ፈልግ

የእስታ ቃጠሎ አደጋ በአውስትራሊያ የእስታ ቃጠሎ አደጋ በአውስትራሊያ  

ካርዲናል ፓሮሊን ከፓሪስ ስምምነት በኋላ “የመንከባከብ ባህል” ማዳበር ያስፈልጋል አሉ!

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ሁለት አስፈላጊ ክንውኖችን የሚያመለክቱ መልእክቶችን በቪዲዮ መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን እነዚህ አበይት ክንውኖች እ.አ.አ በ2015 የተከናወነው የፓሪስ ስምምነት እና እ.ኤ.አ. ከሕዳር 11-12/2020 ዓ.ም ደረስ ግላስኮ በመባል በምትታወቀው የስኮትላንድ ከተማ የተካሄደው በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል COP-26 (Conference of the Parties በአማርኛው የፓርቲዎች ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የስብሰባው ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል) 26 ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንደ ሆኑ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገልጸዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ከተካሄደ እነሆ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊነቱ አሁንም “የአቀበት” ጉዞ እያደርገ እንደ ሆነ የገለጹት የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን  በዚህ በቫቲካን የፈረንሣይ፣ የእንግሊዝ እና የጣሊያን ኤንባሲዎች አማካይነት በተዘጋጀው እና በቪዲዮ በተደርገው ኮንፈረንስ  የአየር ንብረት ለውጥን መጋፈጥ- ከፓሪስ እስከ በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል COP-26 (Conference of the Parties በአማርኛው የፓርቲዎች ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የስብሰባው ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል) 26 ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባሄ በሚል ርዕስ ሐሙስ ታሕሳስ 01/2013 ዓ.ም በተካሄደው የቪዲዮ የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች ለነበሩ ሰዎች ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በቪዲዮ-መልእክት አስተላልፈዋል፣ በመልእክታቸውም ካርዲናል ፓሮሊን እንደ ገለጹት “በፓሪሱ ስምምነት የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት በአገሮች የተያዙት ወቅታዊ የአየር ንብረት ለውጥን ለማቃለል እና ለማጣጣም የገቡት ቁርጠኝነት በእውነቱ ከፓሪሱ ስምምነት እጅግ የራቀ ናቸው” ብለዋል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ማህበራዊ እና ባህላዊ ተግዳሮቶች

በሌላ በኩል ደግሞ ኮቪድ -19 በመባል የሚታወቀው ወረርሽኝ እና የዓለም ሙቀት መጨመር ዓለማችን ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮቶች እየገጠሟት እንደ ሆነ በመልእክታቸው የገለጹት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን “እኛ እራሳችን እውነተኛ ማህበራዊ እና ባህላዊ ተግዳሮት እያጋጠመን ነው” ብለዋል። ካርዲናል አክለው እንደ ገለጹት  ለዚህ ችግር ምላሽ ለመስጠት አዲስ ባህላዊ ዘይ ወይም ሞዴል “የመንከባከብ ባህል” ማዳበር አለብን ብለዋል።አክለውም “ግድየለሽነት ፣ የመበስበስ እና የብክነት ባህል ባለበት ቦታ እራሳችንን ፣ ሌሎችን እና አካባቢያችንን ረስተናል” ያሉ ሲሆን ለራስ ፣ ለሌሎች እና ለአካባቢ ጥበቃ ራሳችንን ማዘጋጀት ይኖርብናል ብለዋል።

ግንዛቤ፣ ጥበብ፣ ፍላጎት

ይህ አዲስ ባህላዊ ሞዴል ካርዲናል ፓሮሊን መልእክታቸውን ሲቀጥሉ እንደ ተናገሩት “በፓሪስ ስምምነት ውስጥ” ሕይወት አስትንፋስ እንዲኖራት የሚያስችሉ ሶስት ፅንሰ-ሀሳቦችን ማለትም ግንዛቤ ፣ ጥበብ እና ፍላጎት ማካተት አለባቸው ብለዋል።

የመጀመሪያው ፅንሰ-ሀሳብ ግንዛቤ የሚለው ሲሆን “የተለያዩ ስነ-ትምህርቶች ወደ ውይይቱ ለማምጣት እና በዚህም ግንዛቤ ለፍጠር እና የእውቀታችንን አድማስ እና ስፋት ከፍ ለማድረግ በአካላዊ ሳይንስም ሆነ በሰብዓዊ ሳይንስ  ምርምር ማዕከላዊነት ጋር የተቆራኘ ነው” ብለዋል።

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አክለው እንደ ገለጹት “በሰፋፊ እና ገንቢ የስነምግባር ግንዛቤዎች የተቀረፀ ገምጋሚ ​​መነፅር” በማለት የገለፁት ጥበብን የተመለከተ አስተያየት የሰጡ ሲሆን “የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ አካል ከረጅም ልምዶች በተወለደ ጥበቡ በዚህ ረገድ እጅግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል” ብለዋል። በተለይም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተጻፈው በላቲን ቋንቋ “Laudato Si” ’(ውዳሴ ለአንተ ይሁን) ውስጥ የተካተተው “የበለፀገ ትምህርት” እንደ ሚገኝ በዋቢነት ገልጸዋል።

