ፈልግ

የኢራቅ ተፈናቃዮች አካባቢያቸውን ለቀው ሲሄዱ፣ የኢራቅ ተፈናቃዮች አካባቢያቸውን ለቀው ሲሄዱ፣ 

ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚውል የሐዋርያዊ አገልግሎት መመሪያ ይፋ መደረጉ ተገለጸ።

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት፣ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ መምሪያ፣ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሊሰጥ የሚገባ ሐዋርታዊ አገልግሎት በማስመልከት ውይይት ማድረጉ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

መምሪያው፣ በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ሊቀርብ የሚገባውን ሐዋርያዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን የሚያስቀምጥ ባለ 122 ነጥብ የአገልግሎት መመሪያን ይፋ ማድረጉን አስታውቋል። ታውቋል። በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ይህን መመሪያ ያዘጋጀበት ዋና ዓላማ በጦርነት፣ በአመጽ እና በሌሎች ማኅበራዊ ችግሮች ምክንያት የሚኖሩበትን አካባቢ ለቀው ለሚፈናቀሉ ቤተሰቦች የመጠለያ፣ የከለላ፣ ራሳቸውን ከሚኖሩበት ማኅበረሰብ ጋር የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን ለማሳየት እና እነዚህን ተግባራት አጠናክሮ ለመገኘት መሆኑ ታውቋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር እስከ 20181 ዓ. ም. መጨረሻ ድረስ በዓለማችን 41.3 ሚልዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መመዝገባቸው የተገለጸ ሲሆን እነዚህም በአካባቢያቸው በሚነሱት ጦርነቶች እና አመጾች ምክንያት የሚሰደዱ ቢሆንም ሕጋዊ ዓለም አቀፍ እውቅና ያልተሰጣቸው፣ ሰብዓዊ እርዳታን እና የሕይወት ከለላን የማያገኙ መሆኑ ታውቋል። የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሕጋዊ መንገድ ዓለም አቀፍ ዋስትናን የማያገኙ ከሆነ የሚደርስባቸውን ስቃይ ተሸክመው በአገራቸው የሚንከራተቱ መሆኑ ታውቋል። በበርካታ አካባቢዎች የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እውቅናን ሳያገኙ፣ ከብዙሃን መገናኛ እይታ ተሰውረው የሚኖሩ መሆኑ ታውቋል። በዚህ ምክንያት የዕለተ ዕለት ስቃያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት፣ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ መምሪያ ያወጣው ሰነድ አመልክቷል።

በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በአግባቡ ማቃለል የሚቻልበትን መንገድ ለማግኘት ቤተክርስቲያን፣ ማኅበራዊ መገናኛዎችን በማስተባበር ለመንግሥታን እና ለማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማስጨበጥ የምትጥር መሆኑን መምሪያው አስታውቋል። በዚህ ረገድ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የበኩሉን እገዛ በማድረግ የአንድን አገር ሉዓላዊነት ማስከበር እንደሚያስፈልግ መምርያው አሳስቧል።

ይህን አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ ግልጽ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በማቅረብ ፍሬያማ የአገልግሎት ዘርፎችን ማዋቀር እንደሚያስፈልግ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት፣ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል።

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የሚጠቁ መሆኑን ያስታወሰው መምሪያው፣ ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ እርዳታ እና የሕይወት ከለላ እንዲሰጣቸው አሳስቧል። መምሪያው ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢዎች ከሚፈናቀሉባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በጎሳዎች መካከል በሚነሱ ግጭቶች መሆኑን አስረድቶ፣ ይህን አመጽ በማስወገድ፣ እርቅን እና ሰላምን ለማውረድ ቤተክርስቲያን የተጠራች መሆኗን አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ በአመጽ እና በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከቤተክርስቲያን እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚሰበሰቡ እርዳታዎች ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል በማለት መምሪያው አሳስቧል።

ይህን ዜና በድምጽ ማድመጥ ከፈለጉ የተጫወት ምልክትን ይጫኑ፣
06 May 2020, 16:19