ፈልግ

የሊቢያ ጦርነት የሊቢያ ጦርነት 

በዓለማችን የጦር መሣሪያ ትጥቅን ለማስፈታት ልማትን፣ ሕግን እና አንድነትን ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት መጋቢት 14/2013 ዓ. ም. በአውታረ መረብ አማካይነት የተዘጋጀውን ስብሰባ የተሳተፉት ምሁራን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና አምስት ካርዲናሎች ባቀረቡት አስተያየት በዓለማችን የጦር መሣሪያ ትጥቅን ለማስፈታት ልማትን፣ የሕግ ተግባራዊነትን እና አንድነትን ማሳደግ እንደሚያፈልግ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአውታረ መረብ ስብሰባን ከተካፈሉት መካከል አንዱ የሆኑት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የተቀናጀ ደህንነት፣ አብሮነትን፣ ፍትህን፣ ሁሉ አቀፍ ሰብዓዊ ልማትን፣ መሠረታዊ የሆኑ ሰብአዊ መብቶች ማክበርን እና ለፍጥረት የሚሰጥ እንክብካቤን ያካተተ መሆን እንዳለበት፣ በዓለማችን የጦር መሣሪያ ትጥቅን ለማስፈታት የሚደረግ እንቅስቃሴን ለማጠናከር በተደረገ የአወታረ መረብ ስብሰባ ላይ ባቀረቡት አስተያየታቸው ገልጸዋል። ማክሰኞ መጋቢት 14/2013 ዓ. ም. በአውታረ መረብ አማካይነት የተካሄደውን ስብሰባ በጋራ ያዘጋጁት በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና በቫቲካን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ ምክር ቤት ለንደን ከሚገኝ የጦር መሣሪያ ትጥቅን እና ዕድገትን የሚያስወግድ ስልታዊ ፅንሰ-ሀሳብ ማስፋፊያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው።

ገንዘብን ለኢኮኖሚ ማገገሚያ ማዋል ያስፈልጋል

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ሐላፊ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ኮዱዎ ታርክሰን፣ በሰብአዊነት ላይ የተደቀኑ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችሉ በከንቱ የሚባክኑ ሀብቶችን ረሃብን እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲያውሉት በማለት ለአገራት መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ታርክሰን እንዳሉት ዓለማችንን ያጋጠመው የጤና እና የኢኮኖሚ ቀውስ፣ የመንግሥታትን የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ለኢኮኖሚ ማገገሚያ የሚውል ገንዘብ ለማግኘት  አጋጣሚውን ተጠቅሞ የጦር መሣሪያ ትጥቅን ወደ ማስፈታት ሂደት ለመሄድ ያግዛል ብለዋል።

ዓለም አቀፋዊ ደህንነት እና አንድነት

ለንደን በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ጥናትና ዲፕሎማሲ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ዳን ፓሌሽ በንግግራቸው በዓለማችን ለወታደራዊ አገልግሎት ከሚውለው 2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ግማሹን ለዓለም አቀፍ የጤና ክብካቤ እና የካርቦን ልቀት ቅነሳ ቢውል በቂ ይሆን ነበር ካሉ በኋላ አክለውም ይህ የገንዘብ መጠን ለጦርነት የሚያደርሱ ምክንያቶችንም ሊያስወግድ ይችል ነበር ብለዋል።

ልማት ጥፋትን ያሸንፋል

ጄኔቫ በሚገኝ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኢቫን ጀርኮቪች በአውታረ መረብ አማካይነት ስብሰባውን ላዘጋጀው፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የኒውክሌር ትጥቅ የማስፈታት እውነተኛ ግብ የሰውን ልጅ ልማት የሚያሳድግ መሆኑን አስረድተዋል። ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኢቫን ጀርኮቪች አክለውም፣ ቅድስት መንበር “ራስን በራስ ለማጥፋት” የሚያስችሉ አዲሶቹ የጦር መሣሪያዎች ምርቶችን አስመልክታ ያቀረበችውን የተቃዉሞ ጥሪዋን አስታውሰው፣ የሰው ልጆች ጦርነት እንዳይካሄድ በማለት በማለት የሚያቀርቡትን ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት የሚያስወግድ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶችን ቫቲካን የምትቃወም መሆኗንም ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኢቫን ጀርኮቪች ገልጸዋል።

