወቅ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራት መርማሪ ኮሚቴ በቅድስት መንበር እና በቫቲካን ከተማ ግዛት በማካሄድ ይፋ ያደረገው የፍርድ ውሳኔዎች በሙሉ ከፍተኛ እና አመርቂ የሚባሉ መልካም ውጤቶችን ማስገኘታቸውን ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ አስረድተዋል። መርማሪ ኮሚቴው አባላት ወደ 200 ከሚሆኑ አገራት እና ግዛቶች ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን አቶ ካርሜሎ ገልጸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየውን ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት ለመከላከል በሚደረግ ጥረት ከፍተኛ ሃላፊነት እና ሚና ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት መርማሪ እና ገምጋሚ ኮሚቴ መዋቀሩ የሥራ ሂደትን ተመልክቶ ትክክለኛ ፍርድ እና ውሳኔን ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ ገልጸው፣ በቅድስት መንበር እና በቫቲካን ከተማ አስተዳደር በስፋት የተካሄደው ግምገማ እና የፍርድ አሰጣጥ ትክክለኛውን መንገድን የተከተለ እና በሥራ የበለጠ ፍሬያማ ለመሆን የሚያግዝ መሆኑን የመርማሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት መርማሪ ኮሚቴ እንደ ምክር ባቀረበው ሃሳቡ፣ በቫቲካን የውስጥ ሰራተኞች ሊከሰቱ ከሚችሉ የገንዘብ ጥሰቶች የሚመጡ አደጋዎች ትንተና ማሻሻል እንደሚገባ አስታውቋል። መሪማሪ ኮሚቴው እ. አ. አ ከ2014 ዓ. ም ጀምሮ ቅድስት መንበር እና የቫቲካን ከተማ አስተዳደር ላደረጉት ጥንቃቄ እና ትኩረቶች እውቅናን ሰጥቶ፣ ከጥንቃቄዎቹ መካከል ጸረ ሙስና ባለ ስልጣንን መሰየሙን እና በቅርቡም የሥራ ኮንትራት ውሎችን የሚመለከት ሰነድ መዘጋጀቱን አስታውሷል።

ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራት መርማሪ ኮሚቴ ፕሬዚደትን የሆኑት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት የሰጡትን አስተያየት ሲያጠቃልሉ እንደገለጹት፣ መርማሪ ኮሚቴው ለቅድስት መንበር እና ለቫቲካን ከተማ አስተዳደር ያቀረቧቸው የምክር ሃሳቦች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን እና ከፍተኛ ቁጥጥርን ለማድረግ የሚያግዙ መሆናቸውን አስታውሰው፣ ቅድስት መንበር እና የቫቲካን ከተማ አስተዳደር በሚያከናውኗቸው ሥራዎች ከፍተኛ ግልጽነት እንዲኖር እና የቤተክርስቲያኗን ተልዕኮ በፍሬያማነት ለመፈጸም የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

10 June 2021, 16:13