ፈልግ

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከካሜሮን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባሄ አባላት ጋር በካሜሮን የነበራቸው ቆያት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከካሜሮን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባሄ አባላት ጋር በካሜሮን የነበራቸው ቆያት  

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የርዕሰ ሊቀ ጳጳሳትን የሰላም መልእክት ለካሜሩን ሕዝብ አቀረቡ!

የቫቲካን ወይም የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከባለፈው ሐሙስ ከጥር 20/2013 ዓ.ም ጀምሮ በካሜሮን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ካርዲናል ፔትር ፓሮሊን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለካሜሩን እና ለአፍሪካ አህጉር ያላቸውን ቅርበት እና መልካም ሐሳብ የገለጹ ሲሆን ይህንን መልእክት ያደረሱት ደግሞ በእንግሊዘኛው ቋንቋ The pallium (ፓሊየም የሚለው ቃል የተወሰደው ፓሊየም ወይም ፓላ ከሚለው ከላቲን ቋንቋ ሲሆን የሱፍ ካባ የሚለውን ቃል ያሰማል፣ ይህም ፓሊየም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል መስዋዕተ ቅዳሴ የሚደረግበት አልባስ ሲሆን በትከሻ ላይ የሚንጠለጠል ነጭ የሱፍ ጨርቅ  ያካትታል። እሱ እረኛው እንደ ክርስቶስ በትከሻው ላይ የሚሸከሙውን በጎች ይወክላል፣ እናም ስለዚህ አለባበሱ የእረኝነት ተግባር ምልክት ነው። መጠሪያው በላቲን ቋንቋ ፓሊየም ፣ የሮማውያን ባህል ዓይነተኛ የሱፍ ካባ መገለጫ ነው። በተለያዩ አገራት ውስጥ ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያላቸውን ሕብረት የሚገልጽ ምልክት ሲሆን አሁንም ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አርማ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል) ይህንን የሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አርማ የባሜንዳ ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት አንድሪው ንካ ፉአንያ ባስረከቡበት ወቅት እንደ ነበረም ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ካሜሮን ያጋጠማትን እና አሁንም እያጋጠማት ያሉትን ችግሮች በሚገባ እንደ ሚያውቁ የገለጹት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በተለይም በተለያዩ አሸባሪዎች ምክንያት በሚቃጡ ጥቃቶች የተነሳ ሰለባ ለሆኑት ወይም በዚህ ቀውስ ውስጥ ቤተቦቻቸውን ላጡ ሰዎች የጌታን መጽናናት እንደ ሚመኙላቸው እና በጸሎት ከእነርሱ ጋር እንደ ሆኑ አክለው ገልጸዋል።

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፐትሮ ፓሮሊን በብሌንዳ ካቴድራል በተደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ ፓሊየም በመባል የሚታወቀውን የሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አርማ ለሊቀ ጳጳስ አንድሪው ንካ ፉአና ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለካለሜሩን ህዝብ እንዲሁም ለመላው የአፍሪካ አህጉር ያላቸውን ቅርበት በተወካያቸው በካርዲናል ፓሮሊን አማካይነት ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ከዚህች ተወዳጅ እና አስደናቂ ምድር ወደ እግዚአብሔር ለሚነሳው የሰላምና የእርቅ ፍላጎት የሚደረገው ጸሎት እንደ ሚቀላቀሉ” ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አክለው ገልጸዋል።

እርቅ ፣ ርህራሄ ፣ እንግዳ ተቀባይነት

ካርዲናል ፓሮሊን ባለፈው ሐሙስ ጥር 20/2013 ዓ.ም ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግኝኑነት በበላይነት የከሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቡነ ኢቫን ሳንተስ ጋር በመሆን በካሜሮን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ እዚያው መጓዛቸው ይታወሳል።

የእነርሱ ጉብኝት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለአፍሪካ አህጉር ያላቸውን ቁርጠኝነት እና የአብሮነት ተጨባጭ ምልክት እና ርህራሄን ፣ እርቅ እና ፈውስን ለማበረታታት ጥሪ ለማድረግ በተለይም ደግሞ ከኮቪድ -19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ተገልጿል።

ከርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ጋር ያለው ኅብረት

በባሜንዳ ካቴድራል ውስጥ በተደረገው ስነ ስረዓት ላይ ካርዲናል ፓሮሊን “ፓሊየም” በመባል የሚታወቀው የጳጳሳት ሐዋርያዊ አርማ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያለንን ልዩ ኅብረት እና ትስስር የሚገልጽ ምልክት እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን በቅድስት አኜስ አመታዊ በዓል ላይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚባረክ ከበግ ጸጉር የሚሰራ የጠፋውን በግ ፍለጋ ሄዶ በጉን ባገኘ ጊዜ በትከሻው ላይ ተሸክሞ የመጣውን መልካሙ እረኛ የሚያመለክት ሐዋርያዊ ገጽታ ያለው ምልክት እንደ ሆነ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የገለጹ ሲሆን እያንዳንዱ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመተባበር የሚያከናውኗቸውን ሐዋርያዊ ተግባራት እንደ ሚወክል አብራርተዋል። የእያንዳንዱ አዲስ ሊቀ ጳጳስ ተልእኮ-አዲሱ አገልግሎቱ ከመጀመሪያው ጀምሮ በኅብረት ምልክት ትስስር በመፍጠር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በታዝዞ እና በመተባበር እንዲያከናውኑ የሚያስታውስ መልክት እንደ ሆነ፣ እንዲሁም ሊቀ ጳጳሱ ከወንድሞቹ ኤጵስቆፖሳት ጋር በመተባበር መስራት እንደ ሚገባው የሚያስታውስ ሐዋርያው እና መንፈሳዊ ይዘት ያለው ምልክት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን በኪስ ውስጥ ይዞ መጓዝ

