ፈልግ

የግሬጎሪያን መንፈሳዊ ዜማ ድርሰት የግሬጎሪያን መንፈሳዊ ዜማ ድርሰት  

በ“ውዳሴ ላንተ ይሁን” ፌስቲቫል ተፈጥሮን የሚያደንቅ መዝሙር መቅረቡ ተገለጸ

ከሰኞ ግንቦት 9/2013 ዓ. ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 15/2013 ዓ. ም ድረስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ሳምንት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ያሳለፍነው ሳምንት “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ላይ መሠረት በማድረግ ጥፋት እየደረሰበት ለሚገኘው የጋራ መኖሪያ ምድራችን እና በድህነት የሚሰቃየውን የዓለማች ሕዝብ በማሰብ ጥበቃን እና እንክብካቤን ለማድረግ የሚያስችሉ ጠቃሚ ሃሳቦች የፈለቁበት ሳምንት መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በዚህ የአንድ ሳምንት ፌስቲቫል ላይ ከፍተኛ ውድመት እየደረሰበት የሚገኘውን ዓለማችን እንድናስብ የሚጋብዙ በርካታ ዝግጅቶች መቅረባቸው ታውቋል። ከዝግጅቶቹ መካከል ለተፈጥሮ የሚሰጥ አድናቆት የተገለጸበት መዝሙር መዘጋጀቱ ታውቋል። “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ሳምንት በተዘጋጀው ፌስቲቫል ላይ የፎቶ ግራፍ ውድድርም የተካተተበት ሲሆን በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ. አ. አ በ2020 ዓ. ም ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን ላይ ቫቲካን ያቀረበው መልዕክት የታሰበበት መሆኑ ታውቋል።

ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን

በየዓመቱ ግንቦት 14 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን እ. አ. አ በግንቦት 22/1992 ዓ. ም በተመሠረተው እና ሕጋዊነትን ባገኘው የብዝሃ ሕይወት ቀን መልዕክቶች ላይ በማስተንተን በምድራችን ውስጥ ለሚገኝ ተፈጥሮ ተገቢውን እንክብካቤ እና ጥበቃን ማድረግ ዘላቂነቱን ማረጋገጥ እንደሚያፈልግ የሚያሳስብ መሆኑ ታውቋል። በተጨማሪም ከተፈጥሮ የሚገኘውን ሃብት በፍትሃዊ መንገድ ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግን የሚያጠቃልል መሆኑ ታውቋል። ጠቅላላ ዓላማውም የምድራችን የተፈጥሮ ሃብት ዘላቂነት እንዲኖረው የሚያግዙ ትምህርቶችን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑ ታውቋል። ይህን ዕላማ መሠረት በማድረግ የዘንድሮ ዓለም አቀፍ በዓል መሪ ቃልም “በተፈጥሮ ላይ ለሚደርስ አደጋ መልስ የሰው ልጅ ነው” የሚል መሆኑ ታውቋል። በመሆኑም በሰዎች ዘንድ ግንዛቤን በማሳደግ፣ በተፈጥሮ ላይ የሚደርስ ጥፋት በሰውች ላይ የሚያደርሰውን አደጋ በሚገባ በመገንዘብ ለአካባቢ ጥበቃ አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ ዘንድሮ የተከበረው ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን መልዕክት አሳስቧል።

በብዝሃ ሕይወት ላይ የሚደርስ መጥፋት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ላይ በዓለማችን ውስጥ በተፈጥሮ ላይ የሚደርስ ጥፋት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው፣ በየዓመቱ በቁጥር ከሺዎች በላይ የእጽዋዕት እና የእንሳሳት ዝሪያዎች ከምድር ገጽ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እየጠፉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም ከፍጥረታቱ መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸው ዕጽዋዕትና እንሳሳት በሰዎች ግድ የለሽነት የሚጠፉ መሆኑን “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው በኩል ገልጸዋል።  

25 May 2021, 19:37