ፈልግ

በሮም አቅራቢያ፣ ካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኝ የርዕሣነ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ወራት ማረፊያ፤ በሮም አቅራቢያ፣ ካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኝ የርዕሣነ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ወራት ማረፊያ፤ 

የጤና ባለሞያዎች የቫቲካን ሙዜሞችን እና ጳጳሳዊ ሕንጻዎችን በነጻ እንዲጎበኟቸው መጋበዛቸው ተነገረ።

ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን የቫቲካን ሙዜምን እና ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ ጳጳሳዊ ሕንጻዎችን የጤና ባለሞያዎች፥ ዶክተሮች፣ ነርሶች እና የጤና ረዳቶች በነጻ እንዲጎበኙ በማለት የቫቲካን ከተማ አስተዳደር መጋበዙ ታውቋል። ይህ ዕድል የተሰጣቸው የጤና ባለሞያዎች፣ በጣሊያን ውስጥ በመንግሥት ሆነ በግል የጤና ተቋማት በኩል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለተጠቁት ሕሙምን ላበረክቱት የሕክምና አገልግሎት እና ድጋፍ ምስጋናን ለማቅረብ መሆኑ ታውቋል። የጤና ባለሞያዎቹ ለአንድ ሳምንት ያህል በነጻ የሚጎበኟቸው ሙዜሞች እና ጳጳሳዊ ሕንጻዎች በቫቲካን ውስጥ እና ከሮም ወጣ ብሎ በሚገኝ ካስተል ጋንዶልፎ በተባለ ሥፍራ የሚገኙ መሆኑ ታውቋል።   

የቫቲካን ዜና

እጅግ ጥንታዊ የሚባሉ የቫቲካን ሙዜሞች እና ጳጳሳዊ ሕንጻዎች አንድ ላይ ለጤና ባለሞያዎች ክፍት የሚሆኑት ምስጋናን ለማቅረብ ከመሆኑ በተጨማሪ የሥነ-ጥበብ እና የሕክምናው ዘርፍ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት አጉልቶ ለማሳየት፣ የሰው ልጅ ከእነዚህ ሁለቱ ዘርፎች የሚያገኘውን የፈውስ አገልግሎት ለማሳየት መሆኑ ታውቋል።

የእምነት እና የባሕል ታላቅነት በስነ-ጥበባት አማካይነት በአስደናቂ መንገድ የሚገልጹ የቫቲካን ሙዜሞች እና ጥንታዊ የሆኑ ጳጳሳዊ ሕንጻዎች በጤናው ዘርፍ ለተሰማሩት ባለሞያዎች ክፍት የተደረጉት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በጣሊያን ውስጥ ተሰራጭቶ በነበረበት ወቅት ፣ በመንግሥት እና በግል የጤና ተቋማት ውስጥ በመሰማራት ለሕሙማኑ የሕክምና አገልግሎታቸውን እና ድጋፋቸውን ላበረከቱ የጤና ባለሞያዎች ከቅድስት መንበር በኩል ልባዊ ምስጋናን ለማቅረብ መሆኑ ታውቋል። የሕክምና ዶክተሮች፣ ነርሶች እና የጤና ረዳቶች የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃቸውን ወይም አገልግሎታቸውን ከሚያቀርቡባቸው የጤና ተቋማት የተሰጣቸውን መታወቂያ ብቻ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መሆኑ ታውቋል። የጤና ባለሞያዎቹ ከራሳቸው ሌላ አንድ ተጨማሪ ሰው ይዘው መግባት የሚችሉ መሆኑ ታውቋል።

ከቫቲካን ከተማ አስተዳደር የወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ የጤና ባለሞያዎቹ ቫቲካን ሙዜሞችን መጎብኘት የሚችሉት ከሰኞ ሰኔ 1/2012 ዓ. ም. እስከ ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓ. ም. ድረስ እንደ ሆነ ገልጾ፣ ሐሙስ ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል። መግለጫው በማከልም የጉብኝት ሰዓታት፣ ከሰኞ ሰኔ 1 ቀን - ረቡዕ ሰኔ 3/2012 ዓ. ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሲሆን አርብ እና ቅዳሜ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 መሆኑን አስታውቋል።

የቫቲካን ከተማ አስተዳደር በመግለጫው፣ የጤና ባለሞያዎቹ ጥንታዊ የሆኑ ጳጳሳዊ ሕንጻዎችን መጎብኘት የሚችሉባቸውን ቀናትን እና ሰዓታትን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት ቅዳሜ ግንቦት 29 እና እሑድ ግንቦት 30 2012 ዓ. ም. እና ሰኔ 6 እና 7/2012 ዓ. ም. ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12፡00 ድረስ መሆኑን አስታውቋል። 

06 June 2020, 17:06