ብዙ የጦር መሣሪያ ምርቶች እና አነስተኛ የጤና እንክብካቤ

የጦር መሣሪያ ምርትን ለመግታት የሚያስችል ተጨባጭ ሀሳብን በማስቀደም የጦር መሣሪያ ትጥቅን ሙሉ ለሙሉ ማስፈታት እንዲቻል አገራት ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነቶችን እንደ መነሻ ለድርድር ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ በውይይቱ ላይ መቅረቡ ታውቋል።

የአውታረ መረብ ላይ ስብሰባን የተሳተፉት፣ ለንደን ከተማ የሚገኝ የጦር መሣሪያ ምርት እና ዕድገት የሚያስወግድ ስልታዊ ፅንሰ-ሀሳብ ማስፋፊያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ኦላሚድ ሳሙኤል ለተሰብሳቢዎች እንደተናገሩት፣ በዓለማችን ውስጥ የሚታዩ አስፈሪ እና ተቃራኒ የሆኑ ግንኙነቶች መኖራቸውን ለመግለጥ ቡድናቸው እስታቲስቲክ ሞዴሎችን መጠቀሙን ነግረው፣ መንግሥታት ከኒውክሌር መሣሪያ ግብር ከፋዮች የበለጠ ገንዘብ እንደሚያገኙ ነገር ግን ለጤና እና ለማህበራዊ ፕሮግራሞች አነስተኛ ገንዘብ የሚያወጡ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ክርስቲያኖችን በጋራ ግብ ውስጥ አንድ ማድረግ

በሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረግ የጋራ ውይይት የጦር መሣሪያ ምርት እና ትጥቅ ተወግዶ ሰላም እንዲመጣ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በስብሰባው ወቅት የተገለጸ መሆኑ ታውቋል። ይህን በማስመልከት በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ሕብረት ማጠናከሪያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ ለስብሰባው ተካፋዮች እንደገለጹት፣ የጦር መሣሪያ ትጥቅን ለማስፈታት የሚደረግ የሐይማኖት ተቋማት ጥረት የክርስቲያኖችን አንድ በማሳካት ወደ ጋራ ግብ እንዲደርሱ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸው፣ ለክርስቲያናዊ አንድነት የሚያደርጉት ጥረት ለቤተክርስቲያን መፈወስ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ፈውስንም የሚያበረታታ ነው ብለዋል። አክለውም ክርስትያኖች ሰላምን ለማስፈን በጋራ በሚሠሩበት ጊዜ፣ በክርስቲያኖች አንድነትም እንዲሁ መሻሻል የሚመጣ መሆኑን በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ሕብረት ማጠናከሪያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ አስረድተዋል።

የመከራን ጩኸት ማድመጥ ያስፈልጋል

በጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት አስተባባሪ ፕሬዚደንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ሚገል አንገል ኣዩሶ በበኩላቸው፣ የጦር መሣሪያ ትጥቅን ለማስፈታት የሚደረግ ጥረት በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ምክንያቱም “ሃይማኖት የሰውን ልጅ ልብ የሚነካ በመሆኑ ነው” ብለዋል። ብጹዕ ካርዲናል ሚገል አንገል ኣዩሶ፣ የጦር መሣሪያ ትጥቅን የሚያስፈቱ ስልቶችን በማቅረብ ጠቃሚ የሆኑ ሥራችን ስናሂድ በጦርነት የተጎዱት ሕፃናት ፣ የሴቶችና የወንዶች ጩኸት ማስታወስ እንችላለን ብለዋል።

በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲወርድ

ብጹዕ ካርዲናል ሲልቫኖ ማርያ ቶማሲ፣ የማልታ ሉዓላዊ ወታደራዊ ዘብ ልዩ ልዑክ በበኩላቸው ማኅበራቸው ሰላምን ለማስፈን እየፈጸመ ያለውን ሥራ ሲገልጹ፣ ያለ አድልዎ አገልግሎቱን ለሁሉም በማቅረብ የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ ሕዝቦች በሰላም እንዲኖሩ ዕርዳታን በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን አስረድተዋል። ስለሆነም እንደ ጦርነት እና ግጭቶች ላሉት አለም አቀፍ ችግሮች መፍትሄዎችን በህዝቦች እና በማህበረሰቦች መካከል በሚደረጉ ተጨባጭ ውይይቶች አማካይነት መፈለግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

25 March 2021, 15:58