ፈልግ

በሕንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ከቀረቡ የምግብ ዕርዳታ አቅርቦቶች መካከል በሕንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ከቀረቡ የምግብ ዕርዳታ አቅርቦቶች መካከል  

በምግብ አቅርቦት ሥርዓት እና ግጭቶች ላይ የጋራ ውይይት መካሄዱ ተገለጸ

ሰኞ ግንቦት 23/2013 ዓ. ም ከሰዓት በኋላ በተካሄደው ሦስተኛ ዙር የአውታረ መረብ ሴሚናር ላይ፣ የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና በቫቲካን የምግብ ዋስትናን የሚከታተሉ ሌሎች ዘርፎች በጋራ፣ ቤተክርስቲያን ረሃብን ለመቀነስ በምታደርገው ጥረት ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ምግብ ለሕይወት” በሚል ርዕሥ በምግብ አቅርቦት ሥርዓት ላይ ሰኞ ግንቦት 23/2013 ዓ. ም ከቀኑ ዘጠኝ ላይ የተካሄደው የአውታረ መረብ ላይ ሴሚናር ትኩረቱን ያደረገው በዓለማችን ውስጥ በሚታየው የምግብ አቅርቦት አለመመጣጠን ችግር ላይ ሲሆን ይህን ችግር ለመቅረፍ በሚያስችሉ መንገዶችም ላይ መወያየቱ ታውቋል። ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ በተካሄደው የመጨረሻ ዙር የአውታረ መረብ ሴሚናር፣ በጳጳሳዊ አካዳሚ የማኅበራዊ ሳይንስ ክፍል በእንግድነት መካፈሉ ታውቋል።

“ምግብ ለሕይወት” በሚል ርዕሥ ሰኞ ግንቦት 9/2013 ዓ. ም የተጀመረው የአውታረ መረብ ላይ ሴሚናር ለዓለማችን ሕዝብ በቂ ዕለታዊ ምግብን ለማቅረብ በሚደረግ ጥረት እና በሌሎች ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ መምከሩ ታውቋል። ውይይቱ በተጨማሪም ሁለገብ ማኅበራዊ ዕድገትን ለማምጣት ሴቶች የሚጨወቱትን ሚና የተመለከተ ሲሆን፣ ከግንቦት 18/2013 ዓ. ም ጀምሮ “ፍትሃዊ የምግብ አቅርቦት” በሚል ርዕሥ ለሰዎች የሥራ ዕድልን ማመቻቸት፣ ፍትሃዊ የምግብ አቅርቦት ማሳደግ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉ ታውቋል።

የአውታረ መርቡ ሴሚናር ዋና ዓላማ፣ በመጪው ሐምሌ ወር 2013 ዓ. ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ አቅርቦት ሥርዓትን በማስመልከት ለሚያካሂደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ እና በዓለም የምግብ ፕሮግራም የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ክፍል፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና በቫቲካን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ምክር ቤት በጋራ የሚያቀርቡትን መሪ ሃሳብ ለማሰባሰብ መሆኑ ታውቋል። የጋራ ሃሳባቸው የሚመነጨውም “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ከሚለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን መሆኑ ታውቋል።

በጋራ ውይይቱ ወቅት መላዋ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች ተዋናይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የጋራ መኖሪያ ምድራችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ በቂ እና ፍትሃዊ የምግብ አቅርቦት ሥርዕዓትን በዓለማች ለመዘርጋት እና ረሃብን ከምድራችን ገጽ ለማጥፋት ጥረት የሚያደርጉ መሆኑ ታውቋል። ለሦስት ዙር የተካሄዱት የዓውታረ መረብ ላይ ውይይቶች ውጤት በሚቀጥለው ሐምሌ ወር ላይ በሚካሄድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሚቀርብ መሆኑን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል አስታውቋል። ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ አክሎም፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረጉ የግል እና የጋራ ጥረቶች፣ ጠቅላላውን የወደ ፊት ዘላቂ እና አስተማማኝ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የሚደረገውን ሂደት ለማገዝ መሆኑ ታውቋል።

31 May 2021, 15:26