ካርዲናል ፓሮሊን፣ በጣሊያን ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩ ወጣቶች ሰላምን የሚገነቡ መሆናቸውን ገለጹ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ወጣቶቹ የመጡባቸውን የአመጽ እና የጦርነት ቀጠናን ያስታወሱት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ አሁን በሚኖሩበት ስላማዊ ሥፍራ የሰላምን አስፈላጊነት በመገንዘብ ለሰላም መቆማቸው የሚያስደስት መሆኑን አስረድተዋል። ካርዲናል ፓሮሊን አክለውም ከወጣቶቹ ጋር መገናኘታቸውን እና ከወጣቶች የተላከላቸውን ሰላምታ እና የወጣቶቹ የሰላም ጥረት ወደ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ዘንድ የሚያደርሱ መሆኑን ገልጽዋል። ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ትናንት የካቲት 9/2013 ዓ. ም. የጎበኙት “ዎርልድ ሃውስ” የተባለ ሥፍራ እ.አ.አ በ1988 ዓ. ም. የተመሰረተ እና በዓለም ዙሪያ በጦር መሣሪያ በመታገዝ የሚደረጉ አመጾችን እና ጦርነቶችን ለማስወገ ጥረት ሲያደርጉ በቆዩት በክቡር አቶ ፍራንኮ ቫካሪ የተገነባ መሆኑ ታውቋል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ አመጽ እና ጦርነት ከሚካሄድባቸው ልዩ ልዩ አካባቢዎች የመጡ ወጣት ሴቶች እና ወጣት ወንዶች የተገኙ ሲሆን ከእነርሱም በመተጨማሪ በጣሊያን ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የሚመራ የክሜዲቴራኒያን የሰላም፣ የትምህርት እና የዕርቅ መርሃ ግብር አባል ወጣቶም መገኘታቸው ታውቋል።
ሰላም የሚገነባበት ሥፍራ
ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ትናንት ወደ ሥፍራው ባደረጉት አጭር ጉብኝታቸው በማዕከሉ የሚገኙ ወጣቶች የሚከታተሏቸው ትምህርቶች የሮንዲን የመሪነት ስልትን የተከተለ መሆኑን ለር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ እንደሚናገሩ ገልጸው፣ እነዚህ ወጣቶችም ቀስ በቀስ ለሰላም ያላቸውን እውቀት በማሳደግ በመጡበት አካባቢ ከምትገኝ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር፣ በባልካን ባሕረ ሰላጤ አገሮች፣ በቱርክ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች እና በሰሜን አፍሪካ አገሮች ውስጥ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ለውጦችን ለማምጣት እንደሚተባበሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
የጋራ ውይይት እና እርቅ ሊኖር ይገባል
ከወጣቶቹ አንዷ እና የቦስኒያ ተወላጅ የሆነች ወጣት አሚና ለተሰብሳቢዎቹ ባሰማችው ንግግር፣ እጅግ አስቸጋሪ ዓመትን አቋርጠን ለሥራ ወደ ጣሊያን አገር መድረሳቸው የሚያስደስት መሆኑን ገልጻ፣ በመራሃ ግብራቸው መሠረት አብረው እየኖሩ የጋራ ውይይቶችን ማድረግ የሚቻል መሆኑን አስረድታለች። ወደ አገራቸው በሚመለሱበት ጊዜ የሚያንቀሰቅሷቸው እቅዶች ዋና ዓላማ የጋራ ውይይቶችን በማድረግ አገራቸውን ወደ እርቅ ማድረስ እንደሚሆን ገልጻ፣ ወጣቶቹ ከያሉበት አገር ሆነው የእርስ በእርስ ግንኙነት መስመርን በማበጀት እዚህ የተማርነውን የሰላም እና የእርቅ ስልቶችን በአገራቸው ተግባራዊ ላማድረግ ማኞት ያላቸው መሆኑን አሚና ገልጻለች። ወጣቶቹ ከማዕከሉ የሚቀስሙት ትምህርት ሚላኖ ከተማ ከሚገኝ የቤተሰብ ጥናት ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑ ታውቋል።
ቫካሪ በካርዲናል ፓሮሊን ጉብኝት ተደስተዋል
በብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጉብኝት የተደሰቱት ቫካሪ በንግግራቸው እንደገለጹት ማዕከላቸው የሚያስተምራቸው ወጣቶች የሮንዲን የመሪነት ዘዴን የሚቀስሙ መሆኑን ገልጸው ይህም በመጡበት አካባቢ የተነሳዉን አመጽ እና ጦርነት ለማርገብ የሚያግዛቸው መሆኑን አስረድተዋል። አቶ ቫካሪ በንግግራቸው እንደገለጹት ከሁለት ዓመት በፊት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን “የሰላም መሪዎች” የተባለ የዘመቻ ዓላማቸው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቀረቡ መሆኑን አስታውሰው፣ ሰላምን የሚያመጡ አዲስ ወጣት መሪዎችን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰው፣ በጉብኝታቸው ወቅት ያሳዩት አድናቆት ወጣት ተማሪዎቹ የሰላም አምባሳደሮች እንዲሆኑ የሚያበረታታ መሆኑን ለብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ገልጸዋል።
የዕለቱ መርሃ ግብር
በጣሊያን የአሬዞ-ኮርቶና-ሳንሴፖልክሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪካርዶ ፎንታና እና ከመብራት ኃይል ፋውንዴሽን ፕሬዚደንት ከሆንት ዶሜኒኮ ጃኒ ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ከብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር ያደረጉት ግንኙነት፣ እ.አ.አ ጥቅምት 9/2020 ዓ. ም. በተካሄደው ዝግጅት ላይ ግድ የለሽነትን ለማወገድ የተደረገውን ጉባኤን የሚያስታውስ መሆኑ ተገልጿል። ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በጉብኝታቸው ወቅት በሚቀጥለው መስከረም ወር ላይ የአራተኛ ዓመት ትምህርታቸውን የሚጀምሩ፣ ከጣሊያን ውስጥ የተወጣጡ 27 ተማሪዎች ገብተው የሚማሩበት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤትን የጎበኙ መሆናቸው ታውቋል።