ፈልግ

የቫቲካን ፍርድ ቤት፤ የቫቲካን ፍርድ ቤት፤  

በቫቲካን አዲስ የሥራ ውል እና የሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ መረቀቁ ተገለጸ።

በቅድስት መንበር እና በቫቲካን መንግሥት ሥር በሚገኙት ሐዋርያዊ እና ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች የሥራ ውሎችን ተመልክቶ ግልጽነታቸውን የሚያረጋግጥ ሕግ መውጣቱ ታውቋል።

የቫቲካን ዜና፤

ላለፉት አራት ዓመታት ያህል ጥናት ተደረጎበት ይፋ የተደረገው አዲስ ሕግ የቫቲካን መንግሥትን የሥራ ሂደት ለመከታተል፣ የሥራ ቅጥሮችን ግልጽ እና ተገቢ በሆነ መንገድ ሕጋዊ ለማድረግ የሚያግዝ ደንብ ሆኖ የሚቆይ መሆኑ ታውቋል። “የቫቲካን ከተማ የሥራ ውሎች ግልፅነት ፣ ቁጥጥር እና የመወዳደሪያ ደንቦች ቅድመ ዕይታ” በመባል የሚታወቀው ይህ ሕግ 86 አንቀጾች እና ተጨማሪ 12 አንቀጾች ያሉት መሆኑ ታውቋል። የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስን ሐዋርያዊ የግል ስልጣን እና መብት መሠረት በማድረግ ይፋ የሚሆነው ሕግ፣ በአስተዳደር ወስጥ የሚፈጠሩቱን አንዳንድ ግልጽነተ የሚጎድላቸውን የሥራ አካሄድ ተቆጣጥሮ ለማስተካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ካወጣው ሕግ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑ ታውቋል።

እንደ ቤተሰብ መልካም አባት፣

ይህን አዲስ ሕግ በማስመልከት ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ “የቤተሰብ መልካም አባት ትጋት” በማለት ባደረጉት ገለጻቸው፣ በቅድስት መንበር እና በቫቲካን መንግሥት ውስጥ የሚካሄዱ የሥራ አፈጻጸሞችን እና የአስተዳደር ሂደቶች በታላቅ ትኩርትን በመስጠት ተግባራዊነታቸውንም መከታተል የሚያስፈልግ መሆኑን አስረድተዋል።  ቅዱስነታቸው በማከልም በሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ የሚፈጸሙትን የሥራ ሂደቶች በማጥናት አስፈላጊ ለውጥ የማድረግ አንገብጋቢነት መኖሩን ገልጸዋል። በር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ የግል ስልጣን እና መብት መሠረት የተዘጋጀው አዲስ ሕግ በሥራ አፈጻጸም ላይ ግልጽነት እንዲኖር፣ አስፈላጊውን ቁጥጥር ለማድረግ የሚያግዝ፣ በቅድስት መንበር እና በቫቲካን መንግሥት ሥር ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች መብት እና ግዴታን የሚያስከብር ነው ተብሏል።

የሕጉ ዓላማ፣

አዲስ የወጣው ሕግ የመጀመሪያ አንቀጽ ቀዳሚ ዓላማ የገንዘብ አጠቃቀምን ፣ የሥራ ሂደቶች ግልፅነትን የሚያረጋግጥ፣ በተለይም ሕገወጥ እና ግልጽነት የሚጎድልባቸውን የሥራ አፈጻጸሞች በማረም እና በማስተካከል፣ በሚወሰዱ እርምጃዎች አማካይነት በተለይም የተቀጣሪዎችን መብት በማስከበር፣ አድልዎ የሌለበት እኩል አስተያየት ለመዘርጋት የሚያግዝ ሕግ መሆኑ ታውቋል።      

መሠረታዊ መርሆዎች

አዲስ የወጣው ሕግ አምስተኛ አንቀጽ በዝርዝር እንዳስቀመጠው፣ የቤተክርስቲያኒቱን ማኅበራዊ አስተምህሮ ደንቦችን መሠረት በማድረግ፣ ኤኮኖሚያዊ በሆኑ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የልዩ ልዩ ጽሕፈት ቤቶች የአስተዳደር ሚናን ከፍ በማድረግ እንዲሁም በልዩ ልዩ ጽሕፈት ቤቶች መካከል ያለውን አንድነት እና ትብብር በማሳደግ፣ ኤኮኖሚያዊ ሥራዎችን ፍሬያማ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል። በኤኮኖሚ ዘርፉ የሚጸድቁ ውሳኔዎች ትክክለኝ ኣመርሃ ግብርን የተከተሉ እና አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ፣ ግልጽነትን ለመከተል የሚያግዝ መሆኑ ታውቋል።  

የቫቲካን ሠራተኞች በፍርድ ሰጭ ምክር ቤት ዓይን ሲገመገሙ፣

በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ የፍላጎት አለመመጣም መታየት እንደሌለበት የሚደነግገው አዲሱ ሕግ፣ በተለይም በገንዘብ ተቋማት መካከል ግልጽነት እና እኩልነት እንዲገለጽ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። በኤኮኖሚ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የሞያ ብቃት እና የሥራ ልምድ የሚገመግም ክፍል በጊዜያዊነት ተቋቁሞ በተለይም ከፍርድ ሰጭ አካላት ጋር ተባብረው እንዲሠሩ የሚደረግ መሆኑ ታውቋል። በሠራተኞች የሞያ ዘርፍ እና በተሰማሩበት የሥራ ዓይነት ጋር የሚኖረውን መጣጣም የሚገመግም ክፍል የሚቋቋም መሆኑ ታውቋል። 

አዲሱ ሕግ ዓለም አቀፍ ልምዶችን የተከተለ እንዲሆን ማድረግ፣

መሠረታዊ መርሆዎችን እና ዓላማዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፣ የቫቲካን መንግሥት ቀኖናዊ ሕጎችን በመከተል፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሐዋርያዊ የግል ስልጣናቸው ያወጁት አዲሱ ሕግ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ የሌሎችን በርካታ መንግሥታት “መልካም ልምዶች” በምሳሌነት የተመለከተ መሆኑ ታውቋል።

03 June 2020, 17:56