በሦስተኛው እና ፍላጎት በሚለው ፅንሰ-ሀሳብ ላይ በማተኮር ካርዲናል ፓሮሊን ለሰፊው ማሕበርሰብ ይህ ሐሳብ ሲቀርብ ጉዳዩ የፖለቲካ ፍላጎት እንደሚሆን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። ግንዛቤን እና ጥበብን በተመለከተ ባለፉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ መፍትሄዎች በእነዚህ አካባቢዎች ከፍተኛ መሻሻል የታየበት መሆኑን እና የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ውይይቶች ላይ በሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎና “በአሁኑ እና መጪው ትውልድ ” ላይ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰተውን ተግዳሮ ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ያሉ ሲሆን ሆኖም “በፖለቲካ ፍላጎት ዙሪያ ያለው እድገት የቀዘቀዘ ይመስላል” ብለዋል።

የፓሪስ ስምምነትን ተቀብለን በሥራ ላይ ማዋል ያለፉትን ክስተቶች ለማክበር ብቻ ሳይሆን ፣ እንዲሁም ለሁለት ቀናት ያህል ተካሂዶ ያለፈው COP-26 (Conference of the Parties በአማርኛው የፓርቲዎች ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የስብሰባው ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል) 26 ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ውስጥ የሚከናወነው እንደ “ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ለማምጣት ፍላጎት ማሳየት” ያሉ የወደፊት ክስተቶችንም ለማምጣት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፈቃደኝነትን ማጠናከሩ እዚህ የምንገኝበት አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል። ለመጪው ዓመት ለሁለተኛ አጋማሽ የተቀመጠው ጊዜ COP-26 (Conference of the Parties በአማርኛው የፓርቲዎች ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የስብሰባው ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል) 26 ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና የዝግጅት ሂደት ነው ”ብለዋል።

ተጨባጭ ውሳኔዎች

“አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ” አሉ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት “አሁን ያለውን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ አካባቢያዊ እና የስነምግባር ቀውስ በአኗኗራችን ላይ ለውጥ እንዲመጣ ለማበረታታት እና ከአሁን በኋላ ሊዘገዩ የማይችሉ ተጨባጭ ውሳኔዎችን ለመውሰድ እንደ አንድ አዲስ አጋጣሚ እንድንመለከት” ተጠርተናል ብለዋል።

በተጨማሪም የCOP-26 (Conference of the Parties በአማርኛው የፓርቲዎች ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የስብሰባው ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል) 26 ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስብሰባ እና በከፍተኛ ደረጃ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ፍላጎት የተንጸባረቀበት ጉባሄ “እነዚያ በአኗኗር ላይ ለውጦችን ለማድረግ እና ተጨባጭ እና የማይዘገዩ ውሳኔዎችን የሚወስድበት ጊዜ እንደደረሰ በግልጽ ለማሳየት እድል እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጣልቃ ገብነት

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በቪዲዮ በተደርገው ኮንፈረንስ ላይ ለታደሙ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12/2020 ዓ.ም በቪዲዮ በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ያስተላለፉትን ሁለት አብይት ቁምነገሮችን አስታውሰዋል።

የመጀመሪያው “በመካከላችን ላሉት በጣም አቅመ ደካማ እና ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች” ትኩረት የሚሰጥ “በሰው ልጆች መካከል ያለው ቃል ኪዳን” ነው ያሉ ሲሆን ሁለተኛው ነጥብ “በተለይም በወጣቶች መካከል አዲስ የአኗኗር ዘይቤን እና የጋራ ሰብአዊነታችንን አዲስ የሚያበረታታ እና ነገሮችን በምንመለከትበት መንገድ ላይ ለውጥ እንዲመጣ የሚያደርግ” የትምህርት ሂደትን የሚደግፉ “ፖለቲካዊ እና ቴክኒካዊ መፍትሄዎችን” ያመለክታል ብለዋል።

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፓሮሊን በቪዲዮ በተደረገው ስብሰባ ላይ ያስተላለፉትን መልእክት ሲያጠቃልሉ COP-26 (Conference of the Parties በአማርኛው የፓርቲዎች ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የስብሰባው ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል) 26 ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ  ስብሰባ እና “የፓሪስ ስምምነት አስፈላጊነትን በእርግጠኝነት አረጋግጣለሁ” ያሉ ሲሆን በተጨማሪም “የጋራ ፍላጎትን እና የግለሰቦችን ምኞት ደረጃ ለመለካት እና ለማበረታታት አስፈላጊ ጊዜ ይሆናል” ካሉ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

10 December 2020, 15:25