የአንድነትና የትብብር ዓላማን የሚያሳድግ ስፖርታዊ ጨረታ የሚካሄድ መሆኑ ተነገረ።
በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አነሳሽነት የተጀመረው የአንድነት እና የትብብር የሩጫ ውድድር ከሰኔ 1 - ነሐሴ 2/2012 ዓ. ም. የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። ዘንድሮ የሚካሄዱት የአትሌቲክስ ስፖርት ውድድሮች አዳዲስ ሽልማቶችን የሚያስገኙ እና ማኅበሩን ለማሳደግ የሚያግዙ ጨረታዎች የሚቀርቡበት መሆኑ ታውቋል። ከዓላማው አንዱ የቫቲካን አትሌትክስ ማኅበርን ለረጅም ዓመታ ሲደግፍ እና ሲያበረታታ የቆየው ጣሊያናዊ አትሌት አሌክስ ዛናርዲን በቅርቡ ከደረሰበት አደጋ እንዲያገግም እና ለማበረታታ መሆኑ ታውቋል።
የቫቲካን ዜና፤
በጣሊያን ውስጥ ቤርጋሞ እና ብሬሻ ከተሞች የሚገኙ ሆስፒታሎችን ለማገዝ የተለያዩ የእርዳታ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ማዘጋጀት ይቻላል በማለት “We Run Together” የተባለ የአትሌቶች ዕርዳታ ማሰባሰቢያ ማኅበርን ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ መመስረታቸው ታውቋል። የቫቲካን አትሌቲክስ ማኅበርን ከሌሎች ማኅበራት ጋር በማስተባበር “We Run Together” ለተባለ የአትሌቶች ዕርዳታ ማሰባሰቢያ ኅብረት ለማደራጀት ቅዱስነታቸው ዕርዳታ ማድረጋቸው ታውቋል። ግንቦት 12/2012 ዓ. ም. የቫቲካን አትሌቲክስ ቡድንን በቫቲካን ተቀብለው ያነጋገሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ስፖርትን ማሳደግ ለዘመናችን ማኅበረሰብ እጅ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተው፣ የስፖርት ጥቅም በማኅበረሰብ መካከለ አቅመ ደካማ ወደ ሆኑት በመሄድ ምስክርነትን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን አስረድተው፣ ለኦሊምፒክ አሸናፊዎች፣ ለታራሚዎች ፣ ለስደተኞች እና ለአካል እና ለአዕምሮ ጉዳተኞች እኩል ሰብዓዊ ክብርን የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል።
ስፖርት የሚሰጠው ልዩ ዕድል፣
ዘንድሮ ከሰኔ 1 - ነሐሴ 2/2012 ዓ. ም. በሚካሄደው “We Run Together” የተባለ የአትሌቶች ዕርዳታ ማሰባሰቢያ ውድድር፣ ወንዶች እና ሴቶች የሚሳተፉባቸው ደማቅ ውድድሮች በመካሄድ ላይ መሆናቸው ታውቋል። በውድድሩ ሥፍራ ሕጻናትን ጨምሮ ወጣቶች እና አዛውንት ተገኝተው የሚመለከቱት መሆኑ ታውቋል። ስፖርታዊ ውድድሮች ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የሚያቀራርብ እና የሚያስተምር፣ ወዳጅነትን የሚያሳድግ፣ ሰብዓዊ እና መንፈሳዊ ዕድገትን በተግባር የሚገልጽ መሆኑ ታውቋል።
የአሌክስ ዛናርዲ በሕይወት የመቆየት ምኞት፣
ታዋቂው ጣሊያናዊ አትሌት አሌክስ ዛናርዲ “We Run Together” የተባለ የአትሌቶች ዕርዳታ ማሰባሰቢያ ማኅበርን ለመርዳት ከተነሱት መካከል አንዱ መሆኑ ታውቋል። ታዋቂው የፓራሊምፒያድ አትሌቲክስ ስፖርት ተወዳዳሪው በብራዚል ሪዮ ዴ ጀኔይሮ ውድድር ያገኘውን የአሸናፊነት ሜዳሊያ በሁለት የቫቲካን አትሌቶች አማካይነት ለቫቲካን ማበርከቱ ታውቋል። ታዋቂው አትሌት አሌክስ ዛናርዲ በጣሊያን ውስጥ የሚገኙ የአካል ጉዳተኞች አትሌቲክስ ማኅበር በማስተባበር የአገሩን ሕዝብ አንድነት የሚያጠናክሩ ውድድሮችን ሲካፈል መቆየቱ እና ለአገሩ ያለውን ፍቅር እየገለጸ ለመቆየት ምኞት ያለው መሆኑን አስታውቋል። አትሌት አሌክስ ዛናርዲ ሰኔ 12/2012 ዓ. ም. በደረሰበት አደጋ ተስፋን ሳይቆርጥ ከቫቲካን አትሌቲክስ ማኅበር ጋር በመተባበር እሑድ ሰኔ 21/2012 ዓ. ም. በጣሊያን ሳንታ ማርያ ዲ ሉካ በሚደረግ የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ለመገኘት የወሰነ መሆኑ ታውቋል።
ሦስተኛ ዙር ውድድር፣
ዘንድሮ በመካሄድ ላይ የሚገኘው “We Run Together” የአትሌቲክስ ውድድር ሦስተኛ ዙሩን የያዘ ሲሆን፣ በዚህ ውድድር ላይ ለመካፈል ለሚፈልጉት የአትሌቲክስ አፍቃሪዎች ዕድሉ ክፍት መሆኑ ታውቋል። በውድድሩ ላይ ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የተበረከተው የሐርሌም ግሎብትሮቴርስ የአትሌቲክስ ማኅበር ታሪካዊ ማለያ፣ ለ“We Run Together” አትሌቲክስ ማኅበር ድጋፍ እንዲሆን ለጨረታ የሚቀርብ መሆኑ ታውቋል። በዘንድሮ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት የማነ ክሪፓ በ10,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር የሚካፈል መሆኑ ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሳተፍ ዕውቅናን ያተረፉ ሴት አትሌቶች ከሰኔ 26/2012 ዓ. ም. ጀምሮ የአጭር እና የረጅም ርቀት ውድድሮች ላይ ተካፋይ እንደሚሆኑ ታውቋል።
የእግር ኳስም ቡድኖችም በጨረታው ይሳተፋሉ፣
እስከ ነሐሴ 2/2012 ዓ. ም. የሚደረጉት ውድድሮች ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን የሚያካትቱ መሆኑ ሲታወቅ ከእነዚህም መካከል ታዋቂዎቹ የጣሊያን የእግር ኳስ ቡድኖች፣ ከእነዚህም መካከል ጁቬንቱስ፣ ሚላን፣ ሮማ፣ ላሲዮ እና ፊዮሬንቲና ቡድኖች ተጫዋቾች እና የቡድኖቹ መሪዎች በውድድሮቹ ጣልቃ በሚቀርቡ ጨረታዎች የሚካፈሉ መሆኑ ታውቋል። ውድድሮችን እና የተለያዩ ዝግጅቶችን በሥፍራው ተገኝተው የሚዘግቡት ቫቲካን ኒውስ እና ራዲዮ ቫቲካና የጣሊያንኛ ቋንቋ አገልግሎት መሆናቸው ታውቋል።