ፈልግ

ለአየር ንብረት ለውጥ እና ለስደተኞች አስቸኳይ የጋራ ምላሽ እንዲሰጥ ቅድስት መንበር ጥሪ አቀረች! ለአየር ንብረት ለውጥ እና ለስደተኞች አስቸኳይ የጋራ ምላሽ እንዲሰጥ ቅድስት መንበር ጥሪ አቀረች! 

ለአየር ንብረት ለውጥ እና ለስደተኞች አስቸኳይ የጋራ ምላሽ እንዲሰጥ ቅድስት መንበር ጥሪ አቀረች!

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ስደተኞችን በተመለከተ ለውይይት በተዘጋጀው የፓነል ውይይት ላይ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱት በአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖ እንደ ሆነ ጥናቶች እንደ ሚያሳዩ ገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በሜድትራንያን ባህር ውስጥ የተፈጥረው ሌላ አሳዛኝ ክስተት ዜና አውሮፓን ያስደነገጠ እንደሆነ የገለጹት በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት እና የሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪች ሲሆኑ ንግግራቸው ያተኮረው የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያስከተለ ስለሚገኘው ጥፋት እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሆች ላይ ባለው የስነምህዳር ቀውስ ላይ እንደ ነበረም ተገልጿል።

በዚህ ዓመት ቢያንስ 743 ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ውስጥ በጀልባቸው ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ መሞታቸው ታውቋል። እነሱ ወንዶች፣ ሴቶች እንዲሁም ሕጻናት የሚገኙባቸው ሲሆን በየአገሮቻቸው በደረሰ አመፅ ወይም በድህነት ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ እንደ ነበሩ የተገለጸ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ይህ ችግር የሚባባሰው ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ጫና እንደ ሆነ ጭምሮ ተገልጿል።

በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪች በሰጡት አስተያየት “ማክሰኞ ዕለት የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ስደተኞችን በተመለከተ በተደረገው ዓለም አቀፍ ውይይት ላይ ሊቀ ጳጳስ ጁርኮቪች ለተባበሩት መንግሥታት ጠንካራ አቤቱታ አቅርበዋል።

"ማየት ወይም አለማየት"

“ማየት ወይም አለማየት” በጋራ ወደ ተግባር እንድናመራ ሊያደርገን የሚገባን ጥያቄ ነው ያሉት በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪች “ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከሰተው ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተለየ ሁኔታ የአየር ንብረት ቀውስ ለዓመታት እየተጋረጠብን የመጣ አስደንጋጭ ክስተት እየሆነ መምጣቱ እንደ ሚያሳስባቸው አክለው የገለጹ ሲሆን ሆኖም ችግሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከፍተኛ ትኩረት ሳይሰጠው መቀረቱን አክለው ተናግረዋል።

በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪች “የአየር ንብረት ቀውስ ያስከተለው አስከፊ መዘዞች ቀደም ሲል በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ እውን እየሆኑ ናቸው” ሲሉ ጠቁመዋል። “የአየር ንብረት ለውጥ በሁሉም ቦታ ቢከሰትም ፣ ምላሽ የመስጠት እና ካስከተለው ተግዳሮት ጋር የመላመድ አቅም በጣም ይለያያል” ያሉ ሲሆን በሥነ-ምህዳራዊ እና በአየር ንብረት ቀውሶች እጅግ በጣም የተጎዱት ድሆች እና በጣም ተጋላጭ የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች ናቸው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ቀውስ “የሰው ፊት ገጽታ” እንዳለው አምኖ መቀበል በጣም አስፈላጊ ነው ያሉት በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የገለጹ ሲሆን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ ብክለት በስደተኞች እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመፍታት እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ ለማድነቅ እወዳለሁ ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ሊቀረፍ የሚችል ክስተት ነው።

“ሰዎች የመኖሪያ አካባቢያቸው ለመኖር አዳጋች በመሆኑ ለመሰደድ ሲገደዱ ተፈጥሮአዊ ሂደት ሊመስል ይችላል ፣ የማይቀር ነገር ሊመስለን ይችል ይሆናል” እውነቱን ግን ስንመለከት እያሽቆለቆለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ራሱ ነው “ብዙውን ጊዜ በመጥፎ ምርጫችን የተነሳ እና አጥፊ የሆኑ እንቅስቃሴ ውጤት የሆነው ተግባራችን የሰው ልጅ የጋራ የመኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን በመጉዳት የሰው ልጆች ከፍጥረት ጋር የሚጋጭ የራስ ወዳድነት እና የቸልተኝነት መንፈስ በብዛት ይታይብናል” ብለዋል።

በመጨረሻም የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የወጣው ስምምነት ለመዘከር በማሰብ በሚካሄደው 26 ኛ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች ሳይዘገዩ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቅረፍ ሁሉም አካላት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ እንዳስታወቁት “ለተፈጥሮ መክፈል የሚገባን ዕዳ አለብን ፣ እንዲሁም በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት በሥነ-ምህዳር ላይ የደረሰው አደጋ እና የብዝሃ-ህይወት መጥፋት ለተጎዱ ህዝቦች ሁሉ መክፈል የሚገባን ዕዳ አለ። እነዚህ ጉዳዮች በቀላሉ ፖለቲካዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ አይደሉም፣ እነሱ የፍትህ ጥያቄዎች ናቸው ፣ ከእንግዲህ ችላ ሊባል ወይም ሊዘገይ የማይችል የፍትህ ጥያቄ ነው። በእርግጥ ለእነሱ የምንሰጠው ምላሽ ለልጆቻችን የምንተወውን ዓለም እንዲቀርፅ ስለሚያደርግ የወደፊቱ ትውልድ ሥነ ምህዳራዊ ግዴታን ይወጣል ብዬ አስባለሁ” ማለታቸው ተዘግቧል።

በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢቫን ጁርኮቪች ስደት እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች “በተፈጥሯቸው እና መጠናቸው” በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የጋራ እና የተቀናጀ ምላሽ ይፈልጋሉ ካሉ ብኋላ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

27 May 2021, 15:37