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን መልእክታቸውን ሲቀጥሉ “ብዙ ድምፆች በዙሪያችን የሚደመጡ ቢሆንም ብዙዎች በሕይወታችን ውስጥ እንደ አስተማሪ ሆነው መሥራት ይፈልጋሉ” ሲሉ አጥብቀው እና አጽኖት ሰጥተው  የተናገሩ ሲሆን ስለሆነም “ለክርስቶስ ቃል ልዩ ክብደት” መስጠት አለብን በማለት ገልጸዋል።

አክለውም “በዚህ ምክንያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለያዩ አጋጣሚዎች ትንሼዬ መጽሐፍ ቅዱስ በኪሳችን ውስጥ ይዘን እንድንጓዝ በተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸውን” ያስታወሱት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን “በኪሳችን ያለው የእግዚአብሔር ቃል መፈክር ሳይሆን መንፈሳዊ የሆን እቅድ ነው” ብለዋል።

የቃሉ ውጤታማነት

ካርዲናል ፓሮሊን “ኢየሱስ ለሰው ልጆች መልካምን ይመኛል፣ ስለሆነም ከክፉ ነፃ ያደርገናል” በማለት በመልእክታቸው አክለው የገለጹ ሲሆን "ኢየሱስ ትሁት በሆኑት እና ኃይል ባላቸው ቃላቱ አማካኝነት በትክክል እኛን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣት ይችላል፣ ቃሉ ከእርሱ ሲወጣ ሕይውትን ይቀይራል! ምንም ዓይነት አስማታዊ የሆኑ ቀመሮችን አይጠቀምም፣ ለእኛ እንግዳ የሆኑ ምልክቶችም እንኳን የሉም ፣ እሱ እጅግ ውጤታማ የሆነው በግልጽ የተቀመጠ ቃል ነው።" ማለታቸው ተገልጿል።

የቅድስት መንባር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ክፉ የሆነ መንፈስ አለ፣ ነገር ግን ክርስቶስ ማነኛውንም ክፉ የሆነ መንፈስ ሊያሸንፍ ይችላል፣ በእየቀኑ ይህንን ውጊያ ማካሄድ የእኛ ፈንታ ነው” ብለዋል።

መረጋጋት እና ንቃት

በመቀጠልም ካርዲናል ፓሮሊን የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊ ጉዞ የሚያመለክቱ ሁለት አስፈላጊ ጭብጦችን በመጥቀስ የሐዋርያው ​​ጳውሎስን ትምህርት ያስታወሱ ሲሆን እነዚህም ውብ የሆኑ እና በሕይወታችን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጋጋት እና ንቃት የተሰኙ ቃላት ናቸው ብለዋል።

"መረጋጋት ያስፈልጋል ምክንያቱም በክርስቶስ አማካይነት እኛ በጸሎት እና በቅዱስ ቁርባን በእርሱ ርዳታ በመታገዛችን ጠላትን ድል ነስተናል። መንቃት ያስፈልጋል ምክንያቱም ከራሳችን ልብ ጀምሮ ክፉ መንፈስ የሚሸሸግበትን ቦታ ለይተን ማወቅ እንችል ዘንድ ንቁ መሆን ይኖርብናል” ብለዋል።

የተስፋ ዘር

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፍ የሆኑት ካርዲናል ፓሮሊን በመቀጠል በካሜሩን የሚኖሩ ምዕመናን የሚጎዱ ሁከቶችን ፣ ክፍፍሎችን እና የእርስ በእርስ ሽኩቻን እንዲታገሉ ያሳሰቡ ሲሆን በልቡ ውስጥ ከሚኖረው ክፋት ጋር የሚዋጋ ሰው በቤተሰቡ ውስጥ ፣ በጓደኞቹ ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ መልካም እና ሰላምን የሚያመጣ መሳርያ ይሆናል፣ በእዚህም ለሁሉም የተስፋ ዘር ይሆናል ብለዋል።

የመንፈሳዊ ኩራት አደጋን ማስወገድ

የቫቲካን ወይም የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አክለው እንደ ገለጹት ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ በጌታ በኢየሱስ ፊት ሆነን እርሱ በሰራቸው ሥራዎች መደነቅ በጥንቃቄ የሚጠበቅ ውድ አመለካከት መሆኑን በማስታወስ በእለቱ ያደረጉትን ንግግር አጠናቀዋል።

ስለ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ቀድሞውኑ እንደሚያውቁ እርግጠኛ ለሆኑት ሰዎች በመንፈሳዊ ኩራት የመያዝ አደጋን ለማስወገድ በዚህ ምስጢር ላይ ማሰላሰላችንን ፈጽሞ ማቆም የለብንም ፣ እሱ በሰው ልጆች መረዳት ከምንችለው በላይ ሁል ጊዜ ድንቅ የሆነ አምላክ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል። በጭራሽ ማቆም የለብንም። በክርስቲያናዊ እምነታችን መሠረታዊ ምስጢር ፊት መደነቅ ማለት እኛን ነፃ ሊያወጣ ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ምስጢር ላይ ማሰላሰል ማለት ነው።

በባሜንዳ ካቴድራል ውስጥ በተደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ስርዓት እጅግ በርካታ ምእመናን የተገኙ ሲሆን ምዕመኑ ለሊቀ ጳጳሱ ፉአንያ ያላቸውን ፍቅር እና ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያላቸውን ሕብረት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

01 February 2021, 20:46